ማቴዎስ 27 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 27:1-66

ይሁዳ ራሱን ሰቀለ

1ጧት በማለዳ ላይ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስ ስለሚገደልበት ሁኔታ ተመካከሩ፤ 2ካሰሩትም በኋላ ወስደው ለገዥው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።

3አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፤ የወሰደውን ሠላሳ ጥሬ ብር ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ ሽማግሌዎች መልሶ በመስጠት፣ 4“ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ” አለ።

እነርሱም፣ “ታዲያ እኛ ምን አገባን፤ የራስህ ጕዳይ ነው!” አሉት።

5ስለዚህ ይሁዳ ብሩን በቤተ መቅደስ ውስጥ ወርውሮ ወጣ፤ ሄዶም ራሱን ሰቅሎ ሞተ።

6የካህናት አለቆች ብሩን አንሥተው፣ “የደም ዋጋ ስለሆነ ወደ መባ ልንጨምረው አይፈቀድም” አሉ፤ 7ተመካክረውም ለእንግዶች የመቃብር ስፍራ እንዲሆን በገንዘቡ የሸክላ ሠሪውን ቦታ ገዙበት። 8ስለዚህም ያ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ “የደም መሬት” ተብሎ ይጠራል። 9በዚህም በነቢዩ ኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፤ “ለእርሱ ዋጋ ይሆን ዘንድ የእስራኤል ልጆች የገመቱትን ሠላሳ ጥሬ ብር ተቀበሉ፤ 10እግዚአብሔርም ባዘዘኝ መሠረት ለሸክላ ሠሪው ቦታ ከፈሉ።”

ኢየሱስ በጲላጦስ ፊት

27፥11-26 ተጓ ምብ – ማር 15፥2-15ሉቃ 23፥2318-25ዮሐ 18፥29–19፥16

11በዚህ ጊዜ ኢየሱስ አገረ ገዥው ፊት ቀረበ፤ አገረ ገዥውም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው።

ኢየሱስም፣ “አንተው እንዳልኸው ነው” ሲል መለሰለት።

12የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ሲከስሱት ግን ምንም መልስ አልሰጠም። 13በዚህ ጊዜ ጲላጦስ፣ “ስንት ነገር አቅርበው እንደሚከስሱህ አትሰማምን?” አለው። 14እርሱ ግን አገረ ገዥው እስኪገረም ድረስ ለቀረበበት ክስ አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰም።

15አገረ ገዥው ሕዝቡ በበዓሉ እንዲፈታላቸው የሚጠይቁትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው። 16በዚያን ጊዜ በዐመፅ የታወቀ በርባን የሚባል እስረኛ ነበር። 17ሕዝቡ እንደ ተሰበሰቡ ጲላጦስ፣ “ከበርባንና ክርስቶስ ከሚባለው ከኢየሱስ፣ ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው፤ 18ጲላጦስም በቅናት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።

19በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፣ “በእርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ስለ ተሠቃየሁ፣ በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም ነገር እንዳታደርግ” የሚል መልእክት ላከችበት።

20ነገር ግን የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች በርባን እንዲፈታላቸው ኢየሱስ ግን እንዲገደል ይለምኑ ዘንድ ሕዝቡን ያግባቡ ነበር።

21አገረ ገዥውም፣ “ከሁለቱ ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቀ።

እነርሱም፤ “በርባንን!” በማለት መለሱ።

22ጲላጦስም፣ “ታዲያ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው።

ሁሉም፣ “ይሰቀል!” አሉ።

23ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን ክፉ ነገር አድርጓል?” በማለት ጠየቃቸው።

እነርሱ ግን አብዝተው እየጮኹ፣ “ይሰቀል!” አሉ።

24ጲላጦስ ሁኔታው ሽብር ከማስነሣት በስተቀር ምንም ፋይዳ የሌለው መሆኑን ተመልክቶ፣ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ኀላፊነቱ የራሳችሁ ነው” በማለት ውሃ አስመጥቶ በሕዝቡ ፊት እጆቹን ታጠበ።

25ሕዝቡም በሙሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን!” ብለው መለሱ።

26በዚህ ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ካስገረፈው በኋላ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።

