ኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ
21፥1-9 ተጓ ምብ – ማር 11፥1-10፤ ሉቃ 19፥29-38
21፥4-9 ተጓ ምብ – ዮሐ 12፥12-15
1ኢየሩሳሌም መቃረቢያ ደብረ ዘይት ተራራ ላይ ወደምትገኘው ቤተ ፋጌ ወደተባለችው ስፍራ እንደ ደረሱ፣ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ 2እንዲህ አላቸው “በአቅራቢያችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፤ እንደ ደረሳችሁም አንዲት አህያ ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም ወደ እኔ አምጧቸው። 3ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ፣ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉት፤ እርሱም ወዲያውኑ ይሰድዳቸዋል።”
4ይህ የሆነውም በነቢዩ እንዲህ በማለት የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው።
5“ለጽዮን ልጅ እንዲህ በሏት፤
‘እነሆ፤ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ፣
በአህያዪቱና በግልገሏ፣
በውርንጫዪቱም ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።’ ”
6ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ። 7አህያዪቱንና ውርንጫዋን አምጥተው ልብሶቻቸውን በላያቸው ላይ አኖሩ፤ እርሱም ተቀመጠባቸው። 8ከሕዝቡም አብዛኛው ልብሶቻቸውን፣ በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎቹም ከዛፎች ቅርንጫፍ እየዘነጠፉ በመንገዱ ላይ ጣል ጣል አደረጉ። 9ቀድሞት ከፊቱ የሚሄደውና ከኋላው ይከተለው የነበረው ሕዝብም እንዲህ እያለ ይጮኽ ነበር፤
“ሆሣዕና21፥9 በዕብራይስጡ አገላለጽ አሁን አድን! ማለት ሲሆን የምስጋና አገላለጽ ነው፤ 15 ይመ ለዳዊት ልጅ!”
“በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!”
“ሆሣዕና በአርያም!”
10ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜም ከተማዋ በመላ፣ “ይህ ማነው?” በማለት ታወከች።
11ሕዝቡም፣ “ይህ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” አሉ።
ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲነግዱ ያገኛቸውን አስወጣቸው
21፥12-16 ተጓ ምብ – ማር 11፥15-18፤ ሉቃ 19፥45-47
12ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይሸጡና ይገዙ የነበሩትን አባረራቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ በመገለባበጥ፣ 13“ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል፤ እናንተ ግን፣ ‘የዘራፊዎች ዋሻ’ አደረጋችሁት” አላቸው።
14በቤተ መቅደሱም ውስጥ ዐይነ ስውሮችና ሽባዎች ወደ እርሱ ቀረቡ፤ እርሱም ፈወሳቸው። 15ነገር ግን የካህናት አለቆችና የኦሪት ሕግ መምህራን ያደረጋቸውን ታምራትና፣ “ሆሣዕና፤ ለዳዊት ልጅ” እያሉ የሚጮኹትን ሕፃናት ባዩ ጊዜ በቍጣ ተሞሉ።
16እነርሱም፣ “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህ?” አሉት።
ኢየሱስም፣ “አዎን እሰማለሁ፤ እንዲህ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?
“ ‘ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ፣
ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ።’ ”
17ትቷቸው ከከተማው ወጣ፤ ወደ ቢታንያም ሄዶ በዚያው ዐደረ።
ፍሬ አልባ የሆነችው በለስ
21፥18-22 ተጓ ምብ – ማር 11፥12-14፡20-24
18ኢየሱስ በማግስቱም ማለዳ ወደ ከተማዪቱ በመመለስ ላይ ሳለ ተራበ፤ 19በመንገድ ዳርም አንድ የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ ሲሄድ ከቅጠል በስተቀር ምንም ስላላገኘባት፣ “ከእንግዲህ ፍሬ አይኑርብሽ!” አላት፤ የበለሷ ዛፍ ወዲያውኑ ደረቀች።
20ደቀ መዛሙርቱም የሆነውን አይተው በመደነቅ፣ “የበለሷ ዛፍ እንዴት በአንዴ ልትደርቅ ቻለች?” አሉ።
21ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩ፣ በበለሷ ዛፍ ላይ የሆነውን ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ተራራ፣ ‘ከዚህ ተነቅለህ ባሕር ውስጥ ግባ’ ብትሉት እንኳ ይሆናል፤ 22እምነት ካላችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።”
በኢየሱስ ሥልጣን ላይ የቀረበ ጥያቄ
21፥23-27 ተጓ ምብ – ማር 11፥27-33፤ ሉቃ 20፥1-8
23ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ፣ የካህናት አለቆችና የሕዝብ ሽማግሌዎች ቀርበው፣ “ይህን ሁሉ ነገር የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ሥልጣንስ የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት።
24ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፤ መልሱን ብትነግሩኝ፣ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፤ 25የዮሐንስ ጥምቀት የመጣው ከየት ነበር? ከሰማይ ወይስ ከሰዎች?”
