ማቴዎስ 24 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 24:1-51

የዓለም መጨረሻ ምልክቶች

24፥1-51 ተጓ ምብ – ማር 13፥1-37ሉቃ 21፥5-36

1ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሲሄድ፣ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሊያሳዩት ወደ እርሱ ቀረቡ። 2እርሱ ግን፣ “ይህን ሁሉ ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ተክቦ የምታዩት፣ ሳይፈርስ እንዲሁ እንዳለ የሚቀር አንድ ድንጋይ እንኳ አይኖርም” አላቸው።

3በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “እስቲ ንገረን፤ የምትለው ሁሉ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክትስ ምንድን ነው?” አሉት።

4ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ 5ብዙዎች፣ ‘እኔ ክርስቶስ24፥5 ወይም መሲሕ፤ 23 ይመ ነኝ’ በማለት በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። 6ስለ ጦርነትና ጦርነትን የሚያናፍስ ወሬ ትሰማላችሁ፤ እነዚህ ነገሮች የግድ መፈጸም አለባቸው፤ ሆኖም መጨረሻው ገና ስለሆነ በዚህ እንዳትደናገጡ ተጠንቀቁ። 7ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በተለያየ ስፍራም ራብና የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፤ 8ይህ ሁሉ ግን የምጡ መጀመሪያ ነው።

9“በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችኋል፤ በስሜ ምክንያት በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። 10በዚያን ጊዜ ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ ይጠላላሉም። 11ብዙዎች ሐሰተኛ ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችን ያስታሉ። 12ክፋት ስለሚገንን የብዙ ሰዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፤ 13እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። 14ለሕዝብ ሁሉ ምስክር እንዲሆን፣ ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።

15“እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተነገረው፣ ‘የጥፋት ርኩሰት’ በተቀደሰው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፣ አንባቢው ያስተውል። 16በዚያን ጊዜ በይሁዳ የሚገኙ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፤ 17በቤቱ ጣራ ላይ የሚገኝ ማንም ሰው ዕቃውን ከቤቱ ለማውጣት አይውረድ፤ 18በዕርሻ ቦታው የሚገኝ ማንም ሰው ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ። 19በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! 20እንግዲህ ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት ቀን እንዳይሆን ጸልዩ፤ 21በዚያን ጊዜ፣ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሆኖ የማያውቅ፣ ከዚያም በኋላ የሚስተካከለው የሌለ፣ ታላቅ መከራ ይሆናል። 22ቀኖቹ ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ባልተረፈ ነበረ፤ ስለተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ። 23በዚያን ጊዜ ማንም፣ ‘ይኸውላችሁ ክርስቶስ እዚህ አለ’ ወይም ‘እዚያ አለ’ ቢላችሁ አትመኑ፤ 24ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነቢያት ይነሣሉና፤ ቢቻል የተመረጡትን ለማሳት ሲሉ ታላላቅ ምልክቶችንና ታምራትን ያደርጋሉ። 25እነሆ፤ አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ።

26“ስለዚህ፣ ‘ያውላችሁ በረሓው ውስጥ አለላችሁ’ ቢሏችሁ ወደዚያ አትውጡ፤ ‘ይኸውላችሁ እልፍኝ ውስጥ አለላችሁ’ ቢሏችሁ አትመኑ፤ 27መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ ምዕራብ ድረስ እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅ አመጣጥም እንደዚሁ ይሆናል። 28በድን ባለበት ስፍራ ሁሉ አሞሮች ይሰበሰባሉ።

29“ወዲያውኑ ከእነዚያ ከመከራው ቀናት በኋላ፣

“ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፤

ጨረቃ ብርሃኗን ትከለክላለች፤

ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤

የሰማይ ኅይላትም ይናጋሉ።’

