ማቴዎስ 4 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 4:1-25

የኢየሱስ መፈተን

4፥1-11 ተጓ ምብ – ማር 1፥1213ሉቃ 4፥1-13

1ከዚህ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። 2አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። 3ፈታኙም ወደ ኢየሱስ ቀርቦ፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው።

4ኢየሱስም፣ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት።

5ቀጥሎም ዲያብሎስ ኢየሱስን ወደ ቅድስት ከተማ በመውሰድ ከቤተ መቅደሱም ዐናት ላይ አውጥቶ፣ 6“የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ራስህን ወደ መሬት ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤

“ ‘እግርህ በድንጋይ እንዳይሰናከል፣

በእጃቸው ያነሡህ ዘንድ፣

መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዝልሃል።’ ”

7ኢየሱስም፣ “እንደዚሁም በመጻሕፍት፣ ‘እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሎ ተጽፏል” በማለት መለሰለት።

8እንደ ገናም ዲያብሎስ ኢየሱስን እጅግ ከፍ ወዳለ ተራራ አወጣው፤ የዓለምንም መንግሥታት ከነክብራቸው አሳየውና፣ 9“ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው።

10ኢየሱስም፣ “አንተ ሰይጣን ከፊቴ ራቅ! ‘ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፏልና” አለው።

11ከዚያም ዲያብሎስ ትቶት ሄደ፤ መላእክትም መጥተው አገለገሉት።

ኢየሱስ ስብከት መጀመሩ

12ኢየሱስ የዮሐንስን መታሰር በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ተመለሰ። 13የናዝሬትንም ከተማ ትቶ፣ በዛብሎንና በንፍታሌም አካባቢ በባሕሩ አጠገብ በምትገኘው በቅፍርናሆም ከተማ መኖር ጀመረ። 14በዚህም በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ተፈጸመ፤

15“የዛብሎን ምድር፣ የንፍታሌም ምድር፣

ከዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ አጠገብ፣

ያለው የአሕዛብ ገሊላ፣

16በጨለማ የሚኖር ሕዝብ፣

ታላቅ ብርሃን አየ፤

በሞት ጥላ ምድር ላለው፣

ብርሃን ወጣለት።”

17ከዚያ ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ፣ “ንስሓ ግቡ፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና” እያለ መስበክ ጀመረ።

የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት መጠራት

4፥18-22 ተጓ ምብ – ማር 1፥16-20ሉቃ 5፥2-11ዮሐ 1፥35-42

18ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲያልፍ፣ ሁለት ወንድማማቾች ማለትም፣ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንንና ወንድሙን እንድርያስን አያቸው። ዓሣ አጥማጆች ነበሩና መረባቸውን ወደ ባሕሩ ይጥሉ ነበር። 19ኢየሱስም፣ “ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን አጥማጆች አደርጋችኋለሁ” አላቸው። 20ወዲያው መረባቸውን ትተው ተከተሉት።

21ዐለፍ እንዳለም፣ ሌሎች ሁለት ወንድማማቾች፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ። ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረባቸውን ያበጁ ነበር። ኢየሱስም ጠራቸው፤ 22ወዲያውኑ ጀልባቸውንም ሆነ አባታቸውን ትተው ተከተሉት።

የበሽተኞች መፈወስ

23ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር። 24ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም። 25ከዚህም የተነሣ ከገሊላ፣ ከ “ዐሥሩ ከተሞች”፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ማዶ የመጡ ብዙ ሰዎች ተከተሉት።

New International Reader’s Version

Matthew 4:1-25

Jesus Is Tempted in the Desert

1The Holy Spirit led Jesus into the desert. There the devil tempted him. 2After 40 days and 40 nights of going without eating, Jesus was hungry. 3The tempter came to him. He said, “If you are the Son of God, tell these stones to become bread.”

4Jesus answered, “It is written, ‘Man must not live only on bread. He must also live on every word that comes from the mouth of God.’ ” (Deuteronomy 8:3)

5Then the devil took Jesus to the holy city. He had him stand on the highest point of the temple. 6“If you are the Son of God,” he said, “throw yourself down. It is written,

“ ‘The Lord will command his angels to take good care of you.

They will lift you up in their hands.

Then you won’t trip over a stone.’ ” (Psalm 91:11,12)

7Jesus answered him, “It is also written, ‘Do not test the Lord your God.’ ” (Deuteronomy 6:16)

8Finally, the devil took Jesus to a very high mountain. He showed him all the kingdoms of the world and their glory. 9“If you bow down and worship me,” he said, “I will give you all this.”

10Jesus said to him, “Get away from me, Satan! It is written, ‘Worship the Lord your God. He is the only one you should serve.’ ” (Deuteronomy 6:13)

11Then the devil left Jesus. Angels came and took care of him.

Jesus Begins to Preach

12John had been put in prison. When Jesus heard about this, he returned to Galilee. 13Jesus left Nazareth and went to live in the city of Capernaum. It was by the lake in the area of Zebulun and Naphtali. 14In that way, what the prophet Isaiah had said came true. He had said,

15“Land of Zebulun! Land of Naphtali!

Galilee, where Gentiles live!

Land along the Mediterranean Sea! Territory east of the Jordan River!

16The people who are now living in darkness

have seen a great light.

They are now living in a very dark land.

But a light has shined on them.” (Isaiah 9:1,2)

17From that time on Jesus began to preach. “Turn away from your sins!” he said. “The kingdom of heaven has come near.”

Jesus Chooses His First Disciples

18One day Jesus was walking beside the Sea of Galilee. There he saw two brothers, Simon Peter and his brother Andrew. They were throwing a net into the lake, because they were fishermen. 19“Come and follow me,” Jesus said. “I will send you out to fish for people.” 20At once they left their nets and followed him.

21Going on from there, he saw two other brothers. They were James, son of Zebedee, and his brother John. They were in a boat with their father Zebedee. As they were preparing their nets, Jesus called out to them. 22Right away they left the boat and their father and followed Jesus.

Jesus Heals Sick People

23Jesus went all over Galilee. There he taught in the synagogues. He preached the good news of God’s kingdom. He healed every illness and sickness the people had. 24News about him spread all over Syria. People brought to him all who were ill with different kinds of sicknesses. Some were suffering great pain. Others were controlled by demons. Some were shaking wildly. Others couldn’t move at all. And Jesus healed all of them. 25Large crowds followed him. People came from Galilee, from the area known as the Ten Cities, and from Jerusalem and Judea. Others came from the area across the Jordan River.