እነርሱም እርስ በርስ በመነጋገር እንዲህ ተባባሉ፤ “ ‘ከሰማይ ነው?’ ካልን ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም?’ ይለናል፤ 26‘ከሰዎች ነው’ ካልን ደግሞ፣ ‘ሕዝቡ ዮሐንስን ነቢይ ነው’ ብሎ ስለሚያምን እንፈራለን።”
27ስለዚህ፣ “አናውቅም” ብለው ለኢየሱስ መለሱለት።
እርሱም፣ “እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
የመታዘዝ ትርጕም
28ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ምን ይመስላችኋል? ሁለት ወንዶች ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበረ፤ ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ፣ ‘ልጄ ሆይ፤ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ’ አለው።
29“ልጁም፣ ‘አልሄድም’ አለው፤ ኋላ ግን ተጸጽቶ ሄደ።
30“ወደ ሁለተኛው ልጁ ሄዶ እንደዚያው አለው፤ ልጁም ‘እሺ ጌታዬ እሄዳለሁ’ አለው፤ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ።
31“ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?”
እነርሱም፣ “የመጀመሪያው ልጅ” አሉት።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሟችኋል፤ 32መጥምቁ ዮሐንስ የጽድቅን መንገድ ሊያሳያችሁ ወደ እናንተ መጣ፤ እናንተ አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። የሆነውን ካያችሁ በኋላ እንኳ ንስሓ ገብታችሁ አላመናችሁትም።
የወይን ዕርሻ ገበሬዎች ምሳሌ
21፥33-46 ተጓ ምብ – ማር 12፥1-12፤ ሉቃ 20፥9-19
33“ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ አንድ የወይን ዕርሻ ባለቤት ነበረ፤ በዕርሻው ዙሪያ ዐጥር ዐጠረ፤ ለወይኑ መጭመቂያ ጕድጓድ ቈፈረ፤ ለጥበቃ የሚሆን ማማ ሠራ፤ ከዚያም ዕርሻውን ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 34የመከር ወራት ሲደርስ፣ ፍሬውን ለመቀበል አገልጋዮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላካቸው።
35“ገበሬዎቹም አገልጋዮቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት። 36እርሱም ከፊተኞቹ የሚበልጡ ሌሎች አገልጋዮቹን ላከ፤ ገበሬዎቹም ተመሳሳይ ድርጊት ፈጸሙባቸው። 37በመጨረሻም፣ ‘ልጄን ያከብሩታል’ በማለት ልጁን ላከ።
38“ነገር ግን ገበሬዎቹ ልጁን ባዩት ጊዜ፣ ‘ይህማ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ። 39ይዘውም ከወይኑ ዕርሻ ውጭ አውጥተው ገደሉት።
40“ታዲያ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት ሲመጣ፣ እነዚያን ገበሬዎች ምን የሚያደርጋቸው ይመስላችኋል?”