ኢየሱስ በሮማውያን ወታደሮች እጅ

27፥27-31 ተጓ ምብ – ማር 15፥16-20

27ከዚያም የአገረ ገዥው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዥው ግቢ ወሰዱት፤ ሰራዊቱንም ሁሉ በዙሪያው አሰባሰቡ። 28ልብሱን ገፍፈው ቀይ ልብስ አጠለቁለት፤ 29እሾኽ ጐንጕነው አክሊል በመሥራት ራሱ ላይ ደፉበት፤ የሸንበቆ በትር በቀኝ እጁ በማስያዝ በፊቱ ተንበርክከው፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” በማለት አሾፉበት፤ 30ተፉበትም፤ የሸንበቆ በትሩን ከእጁ ወስደው ራሱ ላይ በሸንበቆው ደግመው ደጋግመው መቱት፤ 31ካሾፉበት በኋላም ቀዩን ልብስ ገፍፈው የራሱን መጐናጸፊያ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ይዘውት ሄዱ።

የኢየሱስ መሰቀል

27፥33-44 ተጓ ምብ – ማር 15፥22-32ሉቃ 23፥33-43ዮሐ 19፥17-24

32ይዘውትም ሲሄዱ ስምዖን ተብሎ የሚጠራ የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉንም እንዲሸከም አስገደዱት። 33ትርጕሙ፣ “የራስ ቅል ስፍራ” ከሆነው ጎልጎታ ከተባለው ቦታ ሲደርሱ፣ 34ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈቀደም። 35ከሰቀሉትም በኋላ ዕጣ ጥለው ልብሱን ተካፈሉ፤27፥35 ጥቂት የጥንት ቅጆች “በነቢዩ ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ የተባለው ይፈጸም ዘንድ” የሚል አላቸው። 36በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር። ከራስጌውም፣ 37“ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የክስ ጽሑፍ አኖሩ። 38ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ፣ አንዱ በግራው አብረውት ተሰቅለው ነበር። 39መንገድ ዐላፊዎችም በኀይል እየተሳደቡና ራሳቸውን እየነቀነቁ፣ 40“ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን ውስጥ የምትሠራው፤ እስቲ ራስህን አድን! የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ በል ከመስቀል ውረድ!” ይሉት ነበር።

41የካህናት አለቆችም ከኦሪት ሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎች ጋር ሆነው እያሾፉበት እንዲህ ይሉ ነበር፤ 42“ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አይችልም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን። 43በእግዚአብሔር ታምኗል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ይል ስለ ነበር እስቲ ከወደደው አሁን ያድነው!” 44ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም እንደዚሁ የስድብ ናዳ ያወርዱበት ነበር።

የኢየሱስ መሞት

27፥45-56 ተጓ ምብ – ማር 15፥33-41ሉቃ 23፥44-49

45ከቀኑ ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ። 46በዘጠኝ ሰዓት ገደማ፣ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ፤ ትርጕሙም “አምላኬ፤ አምላኬ፤ ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።

47በዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ጩኸቱን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን እየተጣራ ነው!” አሉ።

48ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጦ ሰፍነግ በመውሰድ የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ውስጥ ነከረው፤ ሰፍነጉንም በሸንበቆ ዘንግ ጫፍ ላይ በማድረግ እንዲጠጣው ለኢየሱስ አቀረበለት። 49የቀሩት ግን፣ “ተዉት፤ እስቲ ኤልያስ መጥቶ ሲያድነው እናያለን!” አሉ።

50ኢየሱስ እንደ ገና ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ፤ መንፈሱንም አሳልፎ ሰጠ።

51በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ፤ ምድር ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጣጠቁ፤ 52መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩትም ብዙዎች ቅዱሳን ተነሡ፤ 53ከመቃብርም በመውጣት ከኢየሱስ ትንሣኤ በኋላ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።

54የመቶ አለቃውና አብረውት ኢየሱስን ይጠብቁት የነበሩት የመሬት መናወጡንና የሆነውን ነገር ሁሉ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው፤ ይህስ፣ “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር!” አሉ። 55ከገሊላ የመጡና ኢየሱስን በሚያስፈልገው ነገር ለማገልገል የተከተሉት ብዙ ሴቶች ሁኔታውን ከርቀት እየተመለከቱ በአካባቢው ነበሩ። 56ከእነርሱም መካከል ማርያም መግደላዊት፣ ማርያም የያዕቆብና የዮሴፍ እናት እንዲሁም የዘብዴዎስ ልጆች እናት ነበሩ።

