ራእይ 7 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ራእይ 7:1-17

መቶ አርባ አራት ሺሑ መታተማቸው

1ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱ የምድር ማእዘኖች ቆመው አየሁ፤ እነርሱም ነፋስ በምድር ወይም በባሕር፣ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሶች ያዙ። 2ከዚያም የሕያው አምላክ ማኅተም ያለው ሌላ መልአክ ከምሥራቅ ሲመጣ አየሁ፤ እርሱም ምድርንና ባሕርን ለመጕዳት ሥልጣን የተሰጣቸውን አራቱን መላእክት በታላቅ ድምፅ እንዲህ አላቸው፤ 3“በአምላካችን አገልጋዮች ግንባር ላይ ማኅተም እስከምናደርግባቸው ድረስ ምድርን ወይም ባሕርን፣ ወይም ዛፎችን አትጕዱ።” 4የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ እነርሱም ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ መቶ አርባ አራት ሺሕ ነበሩ፤

5ከይሁዳ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከሮቤል ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከጋድ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

6ከአሴር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከንፍታሌም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከምናሴ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

7ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

8ከዛብሎን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከዮሴፍ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ፣

ከብንያም ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺሕ ታተሙ።

ነጭ ልብስ የለበሱ እጅግ ብዙ ሕዝብ

9ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር። 10በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ጮኹ፤

“ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው፣

የአምላካችንና የበጉ ነው።”

11መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ፣ በአራቱም ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑ ፊት በግንባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ 12እንዲህም ይሉ ነበር፤

“አሜን፤

ውዳሴና ክብር፣

ጥበብ፣ ምስጋናና፣ ሞገስ፣

ኀይልና ብርታትም፣

ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤

አሜን።”

13ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱት እነማን ናቸው? ከወዴትስ መጡ?” አለኝ።

14እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ” አልሁት።

እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም ዐጥበው አንጽተዋል። 15ስለዚህ፣

“በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ሆነው፣

ቀንና ሌሊት በመቅደሱ ያገለግሉታል፤

በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን

በላያቸው ይዘረጋል፤

16ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም፤

ከዚህም በኋላ አይጠሙም፤

ፀሓይ አይመታቸውም፤

ሐሩሩም ሁሉ አያቃጥላቸውም፤

17ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው

በግ እረኛቸው ይሆናል፤

ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭም ይመራቸዋል፤

እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

启示录 7:1-17

为上帝的仆人盖印

1这些事情之后,我看见四位天使分别站在地的四个角落控制着四面的风,使风不再吹向地面、海洋和树木。 2我又看见一位天使从东方日出之地上来,手里拿着永活上帝的印。他对那领受权柄能伤害地和海的四位天使大声说: 3“我们还没在上帝的奴仆额上盖印之前,你们不可伤害地、海和树木。” 4我听见以色列各支派中盖了印的共有十四万四千人: 5犹大支派有一万二千,吕便支派有一万二千,迦得支派有一万二千, 6亚设支派有一万二千,拿弗他利支派有一万二千,玛拿西支派有一万二千, 7西缅支派有一万二千,利未支派有一万二千,以萨迦支派有一万二千, 8西布伦支派有一万二千,约瑟支派有一万二千,便雅悯支派有一万二千。

劫后余生的上帝子民

9后来我又看见一大群人,多得不可胜数。他们来自各国家、各部落、各民族、各语言族群,身穿白袍,手拿棕树枝,站在宝座和羔羊面前, 10大声呼喊说:“救恩来自我们坐在宝座上的上帝,也来自羔羊!” 11众天使都站在宝座、众长老和四个活物的周围,在宝座前俯伏敬拜上帝,说: 12“阿们!愿颂赞、荣耀、智慧、感谢、尊贵、权柄、能力都归给我们的上帝,直到永永远远。阿们!”

13长老中有一位问我:“这些身穿白袍的人是谁?他们从哪里来?”

14我回答说:“先生,你知道答案。”

他便说:“这些都是经过大灾难的人,他们用羔羊的血将衣裳洗得纯净洁白。 15因此,他们在宝座前,在圣殿中不分昼夜地事奉上帝。坐在宝座上的那位要庇护他们。 16他们不会再受饥饿和干渴的折磨,也不会再受太阳和酷热的煎熬, 17因为在宝座中央的羔羊要做他们的牧人,引导他们到生命之泉那里,上帝要擦干他们所有的眼泪。”