41እነርሱም፣ “እነዚያን ክፉዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ከወይኑ ዕርሻ ተገቢውን ፍሬ በወቅቱ ለሚያስረክቡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።
42ኢየሱስም እንዲህ ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን አላነበባችሁምን? አላቸው፤
“ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣
የማእዘን ራስ21፥42 ወይም የማእዘን ድንጋይ ሆነ፤
እግዚአብሔር ይህን አድርጓል፤
ሥራውም ለዐይናችን ድንቅ ነው።’
43“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች፤ 44በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ ደግሞ የሚወድቅበትን ማንኛውንም ሰው ይፈጨዋል።”21፥44 አንዳንድ ቅጆች ቍጥር 44 የላቸውም።
45የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ ስለ እነርሱ የሚናገር መሆኑን ዐወቁ። 46ነገር ግን ይዘው ሊያስሩት ቢፈልጉም፣ ሕዝቡ ኢየሱስን እንደ ነቢይ አድርጎ ይመለከት ስለ ነበር ፈሩ።
Mesijanski ulazak u Jeruzalem
(Mk 11:1-10; Lk 19:28-38; Iv 12:12-19)
1Kad su se Isus i učenici približili Jeruzalemu te stigli pred Betfagu na Maslinskoj gori, Isus pošalje naprijed dvojicu učenika. 2“Idite u selo pred vama”, reče im, “i čim u njega uđete, ugledat ćete vezanu magaricu i magare. Odvežite ih i dovedite k meni. 3Upita li vas tko zbog toga, recite samo: ‘Gospodinu trebaju’ pa će ih odmah pustiti.” 4To se dogodilo da se ispuni proročanstvo:
5“Recite izraelskomu narodu21:5 U grčkome: Recite kćeri sionskoj; Izaija 62:11.:
Evo, dolazi tvoj Kralj,
ponizan jaše na magarcu,
na magaretu, mladomu magaričinu.”21:5 Zaharija 9:9.
6Učenici odu i učine kako ih je Isus uputio. 7Dovedu magaricu i magare, prekriju ih svojim ogrtačima, pa Isus sjedne na njih.
8Silno je mnoštvo prostiralo svoje ogrtače po putu, a neki su trgali grane s drveća i prostirali ih putem. 9Ljudi koji su išli pred njim i za njim klicali su:
“Slava21:9 U grčkome: Hosanna! (uzvik slavljenja koji doslovce znači “Spasi, molim te!”) Sinu Davidovu!
Blagoslovljen koji dolazi u ime Gospodnje!
Slava Bogu na nebu!”21:9 Psalam 118:25-26 i Psalam 148:1.
10Kad je ušao u Jeruzalem, cijeli se grad uskomešao. “Tko je taj?” pitali su.
11Mnoštvo je odgovaralo: “To je Isus, prorok iz Nazareta u Galileji.”
Isus izgoni trgovce iz Hrama
(Mk 11:15-19; Lk 19:45-47; Iv 2:13-17)
12Isus uđe u Hram i počne iz njega izgoniti sve trgovce i njihove kupce, prevrne stolove mjenjačima novca i klupe prodavačima goluba. 13“U Svetome pismu piše: ‘Moj Hram treba biti molitveni dom’, a vi ste ga pretvorili u razbojničku špilju!”21:13 Izaija 56:7; Jeremija 7:11.
14U Hramu mu priđu slijepi i hromi te ih on iscijeli. 15Kad su svećenički poglavari i pismoznanci vidjeli čudesa koja je učinio i čuli djecu u Hramu kako kliču: “Slava21:15 U grčkome: Hosanna! Sinu Davidovu!” razgnjeve se 16i upitaju ga: “Čuješ li ti što govore?”
“Čujem”, odgovori im Isus. “A niste li nikad u Pismu pročitali: ‘Pripravio si sebi hvalu iz usta djece i dojenčadi’?”21:16 Psalam 8:2. 17Zatim se vrati u Betaniju da ondje prespava.
Isus proklinje smokvu
(Mk 11:12-14, 20-24)
18Vraćajući se ujutro u Jeruzalem, Isus ogladni. 19Opazi pokraj puta smokvu i priđe joj, ali na njoj ne nađe ničega osim lišća. Nato joj reče: “Ne bilo više nikada na tebi roda!” I smokva se smjesta osuši.
20Učenici se zaprepaste. “Kako se smokva tako brzo sasušila?” pitali su.
