ቲቶ 2 – NASV & NSP

New Amharic Standard Version

ቲቶ 2:1-15

1አንተ ግን ከትክክለኛው ትምህርት ጋር ተስማሚ የሆነውን አስተምር። 2አረጋውያን ጭምቶች፣ የተከበሩ፣ ራሳቸውን የሚገዙና በእምነት፣ በፍቅርና በትዕግሥት ጤናማነት ያላቸው እንዲሆኑ ምከራቸው።

3እንዲሁም አሮጊቶች በአኗኗራቸው የተከበሩ እንዲሆኑ፣ በጎ የሆነውን የሚያስተምሩ እንጂ የሰው ስም የሚያጠፉ ወይም በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ አስተምራቸው። 4እንዲህ ከሆኑ፣ ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ማስተማር ይችላሉ፤ 5የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።

6እንዲሁም ወጣት ወንዶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው። 7በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣ 8የማይነቀፍ ጤናማ አነጋገርንም አሳይ፤ ይኸውም ተቃዋሚ ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር በማጣት እንዲያፍር ነው።

9ባሮች ለጌቶቻቸው በማንኛውም ነገር እንዲገዙ፣ ደስ እንዲያሰኟቸውና የዐጸፋ ቃል እንዳይመልሱላቸው አስተምር፤ 10አይስረቁ፤ ይኸውም በሁሉም መንገድ የአዳኛችን የእግዚአብሔር ትምህርት ይወደድ ዘንድ ፍጹም ታማኝ መሆናቸውን እንዲያስመሰክሩ ነው።

11ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጧልና፤ 12ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤ 13ይህም የተባረከ ተስፋችን የሆነውን የታላቁን የአምላካችንንና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ በመጠባበቅ ነው፤ 14እርሱም ከክፋት ሊቤዠን፣ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚተጋውን የእርሱ የሆነውን ሕዝብም ለራሱ ያነጻ ዘንድ ራሱን ስለ እኛ ሰጥቷል።

15እንግዲህ ልታስተምር የሚገባህ እነዚህን ነው፤ በሙሉ ሥልጣን ምከር፤ ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።

New Serbian Translation

Титу 2:1-15

Живот у складу са учењем

1А ти говори оно што је у складу са здравим учењем: 2да старци буду трезвени, честити, разумни, здрави у вери, љубави, и стрпљивости.

3Старице такође нека се понашају како то приличи посвећеним женама: да не оговарају, да се не одају многом вину, него да поучавају што је добро. 4Онда нека саветују младе жене како да воле своје мужеве и своју децу, 5да буду разумне, чисте, добре домаћице, покорне својим мужевима, да се реч Божија не би ружила.

6Такође опомињи и младиће да буду разумни. 7У свему се покажи примером чинећи добра дела, буди искрен и озбиљан у учењу које излажеш. 8Нека твоје речи буду здраве и без приговора, да се противник застиди немајући шта лоше да каже о нама.

9Робови да се у свему покоравају својим господарима, да им угађају, да им не противрече 10и не поткрадају их, него да се у свему покажу оданима и добрима, тако да у свему красе учење Спаситеља, нашег Бога.

11Јер Бог је открио своју милост ради спасења свих људи. 12Она нас одгаја да одбацимо безбожност и световне жеље, те да живимо разумно, праведно и побожно у овом свету, 13очекујући блажену наду и славно појављивање нашега великога Бога и Спаситеља Исуса Христа. 14Он је дао себе за нас да нас откупи од сваког безакоња и да за себе очисти изабрани народ који предано чини добро.

15Ово говори и напомињи, користећи пуно право да кориш. Нико нека те не презире.