30“በዚህ ጊዜ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ላይ ይታያል፤ የምድር ወገኖች ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የሰው ልጅም በሰማይ ደመና ሆኖ በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፤ 31መላእክቱንም ከታላቅ የመለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም ምርጦቹን ከአራቱም ነፋሳት፣ ከሰማያት ከአንዱ ዳርቻ ወደ ሌላው ዳርቻ ይሰበስባሉ።

32“ከበለስ ዛፍ ይህን ትምህርት ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለመልም፣ ቅጠሏ ሲያቈጠቍጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደ ተቃረበ ታውቃላችሁ። 33እንደዚሁም እነዚህን ሁሉ ስታዩ፣ እርሱ በደጅ እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ። 34እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ትውልድ24፥34 ወይም ዘር አያልፍም። 35ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።

የሚመጣበት ቀንና ሰዓት አለመታወቁ

24፥37-39 ተጓ ምብ – ሉቃ 17፥2627

24፥45-51 ተጓ ምብ – ሉቃ 12፥42-46

36“ያን ቀንና ሰዓት ግን ከአብ በስተቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፣ ወልድም ቢሆን24፥36 አንዳንድ ቅጆች ወልድም ቢሆን የሚለው የላቸውም። ማንም አያውቅም። 37ልክ በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው የሰው ልጅ መምጣትም እንደዚሁ ይሆናል፤ 38ከጥፋት ውሃ በፊት ኖኅ ወደ መርከቡ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡ እንደ ነበሩ፣ 39እስከዚያ ጊዜ ድረስም ምን እንደሚመጣ ሳያውቁ ድንገት የጥፋት ውሃ እንዳጥለቀለቃቸው፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንደዚሁ ይሆናል። 40በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ላይ ይውላሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። 41ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፣ ሌላዋ ትቀራለች።

42“እንግዲህ ጌታችሁ የሚመጣበትን ቀን ስለማታውቁ ነቅታችሁ ጠብቁ። 43ይህን ልብ በሉ፤ ባለቤት ሌሊት ሌባ በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፣ በነቃ፣ ቤቱም እንዳይደፈር በተጠባበቀ ነበር። 44የሰው ልጅም ባላሰባችሁት ሰዓት ይመጣልና እናንተም እንደዚሁ ዝግጁ ሁኑ።

45“በተገቢው ጊዜ ምግባቸውን እንዲሰጣቸው ባለቤቱ በቤተ ሰዎቹ ላይ የሾመው ታማኝና ብልኅ አገልጋይ እንግዲህ ማነው? 46ባለቤቱ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የተጣለበትን ዐደራ እየፈጸመ የሚያገኘው ያ አገልጋይ የተባረከ ነው፤ 47እውነት እላችኋለሁ፤ በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል። 48ነገር ግን ያ አገልጋይ ክፉ ቢሆንና ለራሱ፣ ‘ጌታዬ ይዘገያል’ በማለት፣ 49ተነሥቶ ሌሎች አገልጋይ ባልንጀሮቹን መምታት ቢጀምር፣ ከሰካራሞችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፣ 50እርሱ ባልጠበቀው ቀንና ባላሰበው ሰዓት ጌታው መጥቶ፣ 51ይቈራርጠዋል፤ ዕድል ፈንታውንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

馬太福音 24:1-51

預言聖殿被毀

1耶穌離開聖殿時,門徒上前把宏偉的聖殿指給祂看。 2耶穌對他們說:「你們看見這殿宇了嗎?我實在告訴你們,將來它要被完全拆毀,在這裡找不到兩塊疊在一起的石頭。」

世界末日的預兆

3耶穌正坐在橄欖山上,門徒私下來問祂:「請告訴我們,這事什麼時候會發生?你再來和世界末日的時候會有什麼預兆?」

4耶穌回答說:「你們要小心,免得被人迷惑。 5因為將來會有許多人冒我的名而來,說『我是基督』,欺騙許多人。 6你們聽見戰爭爆發、戰訊頻傳時,不要驚慌,因為這些事必然發生,只是末日還沒有到。 7民族將與民族互鬥,國家將與國家相爭,各處將有饑荒和地震。 8這些只是災難24·8 災難」希臘文是「生產之痛」。的開始。