21“Zaista vam kažem,” odgovori im Isus, “budete li imali vjere i ne budete li sumnjali, činit ćete ne samo to što sam ja učinio sa smokvom nego kažete li ovoj planini: ‘Digni se i baci se u more!’—to će se i dogoditi. 22Sve što s vjerom zamolite, primit ćete.”
O Isusovoj vlasti
(Mk 11:27-33; Lk 20:1-8)
23Isus ode u Hram. Dok je ondje poučavao, priđu mu svećenički poglavari i narodni starješine pa ga upitaju: “Tko ti je dao pravo da to činiš? Tko te je ovlastio za to?”
24Isus im odgovori: “Reći ću vam tko ako najprije vi meni odgovorite na pitanje: 25Je li Ivanovo krštenje bilo s neba ili od ljudi?”
Oni počnu umovati i međusobno raspravljati: “Ako kažemo da je s neba, pitat će nas zašto mu onda nismo vjerovali. 26A od mnoštva nas je strah reći da je bilo od ljudi jer Ivana svi drže za proroka.” 27Zato Isusu odgovore: “Ne znamo.”
A Isus im reče: “Onda ni ja vama neću reći otkuda mi vlast!”
Prispodoba o dvojici sinova
28“Što mislite o ovomu: Neki je čovjek imao dva sina. Reče prvomu: ‘Sine, idi danas raditi u vinogradu!’ 29‘Neću!’ odgovori on, ali se poslije predomisli i ode. 30Otac i drugome sinu reče isto. ‘Idem, oče!’ odgovori sin, ali se zatim predomisli i odustane. 31Koji je od njih dvojice ispunio očevu volju?”
“Onaj prvi”, odgovore.
Isus im nato reče: “Zaista vam kažem, bludnice i ubirači poreza ući će prije vas u Božje kraljevstvo! 32Jer Ivan Krstitelj došao vam je pokazati put pravednosti, ali mu niste povjerovali, a bludnice i ubirači poreza jesu. Pa čak ni kad ste to vidjeli, niste se pokajali i vjerovali mu.”
Prispodoba o zlim vinogradarima
(Mk 12:1-12; Lk 20:9-19)
33“Poslušajte još jednu prispodobu. Neki čovjek posadi vinograd i ogradi ga, iskopa tijesak za grožđe i izgradi kulu. Zatim ga iznajmi vinogradarima i otputuje. 34Kad dođe vrijeme berbe, pošalje sluge da uzmu njegov dio uroda.
35Ali vinogradari ih pograbe te jednoga pretuku, drugoga ubiju, a trećega kamenuju. 36On zatim pošalje više slugu nego prvi put, ali vinogradari i s njima jednako postupe.
37Naposljetku pošalje k njima svojega sina misleći: ‘Prema mojem sinu sigurno će se odnositi s poštovanjem.’
38Ali kad vinogradari ugledaju sina, rekoše: ‘Ovaj će naslijediti imanje. Ubijmo ga pa ćemo se domognuti imanja umjesto njega!’ 39Pograbe ga, izbace iz vinograda i ubiju.”
40Isus ih upita: “Što mislite, kako će vlasnik imanja postupiti s tim vinogradarima kada se vrati?”
41Oni mu odgovorili: “Te će zlikovce bez smilovanja pogubiti, a vinograd iznajmiti drugima koji će mu davati urod kad za to dođe vrijeme.”
42Isus ih upita: “Niste li nikada čitali u Svetom pismu:
‘Kamen koji su graditelji odbacili
postane ugaonim kamenom.
To je Gospodnje djelo,
čudesno u našim očima.’21:42 Psalam 118:22-23.?
43Zato vam kažem, oduzet će vam se Božje kraljevstvo i dat će se narodu koji će davati njegove plodove. 44Padne li tko na taj kamen, smrskat će se, i padne li kamen na koga, satrt će ga.”
45Kad su svećenički poglavari i farizeji čuli te prispodobe i shvatili da govori o njima, 46htjeli su ga uhvatiti, ali bojali su se mnoštva koje je Isusa smatralo prorokom.