ማቴዎስ 16 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ማቴዎስ 16:1-28

ኢየሱስ ከሰማይ ምልክት እንዲያሳይ መጠየቁ

16፥1-12 ተጓ ምብ – ማር 8፥11-21

1ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው ሊፈትኑት በመሻት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።

2እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤16፥2 አንዳንድ የጥንት ቅጆች የቍጥር 2 ከፊልና ቍጥር 3 በሙሉ የላቸውም። “ምሽት ላይ፣ ‘ሰማዩ ስለ ቀላ ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ፤ 3ንጋት ላይም፣ ‘ሰማዩ ቀልቷል፣ ከብዷልም፤ ስለዚህ ዝናብ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ገጽታ ትለያላችሁ፤ ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም። 4ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዮናስ ምልክት በስተቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።” ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ሄደ።

የፈሪሳውያንና የሰዱቃውያን እርሾ

5ባሕሩን እንደ ተሻገሩም፣ ደቀ መዛሙርቱ እንጀራ መያዝ ረስተው ነበር። 6ኢየሱስም፣ “ልብ በሉ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠበቁ” አላቸው።

7እነርሱ ግን እርስ በርሳቸው፣ “እንጀራ ስላልያዝን ይሆናል” ተባባሉ።

8ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እርስ በርሳችሁ እንጀራ ስለ አለመያዛችሁ ለምን ትነጋገራላችሁ? 9አምስቱ እንጀራ ለአምስት ሺሕ ሰው በቅቶ ስንት መሶብ ተርፎ እንዳነሣችሁ አታስታውሱምን? 10እንዲሁም ሰባቱ እንጀራ ለአራት ሺሕ ሰው በቅቶ ስንት መሶብ ተርፎ እንዳነሣችሁ ልብ አላላችሁም ማለት ነውን? 11ታዲያ የነገርኋችሁ ስለ እንጀራ እንዳልሆነ እንዴት አታስተውሉም? አሁንም ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ።” 12በዚህ ጊዜ ያስጠነቀቃቸው እንጀራ ውስጥ ስለሚጨመረው እርሾ ሳይሆን፣ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት መሆኑ ገባቸው።

ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ማንነት መናገሩ

16፥13-16 ተጓ ምብ – ማር 8፥27-29ሉቃ 9፥18-20

13ኢየሱስ ፊልጶስ ቂሳርያ ወደተባለው አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ “ለመሆኑ ሰዎች፣ የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?” ብሎ ጠየቃቸው።

14እነርሱም፣ “አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” አሉት።

15እርሱም፣ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው።

16ስምዖን ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ16፥16 ወይም መሲሕ፤ 20 ይመ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት መለሰ።

17ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ብፁዕ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም አይደለም። 18አንተ ጴጥሮስ16፥18 ጴጥሮስ ትርጕሙ ዐለት ማለት ነው። ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም።16፥18 ወይም ሊቋቋሟት አይችሉም 19የመንግሥተ ሰማይን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርኸው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድርም የፈታኸው ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።” 20ቀጥሎም እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አስጠነቀቃቸው።

ኢየሱስ ስለሚደርስበት መከራ ተናገረ

16፥21-28 ተጓ ምብ – ማር 8፥31–9፥1ሉቃ 9፥22-27

21ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ፣ በዚያም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በኦሪት ሕግ መምህራን እጅ መከራን ይቀበልና ይገደል ዘንድ፣ በሦስተኛው ቀን ከሞት ይነሣ ዘንድ እንደሚገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጽላቸው ጀመር።

22ጴጥሮስም ኢየሱስን ወደ ጐን ሳብ አድርጎ፣ “ጌታ ሆይ፤ እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይድረስብህ” እያለ ይገሥጸው ጀመር።

23ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ዘወር ብሎ፣ “አንተ ሰይጣን፣ ወደ ኋላዬ ሂድ፤ የሰው እንጂ የእግዚአብሔር ነገር በዐሳብህ ስለሌለ መሰናክል ሆነህብኛል!” አለው።