የኢየሱስ መቀበር

27፥57-61 ተጓ ምብ – ማር 15፥42-47ሉቃ 23፥50-56ዮሐ 19፥38-42

57ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚባል ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱም የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበረ። 58ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስን በድን ለመነው፤ ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ። 59ዮሴፍም በድኑን ወስዶ በንጹሕ የበፍታ ጨርቅ ከፈነው፤ 60ለራሱ ከዐለት አስፈልፍሎ ባዘጋጀው መቃብር ውስጥ አኖረው፤ ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባልሎ የመቃብሩን በር ዘግቶ ሄደ። 61በዚህ ጊዜ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ከመቃብሩ ትይዩ ተቀምጠው ነበር።

የመቃብሩ ጥበቃ

62በማግስቱም፣ ከሰንበት ዝግጅት በኋላ ባለው ቀን፣ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ጲላጦስ ፊት ቀርበው እንዲህ አሉት፤ 63“ክቡር ሆይ፤ ያ አሳች በሕይወት ሳለ፣ ‘ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ’ ያለው ትዝ ብሎናል፤ 64ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ አስከሬኑን ሰርቀው ለሕዝቡ፣ ‘ከሙታን ተነሥቷል’ ብለው እንዳያስወሩ መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ ትእዛዝ ስጥልን፤ አለዚያ የኋለኛው ስሕተት ከፊተኛው የባሰ ይሆናል!”

65ጲላጦስም፣ “ጠባቂዎች አሏችሁ፤ ሄዳችሁ በምታውቁት መንገድ አስጠብቁ” አላቸው። 66እነርሱም ሄደው መቃብሩን በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት።

King James Version

Matthew 27:1-66

1When the morning was come, all the chief priests and elders of the people took counsel against Jesus to put him to death: 2And when they had bound him, they led him away, and delivered him to Pontius Pilate the governor.

3¶ Then Judas, which had betrayed him, when he saw that he was condemned, repented himself, and brought again the thirty pieces of silver to the chief priests and elders, 4Saying, I have sinned in that I have betrayed the innocent blood. And they said, What is that to us? see thou to that. 5And he cast down the pieces of silver in the temple, and departed, and went and hanged himself. 6And the chief priests took the silver pieces, and said, It is not lawful for to put them into the treasury, because it is the price of blood. 7And they took counsel, and bought with them the potter’s field, to bury strangers in. 8Wherefore that field was called, The field of blood, unto this day. 9Then was fulfilled that which was spoken by Jeremy the prophet, saying, And they took the thirty pieces of silver, the price of him that was valued, whom they of the children of Israel did value; 10And gave them for the potter’s field, as the Lord appointed me. 11And Jesus stood before the governor: and the governor asked him, saying, Art thou the King of the Jews? And Jesus said unto him, Thou sayest. 12And when he was accused of the chief priests and elders, he answered nothing. 13Then said Pilate unto him, Hearest thou not how many things they witness against thee? 14And he answered him to never a word; insomuch that the governor marvelled greatly. 15Now at that feast the governor was wont to release unto the people a prisoner, whom they would. 16And they had then a notable prisoner, called Barabbas. 17Therefore when they were gathered together, Pilate said unto them, Whom will ye that I release unto you? Barabbas, or Jesus which is called Christ? 18For he knew that for envy they had delivered him.

19¶ When he was set down on the judgment seat, his wife sent unto him, saying, Have thou nothing to do with that just man: for I have suffered many things this day in a dream because of him. 20But the chief priests and elders persuaded the multitude that they should ask Barabbas, and destroy Jesus. 21The governor answered and said unto them, Whether of the twain will ye that I release unto you? They said, Barabbas. 22Pilate saith unto them, What shall I do then with Jesus which is called Christ? They all say unto him, Let him be crucified. 23And the governor said, Why, what evil hath he done? But they cried out the more, saying, Let him be crucified.

