ራእይ 5 – NASV & HHH

New Amharic Standard Version

ራእይ 5:1-14

ጥቅልል መጽሐፉና በጉ

1በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው በውስጥና በውጭ በኩል የተጻፈበት፣ በሰባት ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሐፍ በቀኝ እጁ ይዞ አየሁ። 2አንድ ብርቱ መልአክ በታላቅ ድምፅ፣ “ማኅተሞቹን ለመፍታትና መጽሐፉን ለመክፈት የተገባው ማን ነው?” ብሎ ሲያውጅ አየሁ። 3ነገር ግን በሰማይም ሆነ በምድር፣ ከምድርም በታች መጽሐፉን ለመክፈት ወይም ገልጦ ለመመልከት የሚችል ማንም አልነበረም። 4እኔም መጽሐፉን ለመክፈት ወይም ገልጦ ለመመልከት የተገባው ማንም ባለመኖሩ እጅግ አለቀስሁ። 5ከዚያም ከሽማግሌዎቹ አንዱ፣ “አታልቅስ፤ እነሆ፤ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፣ የዳዊት ሥር ድል ነሥቷል፤ እርሱ መጽሐፉን ሊከፍትና ሰባቱንም ማኅተሞች ሊፈታ ይችላል” አለኝ።

6ከዚያም በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ በሽማግሌዎቹም መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩት ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት5፥6 ወይም ሰባት ዕጥፍ መንፈስ ናቸው። 7እርሱም መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ መጽሐፉን ወሰደ። 8መጽሐፉን በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችም በበጉ ፊት በግንባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም የቅዱሳን ጸሎት የሆኑትን በገናና ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሙዳይ ይዘው ነበር። 9እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤

“መጽሐፉን ልትወስድ፣

ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤

ምክንያቱም ታርደሃል፤

በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣

ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።

10ለአምላካችንም መንግሥትና ካህናት አድርገሃቸዋል፤

እነርሱም በምድር ላይ ይነግሣሉ።”

11ከዚያም ተመለከትሁ፤ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም ሺሕ ጊዜ ሺሕና እልፍ ጊዜ እልፍ ነበረ። እነርሱም በዙፋኑና በሕያዋን ፍጡራኑ፣ በሽማግሌዎቹም ዙሪያ ከብበው ነበር፤ 12በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ዘመሩ፤

“የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፣

ጥበብና ብርታት፣

ክብርና ሞገስ፣ ምስጋናም፣

ሊቀበል ይገባዋል።”

13ከዚያም በሰማይና በምድር፣ ከምድር በታችና በባሕር፣ በእነርሱ ውስጥ ያሉ ፍጡራንም ሁሉ እንዲህ ብለው ሲዘምሩ ሰማሁ፤

“በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉ፣

ምስጋናና ሞገስ፣ ክብርና ኀይል፣

ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን!”

14አራቱ ሕያዋን ፍጡራንም፣ “አሜን!” አሉ፤ ሽማግሌዎቹም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።

Habrit Hakhadasha/Haderekh

התגלות 5:1-14

1ראיתי לימין היושב על הכסא מגילה כתובה בפנים ובחוץ וחתומה בשבעה חותמות. 2מלאך גיבור הופיע וקרא בקול גדול: ”מי ראוי לשבור את החותמות ולפתוח את המגילה?“ 3ולא נמצא איש בשמים, בארץ או מבין המתים אשר היה מסוגל לפתוח את המגילה או להביט בכתוב.

4פרצתי בבכי מר, כי איש לא נמצא ראוי לפתוח את המגילה ולקרוא בה. 5אך אחד מעשרים־וארבעה הזקנים אמר אלי: ”אל תבכה. ראה, האריה משבט יהודה ושורש דויד ניצח, והוכיח את עצמו ראוי לשבור את החותמות ולפתוח את המגילה.“

6הבטתי במרכז כסא־המלכות, שמוקף בארבע החיות ובעשרים־וארבעה הזקנים, וראיתי שה שעליו פצעים וחבורות אשר גרמו פעם למותו. לשה היו שבע קרניים ושבע עיניים, שהן שבע רוחות האלוהים שנשלחות אל כל קצווי העולם. 7השה בא ולקח את המגילה מימינו של היושב על כיסא המלכות. 8בלקחו את המגילה השתחוו לפניו ארבע החיות ועשרים־וארבעה הזקנים. כל אחד מהזקנים אחז כינור וקערת זהב מלאה קטורת, אשר היא תפילת בני־האלוהים הקדושים. 9הם שרו שיר חדש, ואלו מילותיו:

”ראוי אתה לקחת את המגילה

ולפתוח את חותמיה,

כי אתה נשחטת,

ובדמך קנית לאלוהים את בניו

מכל עם, גזע ולשון.

10ממלכת כוהנים לאלוהינו עשית אותם,

והם ימלכו על הארץ.“

11לאחר מכן שמעתי בחיזיון קול מלאכים רבים סביב כסא המלכות, ארבע החיות והזקנים. 12הם שרו שירה אדירה:

”ראוי השה הטבוח

לקבל עוז,

עושר וחכמה,

גבורה והדר,

כבוד וברכה.“

13וכל בריה בשמים, בארץ, מתחת לארץ ובים, שמעתי קוראים:

”ליושב על הכסא ולשה

הברכה וההדר והעוז,

לעולם ועד!“

14ארבע החיות אמרו: ”אמן!“ ועשרים וארבעה הזקנים נפלו על פניהם והשתחוו לו.