ሮሜ 16 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ሮሜ 16:1-27

የግል ሰላምታ

1በክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ16፥1 ወይም ዲያቈን የሆነችውን እኅታችንን ፌቤንን ዐደራ እላችኋለሁ። 2ለቅዱሳን ተገቢ በሆነው አቀባበል በጌታ እንድትቀበሏትና ከእናንተም የምትፈልገውን ማንኛውንም ርዳታ እንድታደርጉላት አሳስባችኋለሁ፤ ለብዙ ሰዎችና ለእኔም ጭምር ታላቅ ድጋፍ ነበረችና።

3በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚያገለግሉት ለጵርስቅላና16፥3 በግሪኩ ጰርስቃ የጵርስቅላ ተለዋጭ ስም ነው። ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ። 4እነርሱም ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለዐደጋ አጋልጠው ሰጡ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል።

5በእነርሱ ቤት ላለች ቤተ ክርስቲያንም ሰላምታ አቅርቡልኝ።

ከእስያ አገር ለመጀመሪያ ወደ ክርስቶስ ለተመለሰው፣ ለወዳጄ ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

6ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

7ከእኔ ጋር ታስረው ለነበሩት ዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በሐዋርያት መካከል ስመጥሮችና በክርስቶስ በማመንም እኔን የቀደሙ ናቸው።

8በጌታ ለምወድደው ለጵልያጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

9በክርስቶስ አብሮን ለሚሠራው ለኢሩባኖንና ለውድ ወዳጄ ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

10በክርስቶስ ያለው እምነቱ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለኤጤሌን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤

ከአርስጣባሉ ቤተ ሰብ ለሆኑትም ሰላምታ አቅርቡልኝ።

11ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሰላምታ አቅርቡልኝ፤

በጌታ ላሉት ለንርቀሱ ቤተ ሰቦች ሰላምታ አቅርቡልኝ።

12በጌታ ሆነው በትጋት ለሚሠሩት ሴቶች፣ ለፕሮፊሞናና ለጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

በጌታ ሆና እጅግ ለደከመችው ለሌላዋ ሴት፣ ለተወደደችው ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

13በጌታ ለተመረጠው ለሩፎንና የእኔም እናት ለሆነችው ለእናቱ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

14ለአስቀሪጦንና ለአፍለሶንጳ፣ ለሄሮሜን፣ ለጳጥሮባን፣ ለሄርማን፣ ከእነርሱም ጋር ላሉት ወንድሞች ሰላምታ አቅርቡልኝ።

15ለፍሌጎን፣ ለዩልያ፣ ለኔርያና ለእኅቱ፣ እንዲሁም ለአልንጦን፣ ከእነርሱም ጋር ላሉት ቅዱሳን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

16በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።

የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

17ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጕዟችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ። 18እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ። 19የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።

20የሰላም አምላክ፣ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል።

የጌታችን የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

21አብሮኝ የሚሠራው ጢሞቴዎስ፣ እንዲሁም ዘመዶቼ የሆኑት ሉቂዮስ፣ ኢያሶንና ሱሲጴጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

22ይህን መልእክት የጻፍሁት እኔ ጤርጥዮስ፣ በጌታ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።

23በመልካም መስተንግዶው እኔና በዚህ የምትገኘዋ መላዋ ቤተ ክርስቲያን ደስ የምንሰኝበት ጋይዮስ፣ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።

የከተማዪቱ ግምጃ ቤት ሹም የሆነው ኤርስጦስ፣ ወንድማችንም ቍአስጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

24የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።16፥24 ቍጥር 24 የሚገኘው በአንዳንድ ቅጆች ብቻ ነው።

25-26በዘላለማዊ አምላክ ትእዛዝ ሕዝቦች ሁሉ አምነው እንዲታዘዙ፣ በነቢያት መጻሕፍት አሁን በተገለጠው፣ ላለፉት ረዥም ዘመናት ተሰውሮ በነበረው ምስጢር መገለጥ መሠረት፣ በአስተማርሁት ወንጌልና በኢየሱስ ክርስቶስ መሰበክ ሊያጸናችሁ ለሚችለው፣ 27እርሱ ብቻ ጥበበኛ ለሆነ አምላክ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

New International Version – UK

Romans 16:1-27

Personal greetings

1I commend to you our sister Phoebe, a deacon16:1 Or servant16:1 The word deacon refers here to a Christian designated to serve with the overseers/elders of the church in a variety of ways; similarly in Phil. 1:1 and 1 Tim. 3:8,12. of the church in Cenchreae. 2I ask you to receive her in the Lord in a way worthy of his people and to give her any help she may need from you, for she has been the benefactor of many people, including me.

3Greet Priscilla16:3 Greek Prisca, a variant of Priscilla and Aquila, my fellow workers in Christ Jesus. 4They risked their lives for me. Not only I but all the churches of the Gentiles are grateful to them.

5Greet also the church that meets at their house.

Greet my dear friend Epenetus, who was the first convert to Christ in the province of Asia.

6Greet Mary, who worked very hard for you.

7Greet Andronicus and Junia, my fellow Jews who have been in prison with me. They are outstanding among16:7 Or are esteemed by the apostles, and they were in Christ before I was.

8Greet Ampliatus, my dear friend in the Lord.

9Greet Urbanus, our fellow worker in Christ, and my dear friend Stachys.

10Greet Apelles, whose fidelity to Christ has stood the test.

Greet those who belong to the household of Aristobulus.

11Greet Herodion, my fellow Jew.

Greet those in the household of Narcissus who are in the Lord.

12Greet Tryphena and Tryphosa, those women who work hard in the Lord.

Greet my dear friend Persis, another woman who has worked very hard in the Lord.

13Greet Rufus, chosen in the Lord, and his mother, who has been a mother to me, too.

14Greet Asyncritus, Phlegon, Hermes, Patrobas, Hermas and the other brothers and sisters with them.

15Greet Philologus, Julia, Nereus and his sister, and Olympas and all the Lord’s people who are with them.

16Greet one another with a holy kiss.

All the churches of Christ send greetings.

17I urge you, brothers and sisters, to watch out for those who cause divisions and put obstacles in your way that are contrary to the teaching you have learned. Keep away from them. 18For such people are not serving our Lord Christ, but their own appetites. By smooth talk and flattery they deceive the minds of naive people. 19Everyone has heard about your obedience, so I rejoice because of you; but I want you to be wise about what is good, and innocent about what is evil.

20The God of peace will soon crush Satan under your feet.

The grace of our Lord Jesus be with you.

21Timothy, my co-worker, sends his greetings to you, as do Lucius, Jason and Sosipater, my fellow Jews.

22I, Tertius, who wrote down this letter, greet you in the Lord.

23Gaius, whose hospitality I and the whole church here enjoy, sends you his greetings.

Erastus, who is the city’s director of public works, and our brother Quartus send you their greetings. 2416:24 Some manuscripts include here May the grace of our Lord Jesus Christ be with all of you. Amen.

25Now to him who is able to establish you in accordance with my gospel, the message I proclaim about Jesus Christ, in keeping with the revelation of the mystery hidden for long ages past, 26but now revealed and made known through the prophetic writings by the command of the eternal God, so that all the Gentiles might come to the obedience that comes from16:26 Or that is faith – 27to the only wise God be glory for ever through Jesus Christ! Amen.