ራእይ 16 – NASV & CRO

New Amharic Standard Version

ራእይ 16:1-21

ሰባቱ የእግዚአብሔር ቍጣ ጽዋዎች

1ከዚያም ለሰባቱ መላእክት፣ “ሂዱ፤ ሰባቱን የእግዚአብሔር ቍጣ ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከቤተ መቅደሱ ሰማሁ።

2የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውን ምልክት በተቀበሉትና ለምስሉም በሰገዱት ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚያሠቃይ ቍስል ወጣባቸው።

3ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን በባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩም እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ በባሕሩ ውስጥ የሚኖሩ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ ሞቱ።

4ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን በወንዞችና በውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ። 5ከዚያም በውሆች ላይ ሥልጣን ያለው መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤

“ያለህና የነበርህ ቅዱሱ ሆይ፤

እንዲህ ስለ ፈረድህ፣

አንተ ጻድቅ ነህ፤

6የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣

አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።”

7እንዲሁም ከመሠዊያው እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፤

“አዎን፤ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤

ፍርድህ እውነትና ጽድቅ ነው።”

8አራተኛውም መልአክ ጽዋውን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ፀሓይም ሰዎችን በእሳት እንድታቃጥል ኀይል ተሰጣት። 9እነርሱም በታላቅ ሐሩር ተቃጠሉ፤ በእነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ እንጂ ንስሓ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።

10አምስተኛውም መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ፤ ሰዎችም ከሥቃያቸው የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር፤ 11ደግሞም ከሥቃያቸውና ከቍስላቸው የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ እንጂ ከሥራቸው ንስሓ አልገቡም።

12ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸው የወንዙ ውሃ ደረቀ። 13ከዚያም ከዘንዶው አፍ፣ ከአውሬው አፍና ከሐሰተኛው ነቢይ አፍ እንቍራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ። 14እነርሱም ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ታላቅ ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲሰበስቧቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይሄዳሉ።

15“እነሆ፤ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ዕራቍቱን እንዳይሆን ኀፍረቱም እንዳይታይ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”

16እነርሱም ነገሥታቱን በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ ሰበሰቧቸው።

17ሰባተኛውም መልአክ ጽዋውን በአየር ላይ አፈሰሰ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ካለው ዙፋንም “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ወጣ። 18ከዚያም መብረቅ፣ ድምፅ፣ ነጐድጓድና ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ላይ ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ የምድር መናወጥ ታይቶ አይታወቅም፤ ነውጡም እጅግ ታላቅ ነበር። 19ታላቂቱ ከተማ ከሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ፈራረሱ፤ እግዚአብሔርም ታላቂቱን ባቢሎን አስታወሰ፤ በብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የተሞላውን ጽዋ ሰጣት። 20ደሴቶች ሁሉ ሸሹ፤ ተራሮችም ሊገኙ አልቻሉም። 21በሚዛን ሲመዘን እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም16፥21 ግሪኩ አንድ ታላንት ይለዋል። የሚሆን ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበር፣ ሰዎቹ ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ።

Knijga O Kristu

Otkrivenje 16:1-21

1Začujem zatim kako jak glas iz hrama dovikuje sedmorici anđela: “Idite i izlijte sedam čaša Božjega gnjeva na zemlju!”

2Prvi anđeo ode i izlije posudu na zemlju. Strašni i bolni čirovi pojave se na ljudima koji nose žig Zvijeri i koji se klanjaju njezinu kipu.

3Drugi anđeo izlije posudu na more. Ono postane poput mrtvačeve krvi te svako živo biće u njemu ugine.

4Treći anđeo izlije posudu na rijeke i izvore. Oni se pretvore u krv. 5Začujem anđela koji ima vlast nad vodom kako kaže:

“Pravedan si, Ti koji jesi i koji si bio,

Sveti, što si tako dosudio.

6Oni su prolili krv tvojih svetih i tvojih proroka.

Zato ih sada krvlju napajaš.

To su i zaslužili.”

7Začujem zatim žrtvenik kako govori:

“Da, Svemogući Gospodine Bože!

Tvoje su presude pravedne i istinite!”

8Zatim četvrti anđeo izlije posudu na sunce te ono počne žeći ljude ognjem. 9Silna je žega palila ljude pa su psovali ime Boga koji ima vlast nad tim zlima. Nisu se pokajali i dali mu slavu.

10Peti anđeo izlije posudu na Zvijerino prijestolje. Njezinim kraljevstvom nato zavlada tmina. Ljudi su od muke grizli jezik 11i psovali nebeskoga Boga zbog svojih boli i čirova. Ali nisu se pokajali i obratili od svojih zlih djela.

12Šesti anđeo izlije posudu na veliku rijeku Eufrat te ona presuši da onuda mogu proći kraljevi sa sunčeva istoka. 13Ugledam zatim kako tri žabe iskaču iz usta Zmaja, Zvijeri i lažnoga proroka. 14Ti nečisti duhovi, koji čine čudesa, okupe vladare svega svijeta na rat protiv Boga, koji će se zbiti na veliki Dan Svemogućega Boga.

15“Pazite: dolazim kao tat! Blago onima koji bdiju i koji čuvaju svoje haljine da ne idu goli i da im se ne vidi sramota.”

16Oni okupe sve vojske svijeta na mjestu koje se hebrejski zove Harmagedon.

17Sedmi anđeo izlije posudu u zrak. Iz hrama, s prijestolja, jaki glas vikne: “Svršeno je!” 18Nato udare munje, grmljavina i gromovi te nastane jak potres. Otkako je ljudi, nije bilo tako silna potresa. 19Veliki grad Babilon prasne na tri dijela, gradovi naroda po svijetu sruše se. Sjetio se Bog velikome Babilonu zbog njegovih grijeha dati da pije vino iz čaše strašnoga Božjega gnjeva. 20Svi otoci pobjegnu, sve gore iščeznu. 21Na ljude s neba zapljušti strašna tuča. Padali su komadi teški po trideset pet kilograma.16:21 U grčkome: tuča teška jedan talenat. Ljudi su psovali Boga zbog tuče jer je nanosila strašno zlo.