ሮሜ 9 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ሮሜ 9:1-33

የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫ

1በክርስቶስ ሆኜ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም፤ ኅሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል። 2ታላቅ ሐዘንና የማያቋርጥ ጭንቀት በልቤ አለ። 3ለወገኖቼ ስል ስለ ወንድሞቼ እኔ ራሴ የተረገምሁና ከክርስቶስም ተለይቼ የተጣልሁ እንድሆን እንኳ እወድድ ነበር፤ 4እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ ናቸው፤ ልጅ መሆን፣ መለኮታዊ ክብር፣ ኪዳን፣ ሕግን መቀበል፣ የቤተ መቅደስ ሥርዐትና ተስፋ የእነርሱ ናቸውና። 5አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው፤9፥5 ወይም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ይሁን ወይም ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን አሜን።

6ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ተሽሯል ማለት አይደለም፤ ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ እስራኤላዊ አይደለምና። 7ከአብርሃም ዘርም ስለ ሆኑ፣ ሁሉም ልጆቹ አይደሉም፤ ይልቁንስ፣ “ትውልድህ በይሥሐቅ በኩል ይጠራልሃል” እንደ ተባለው ነው። 8ይህም ማለት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት የሥጋ ልጆች አይደሉም፤ ነገር ግን የአብርሃም ልጆች የተባሉት የተስፋው ልጆች ናቸው። 9“ጊዜው ሲደርስ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች” ተብሎ ተስፋው ተሰጥቷልና።

10ይህም ብቻ ሳይሆን፣ የርብቃ ልጆች አንድ አባት አላቸው፤ እርሱም አባታችን ይስሐቅ ነው። 11መንትዮቹ ገና ሳይወለዱ፣ ወይም በጎም ሆነ ክፉ ሳያደርጉ፣ የእግዚአብሔር ሐሳብ በምርጫ ይጸና ዘንድ፣ 12በሥራ ሳይሆን ከጠሪው በመሆኑ፣ “ታላቁ ታናሹን ያገለግላል” ተብሎ ተነገራት። 13ይህም፣ “ያዕቆብን ወደድሁ፤ ዔሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።

14እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር አድልዎ ያደርጋልን? በፍጹም አያደርግም! 15ለሙሴ፣

“የምምረውን እምረዋለሁ፤

ለምራራለትም እራራለታለሁ” ይላልና።

16እንግዲህ ይህ ከሰው ፍላጎት ወይም ጥረት ሳይሆን፣ ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው። 17መጽሐፍ ፈርዖንን፣ “ኀይሌ በአንተ እንዲታይ፣ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲነገር ለዚህ አስነሣሁህ” ይላልና። 18ስለዚህ እግዚአብሔር ሊምረው ለሚወድደው ምሕረት ያደርግለታል፤ ልቡ እንዲደነድን የፈለገውንም ያደነድነዋል።

19ከእናንተ አንዱ፣ “ታዲያ እንደዚህ ከሆነ እግዚአብሔር እስከ አሁን ለምን ይወቅሠናል? ምክንያቱም ፈቃዱን ሊቋቋም የሚችል ማን አለ?” ይለኝ ይሆናል። 20ነገር ግን ለእግዚአብሔር መልስ የምትሰጥ አንተ ማን ነህ? “ሥራ ሠሪውን፣ ‘ለምን እንዲህ ሠራኸኝ?’ ይለዋልን?” 21ሸክላ ሠሪ፣ ከሚሠራው ጭቃ፣ አንዳንዱን ሸክላ ለክብር፣ ሌላውን ደግሞ ለተራ አገልግሎት የማድረግ መብት የለውምን?

22እግዚአብሔር ቍጣውን ለማሳየት፣ ኀይሉንም ለማሳወቅ ፈልጎ የቍጣው መግለጫ የሆኑትን፣ ለጥፋትም የተዘጋጁትን እጅግ ታግሦ ቢሆንሳ! 23አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው፣ የምሕረቱም መግለጫዎች ለሆኑት፣ የክብሩ ባለጠግነት እንዲታወቅ ይህን አድርጎ እንደሆነስ? 24የጠራው ከአይሁድ ወገን ብቻ ሳይሆን ከአሕዛብ ወገን የሆንነውን እኛን እንኳ ሳይቀር አይደለምን? 25በሆሴዕ እንዲህ እንደሚል፤

“ሕዝቤ ያልሆኑትን፣ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ”፤

“ያልተወደደችውንም ‘የተወደደችው’ ብዬ እጠራለሁ።”

26ደግሞም፣

“ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’፤

ተብሎ በተነገራቸው በዚያ ቦታ፣

‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።”

