ሩት 3 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሩት 3:1-18

ቦዔዝና ሩት በእህል ዐውድማው ላይ

1ከዚህ በኋላ ዐማቷ ኑኃሚን ሩትን እንዲህ አለቻት፤ “ልጄ ሆይ፤ የሚመችሽን ቤት3፥1 ወይም የምታርፊበትን እንድፈልግልሽ አይገባኝምን? 2ከሴቶች ሠራተኞቹ ጋር አብረሽ የነበርሽበት ቦዔዝ፣ ዘመዳችን አይደለምን? ዛሬ ማታ በዐውድማው ላይ ገብስ ያበራያል፤ 3ተጣጠቢ፤ ሽቶ ተቀቢ፤ እንዲሁም የክት ልብስሽን ልበሺ፤ ከዚያም ወደ ዐውድማው ውረጂ፤ ይሁን እንጂ በልቶና ጠጥቶ እስኪያበቃ ድረስ፣ እዚያ መሆንሽን እንዳያውቅ ይሁን። 4በተኛም ጊዜ፣ የሚተኛበትን ቦታ ልብ ብለሽ እዪና ሄደሽ እግሩን ገልጠሽ ተኚ፤ ከዚያም የምታደርጊውን ራሱ ይነግርሻል።”

5ሩትም፣ “ያልሽውን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት። 6ስለዚህ ተነሥታ ወደ ዐውድማው ወረደች፤ ዐማቷ አድርጊ ያለቻትንም ሁሉ አደረገች።

7ቦዔዝ በልቶ ጠጥቶ ከጨረሰና ደስም ከተሰኘ በኋላ፣ ራቅ ካለው የእህል ክምር አጠገብ ለመተኛት ሄደ። ሩት በቀስታ ከአጠገቡ ደረሰች፤ እግሩንም ገልጣ ተኛች። 8እኩለ ሌሊት ላይ ሰውየውን አንዳች ነገር አስደነገጠው፤ ገልበጥ ሲልም አንዲት ሴት እግርጌው ተኝታ አገኘ።

9እርሱም፣ “አንቺ ማነሽ?” ሲል ጠየቀ። እርሷም፣ “እኔ አገልጋይህ ሩት ነኝ፤ መቤዠት የሚገባህ ቅርብ የሥጋ ዘመድ አንተ ነህና ልብስህን ጣል አድርግብኝ” አለችው።

10እርሱም መልሶ እንዲህ አላት፤ “ልጄ ሆይ፤ እግዚአብሔር ይባርክሽ፤ ከዚህ በፊት ካደረግሽው ይልቅ ያሁኑ በጎነትሽ ይበልጣል፤ ባለጠጋም ሆነ ድኻ፣ ወጣት ወንድ ፈልገሽ አልሄድሽምና። 11አሁንም ልጄ ሆይ፤ አትፍሪ፤ የምትጠይቂውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፤ አንቺ ምግባረ መልካም ሴት መሆንሽንም የአገሬ ሰው ሁሉ ያውቀዋል። 12ምንም እንኳ እኔ ቅርብ የሥጋ ዘመድ መሆኔ የተረጋገጠ ቢሆንም፣ ከእኔ ይልቅ መቤዠት የሚገባው ቅርብ የሥጋ ዘመድ አለ። 13ከዚህ ዕደሪ፤ ሲነጋም ሰውየው ሊቤዥሽ ከፈለገ፣ መልካም ነው፤ ይቤዥሽ፤ የማይፈልግ ከሆነ ግን በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ፤ እኔ እቤዥሻለሁ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ተኚ።”

14ስለዚህም ሩት እስኪነጋ ድረስ እግርጌው ተኛች፤ ዳሩ ግን ማንም ሰው ተለይቶ ሊታወቅ በማይችልበት ሰዓት ቀደም ብላ ተነሣች፤ እርሱም፣ “ሴት ወደዚህ ዐውድማ መምጣቷ እንዳይታወቅ” አላት።

15እንዲሁም፣ “በላይሽ የደረብሽውን ልብስ አቅርቢልኝ፤ ዘርግተሽም ያዢው” አላት፤ ዘርግታ እንደ ያዘችም ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰፍሮ አሸከማት፤ ከዚያም ወደ ከተማ ተመለሰች3፥15 አብዛኞቹ የዕብራይስጥ ቅጆች፣ ቩልጌትና ሱርስት ከዚህ ጋር ይስማማሉ፤ አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ይነገረኝና ይላሉ።

16ሩት ወደ ዐማቷ እንደ ተመለሰች፣ ኑኃሚን፣ “ልጄ ሆይ፤ የሄድሽበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” ብላ ጠየቀቻት።

ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት፤ 17ቀጥላም፣ “ ‘ወደ ዐማትሽ ባዶ እጅሽን አትመለሺ’ በማለት ይህን ስድስት መስፈሪያ ገብስ ሰጠኝ” አለቻት።

18ኑኃሚንም፣ “ልጄ ሆይ፤ የሚሆነውን ነገር እስክታውቂ ድረስ ታገሺ፤ ጕዳዩ ዛሬውኑ እልባት ካላገኘ ሰውየው አያርፍም” አለቻት።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

路得記 3:1-18

路得麥場見波阿斯

1一天,路得的婆婆拿俄米對她說:「我的女兒啊,我實在應該為你找個好歸宿,使你生活幸福。 2波阿斯不是我們的親戚嗎?而且你又常與他的女工在一起。今天晚上他會在麥場簸大麥。 3你要梳洗打扮、抹上香膏、換件衣服,然後去麥場,但不要讓他認出你是誰。等他吃飽喝足, 4躺下睡覺的時候,你看準他躺臥的地方,去掀開蓋在他腳上的被,躺在那裡,到時他必定會告訴你該怎樣做。」 5路得說:「好,我一定照你的吩咐去做。」

6於是,路得就到麥場去,照她婆婆吩咐的去做。 7波阿斯吃過晚飯,心裡舒暢,便躺在麥堆旁邊睡著了。路得悄悄過去掀起蓋在他腳上的被,躺在他腳旁。 8到了半夜,波阿斯忽然驚醒,翻過身來,發現一個女子躺在他的腳旁, 9便問道:「你是誰?」她答道:「我是你的婢女路得,請用你的衣襟遮蓋我,因為你是我的近親。」 10波阿斯說:「姑娘,願耶和華賜福給你,因為你一直對婆家情深義重,現在更是如此。你本來可以找一個或窮或富的年輕丈夫,然而你卻沒有這樣做。 11姑娘,不要怕,你所說的一切,我都會去為你安排,城裡所有的人都知道你是個賢德的女子。 12不錯,我是你的近親,可是有一個人比我更近。 13你今晚就留在這裡,明天早上,如果他答應盡親屬的義務,就由他照顧你;如果他不肯,我憑永活的耶和華起誓,我會盡我的本分。現在你只管安心睡覺吧。」

14路得就躺在波阿斯的腳旁。天未亮,還看不清人的時候,路得就起來了。因為波阿斯曾對她說:「不可讓別人知道有女人來過這裡。」 15離開的時候,波阿斯對她說:「把你的外衣拿來鋪開。」路得就照做了。他用路得的外衣包了六簸箕大麥,幫她扛在肩上,她便回城了。 16回到家中,婆婆問她:「女兒啊,怎麼樣了?」路得便將事情的經過都告訴了婆婆。 17她又說:「那個人給了我六簸箕大麥,對我說,『不要空手回去見你婆婆。』」 18拿俄米說:「女兒啊!你只管安靜等候,看這事怎樣發展,因為那人今天不把事情辦妥,是絕不會休息的。」