9「那時,你們將遭人迫害、殺害,並因我的名而被萬民憎恨。 10那時,許多人會放棄信仰,互相出賣,彼此憎恨。 11許多假先知也會出現,迷惑許多人。 12由於罪惡氾濫,許多人的愛逐漸冷淡。 13但堅忍到底的必定得救。 14這天國的福音將傳遍天下,讓萬民都聽見,然後末日才會來臨。

15「當你們看見但以理先知所說的『那帶來毀滅的可憎之物』站立在聖地的時候(讀者須會意), 16住在猶太地區的人要趕快逃到山上去, 17在屋頂上的人不要下來進屋收拾行李, 18在田間工作的人也不要回家取外衣。 19那時,孕婦和哺育嬰兒的母親們可就遭殃了! 20你們要祈求上帝,不要讓你們在冬天或安息日逃難, 21因為那時世上將有空前絕後的大災難。 22如果不縮短災期,恐怕沒有人能活命。但為了選民的緣故,災期必被縮短。

23「那時,如果有人對你們說,『看啊!基督在這裡』,或說,『基督在那裡』,你們不要相信。 24因為假基督和假先知將出現,行很大的神蹟奇事來迷惑人,如果可能,甚至要迷惑上帝揀選的子民。 25你們要記住,我已經預先告訴你們了。

26「因此,如果有人對你們說,『看啊!基督在曠野』,你們不要出去;或者說,『看啊!基督在屋裡』,你們也不要相信。 27人子降臨時的情形就像閃電從東方發出一直照到西方。 28屍體在哪裡,禿鷹就會聚集在哪裡。

29「當災難的日子一過,

『太陽變黑,

月亮無光,

眾星隕落,

天體震動。』

30「那時,天上會出現人子降臨的預兆,地上的萬族都要哀哭,他們將看見人子帶著能力和極大的榮耀駕著天上的雲降臨。 31在響亮的號聲中,祂將差遣天使從四面八方、天涯海角招聚祂揀選的人。

無花果樹的比喻

32「你們可以從無花果樹學個道理。當無花果樹發芽長葉的時候,你們就知道夏天快來了。 33同樣,當你們看見這一切事發生時,就知道人子快來了,就在門口。 34我實在告訴你們,這個世代還沒有過去,這一切都要發生。 35天地都要過去,但我的話永遠長存。

警醒準備

36「但沒有人知道那日子和時辰何時來到,連天上的天使也不知道,人子24·36 人子」希臘文是「子」。也不知道,只有天父知道。 37人子降臨時的情形就像挪亞的時代。 38洪水來臨之前,人們吃吃喝喝,男婚女嫁,一直到挪亞進方舟那天; 39他們懵然不知,直到洪水來把他們全沖走了。人子降臨時的情形也是這樣。 40那時,兩個人在田裡,一個將被接去,一個將被撇下; 41兩個婦人推磨,一個將被接去,一個將被撇下。 42所以,你們要警醒,因為你們不知道你們的主會在哪一天來。 43你們都知道,如果一家的主人知道賊會在半夜幾點來,就必警醒,不讓賊入屋偷竊。 44同樣,你們也要做好準備,因為在你們意想不到的時候,人子就來了。

兩種奴僕

45「誰是那個受主人委託管理家中大小僕役、按時分糧食給他們、又忠心又精明的奴僕呢? 46主人回家時,看見他盡忠職守,他就有福了。 47我實在告訴你們,主人一定會把所有產業都交給他管理。 48但如果奴僕邪惡,以為主人不會那麼快回來, 49就毆打同伴,跟醉漢一起吃喝玩樂, 50主人會在他想不到的日子、不知道的時辰回來, 51嚴厲地懲罰24·51 嚴厲地懲罰」或作「腰斬」。他,判他和偽君子同樣的罪。他必在那裡哀哭切齒。