24ከዚያም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሊከተለኝ የሚወድድ ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ 25ነፍሱን16፥25 የግሪኩ ቃል ትርጕም ሕይወት ወይም ነፍስ ነው፤ እንደዚሁም 26። ሊያድን የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነገር ግን ነፍሱን ስለ እኔ የሚያጠፋት ያድናታል። 26ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ፣ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው በነፍሱ ምትክ ሊከፍለው የሚችለው ዋጋ ምንድን ነው? 27የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክት ጋር ይመጣል፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል። 28እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት ሰዎች መካከል፣ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስከሚያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አሉ።”

New International Version

Matthew 16:1-28

The Demand for a Sign

1The Pharisees and Sadducees came to Jesus and tested him by asking him to show them a sign from heaven.

2He replied, “When evening comes, you say, ‘It will be fair weather, for the sky is red,’ 3and in the morning, ‘Today it will be stormy, for the sky is red and overcast.’ You know how to interpret the appearance of the sky, but you cannot interpret the signs of the times.16:2,3 Some early manuscripts do not have When evening comes… of the times. 4A wicked and adulterous generation looks for a sign, but none will be given it except the sign of Jonah.” Jesus then left them and went away.

The Yeast of the Pharisees and Sadducees

5When they went across the lake, the disciples forgot to take bread. 6“Be careful,” Jesus said to them. “Be on your guard against the yeast of the Pharisees and Sadducees.”

7They discussed this among themselves and said, “It is because we didn’t bring any bread.”

8Aware of their discussion, Jesus asked, “You of little faith, why are you talking among yourselves about having no bread? 9Do you still not understand? Don’t you remember the five loaves for the five thousand, and how many basketfuls you gathered? 10Or the seven loaves for the four thousand, and how many basketfuls you gathered? 11How is it you don’t understand that I was not talking to you about bread? But be on your guard against the yeast of the Pharisees and Sadducees.” 12Then they understood that he was not telling them to guard against the yeast used in bread, but against the teaching of the Pharisees and Sadducees.

Peter Declares That Jesus Is the Messiah

13When Jesus came to the region of Caesarea Philippi, he asked his disciples, “Who do people say the Son of Man is?”

14They replied, “Some say John the Baptist; others say Elijah; and still others, Jeremiah or one of the prophets.”

15“But what about you?” he asked. “Who do you say I am?”

16Simon Peter answered, “You are the Messiah, the Son of the living God.”

17Jesus replied, “Blessed are you, Simon son of Jonah, for this was not revealed to you by flesh and blood, but by my Father in heaven. 18And I tell you that you are Peter,16:18 The Greek word for Peter means rock. and on this rock I will build my church, and the gates of Hades16:18 That is, the realm of the dead will not overcome it. 19I will give you the keys of the kingdom of heaven; whatever you bind on earth will be16:19 Or will have been bound in heaven, and whatever you loose on earth will be16:19 Or will have been loosed in heaven.” 20Then he ordered his disciples not to tell anyone that he was the Messiah.

Jesus Predicts His Death

21From that time on Jesus began to explain to his disciples that he must go to Jerusalem and suffer many things at the hands of the elders, the chief priests and the teachers of the law, and that he must be killed and on the third day be raised to life.

22Peter took him aside and began to rebuke him. “Never, Lord!” he said. “This shall never happen to you!”

23Jesus turned and said to Peter, “Get behind me, Satan! You are a stumbling block to me; you do not have in mind the concerns of God, but merely human concerns.”

24Then Jesus said to his disciples, “Whoever wants to be my disciple must deny themselves and take up their cross and follow me. 25For whoever wants to save their life16:25 The Greek word means either life or soul; also in verse 26. will lose it, but whoever loses their life for me will find it. 26What good will it be for someone to gain the whole world, yet forfeit their soul? Or what can anyone give in exchange for their soul? 27For the Son of Man is going to come in his Father’s glory with his angels, and then he will reward each person according to what they have done.

28“Truly I tell you, some who are standing here will not taste death before they see the Son of Man coming in his kingdom.”