27ኢሳይያስም ስለ እስራኤል እንዲህ ሲል ይጮኻል፤

“የእስራኤል ልጆች ቍጥር በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣

ትሩፉ ብቻ ይድናል።

28ጌታ ፍርዱን በምድር ላይ፣

በፍጥነትና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈጽማልና።”

29ይኸውም ቀደም ሲል ኢሳይያስ እንደ ተናገረው ነው፤

“የሰራዊት ጌታ፣

ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፣

እንደ ሰዶም በሆን ነበር፤

ገሞራንም በመሰልን ነበር።”

የእስራኤል አለማመን

30እንግዲህ ምን እንበል? በእምነት የሆነውን ጽድቅ፣ ለጽድቅ ያልደከሙት አሕዛብ አገኙት፤ 31ነገር ግን የጽድቅን ሕግ የተከታተሉት እስራኤል አላገኙትም። 32ይህ ለምን ሆነ? በእምነት ሳይሆን በሥራ እንደ ሆነ አድርገው በመቍጠር ስለ ተከታተሉት ነው፤ እነርሱም፣ “በማሰናከያው ድንጋይ” ተሰናከሉ። 33ይህም፣

“እነሆ፤ ሰዎችን እንዲደናቀፉ የሚያደርግ ድንጋይ፣

እንዲወድቁ የሚያደርግ ዐለት፣

በጽዮን ላይ አስቀምጣለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም”

ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።

King James Version

Romans 9:1-33

1I say the truth in Christ, I lie not, my conscience also bearing me witness in the Holy Ghost, 2That I have great heaviness and continual sorrow in my heart. 3For I could wish that myself were accursed from Christ for my brethren, my kinsmen according to the flesh: 4Who are Israelites; to whom pertaineth the adoption, and the glory, and the covenants, and the giving of the law, and the service of God, and the promises; 5Whose are the fathers, and of whom as concerning the flesh Christ came, who is over all, God blessed for ever. Amen.

6Not as though the word of God hath taken none effect. For they are not all Israel, which are of Israel: 7Neither, because they are the seed of Abraham, are they all children: but, In Isaac shall thy seed be called. 8That is, They which are the children of the flesh, these are not the children of God: but the children of the promise are counted for the seed. 9For this is the word of promise, At this time will I come, and Sara shall have a son. 10And not only this; but when Rebecca also had conceived by one, even by our father Isaac; 11(For the children being not yet born, neither having done any good or evil, that the purpose of God according to election might stand, not of works, but of him that calleth;) 12It was said unto her, The elder shall serve the younger. 13As it is written, Jacob have I loved, but Esau have I hated.

14What shall we say then? Is there unrighteousness with God? God forbid. 15For he saith to Moses, I will have mercy on whom I will have mercy, and I will have compassion on whom I will have compassion. 16So then it is not of him that willeth, nor of him that runneth, but of God that sheweth mercy. 17For the scripture saith unto Pharaoh, Even for this same purpose have I raised thee up, that I might shew my power in thee, and that my name might be declared throughout all the earth. 18Therefore hath he mercy on whom he will have mercy, and whom he will he hardeneth. 19Thou wilt say then unto me, Why doth he yet find fault? For who hath resisted his will? 20Nay but, O man, who art thou that repliest against God? Shall the thing formed say to him that formed it, Why hast thou made me thus? 21Hath not the potter power over the clay, of the same lump to make one vessel unto honour, and another unto dishonour? 22What if God, willing to shew his wrath, and to make his power known, endured with much longsuffering the vessels of wrath fitted to destruction: 23And that he might make known the riches of his glory on the vessels of mercy, which he had afore prepared unto glory, 24Even us, whom he hath called, not of the Jews only, but also of the Gentiles? 25As he saith also in Osee, I will call them my people, which were not my people; and her beloved, which was not beloved. 26And it shall come to pass, that in the place where it was said unto them, Ye are not my people; there shall they be called the children of the living God. 27Esaias also crieth concerning Israel, Though the number of the children of Israel be as the sand of the sea, a remnant shall be saved: 28For he will finish the work, and cut it short in righteousness: because a short work will the Lord make upon the earth. 29And as Esaias said before, Except the Lord of Sabaoth had left us a seed, we had been as Sodoma, and been made like unto Gomorrha. 30What shall we say then? That the Gentiles, which followed not after righteousness, have attained to righteousness, even the righteousness which is of faith. 31But Israel, which followed after the law of righteousness, hath not attained to the law of righteousness. 32Wherefore? Because they sought it not by faith, but as it were by the works of the law. For they stumbled at that stumblingstone; 33As it is written, Behold, I lay in Sion a stumblingstone and rock of offence: and whosoever believeth on him shall not be ashamed.