24¶ When Pilate saw that he could prevail nothing, but that rather a tumult was made, he took water, and washed his hands before the multitude, saying, I am innocent of the blood of this just person: see ye to it. 25Then answered all the people, and said, His blood be on us, and on our children.

26¶ Then released he Barabbas unto them: and when he had scourged Jesus, he delivered him to be crucified. 27Then the soldiers of the governor took Jesus into the common hall, and gathered unto him the whole band of soldiers. 28And they stripped him, and put on him a scarlet robe.

29¶ And when they had platted a crown of thorns, they put it upon his head, and a reed in his right hand: and they bowed the knee before him, and mocked him, saying, Hail, King of the Jews! 30And they spit upon him, and took the reed, and smote him on the head. 31And after that they had mocked him, they took the robe off from him, and put his own raiment on him, and led him away to crucify him. 32And as they came out, they found a man of Cyrene, Simon by name: him they compelled to bear his cross. 33And when they were come unto a place called Golgotha, that is to say, a place of a skull,

34¶ They gave him vinegar to drink mingled with gall: and when he had tasted thereof, he would not drink. 35And they crucified him, and parted his garments, casting lots: that it might be fulfilled which was spoken by the prophet, They parted my garments among them, and upon my vesture did they cast lots. 36And sitting down they watched him there; 37And set up over his head his accusation written, THIS IS JESUS THE KING OF THE JEWS. 38Then were there two thieves crucified with him, one on the right hand, and another on the left.

39¶ And they that passed by reviled him, wagging their heads, 40And saying, Thou that destroyest the temple, and buildest it in three days, save thyself. If thou be the Son of God, come down from the cross. 41Likewise also the chief priests mocking him, with the scribes and elders, said, 42He saved others; himself he cannot save. If he be the King of Israel, let him now come down from the cross, and we will believe him. 43He trusted in God; let him deliver him now, if he will have him: for he said, I am the Son of God. 44The thieves also, which were crucified with him, cast the same in his teeth. 45Now from the sixth hour there was darkness over all the land unto the ninth hour. 46And about the ninth hour Jesus cried with a loud voice, saying, Eli, Eli, lama sabachthani? that is to say, My God, my God, why hast thou forsaken me? 47Some of them that stood there, when they heard that, said, This man calleth for Elias. 48And straightway one of them ran, and took a spunge, and filled it with vinegar, and put it on a reed, and gave him to drink. 49The rest said, Let be, let us see whether Elias will come to save him.

50¶ Jesus, when he had cried again with a loud voice, yielded up the ghost. 51And, behold, the veil of the temple was rent in twain from the top to the bottom; and the earth did quake, and the rocks rent; 52And the graves were opened; and many bodies of the saints which slept arose, 53And came out of the graves after his resurrection, and went into the holy city, and appeared unto many. 54Now when the centurion, and they that were with him, watching Jesus, saw the earthquake, and those things that were done, they feared greatly, saying, Truly this was the Son of God. 55And many women were there beholding afar off, which followed Jesus from Galilee, ministering unto him: 56Among which was Mary Magdalene, and Mary the mother of James and Joses, and the mother of Zebedee’s children. 57When the even was come, there came a rich man of Arimathæa, named Joseph, who also himself was Jesus’ disciple: 58He went to Pilate, and begged the body of Jesus. Then Pilate commanded the body to be delivered. 59And when Joseph had taken the body, he wrapped it in a clean linen cloth, 60And laid it in his own new tomb, which he had hewn out in the rock: and he rolled a great stone to the door of the sepulchre, and departed. 61And there was Mary Magdalene, and the other Mary, sitting over against the sepulchre.

62¶ Now the next day, that followed the day of the preparation, the chief priests and Pharisees came together unto Pilate, 63Saying, Sir, we remember that that deceiver said, while he was yet alive, After three days I will rise again. 64Command therefore that the sepulchre be made sure until the third day, lest his disciples come by night, and steal him away, and say unto the people, He is risen from the dead: so the last error shall be worse than the first. 65Pilate said unto them, Ye have a watch: go your way, make it as sure as ye can. 66So they went, and made the sepulchre sure, sealing the stone, and setting a watch.