ማርቆስ 11 – NASV & KJV

New Amharic Standard Version

ማርቆስ 11:1-33

ኢየሱስ በታላቅ ክብር ወደ ኢየሩሳሌም ገባ

11፥1-10 ተጓ ምብ – ማቴ 21፥1-9ሉቃ 19፥29-38

11፥7-10 ተጓ ምብ – ዮሐ 12፥12-15

1ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፤ 2“በፊታችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፣ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ የአህያ ውርንጫ እዚያ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈታችሁ አምጡት፤ 3ማንም፣ ‘ምን ማድረጋችሁ ነው?’ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤ በቶሎም መልሶ ይልከዋል’ ብላችሁ ንገሩት።”

4እነርሱም ሄዱ፤ በአንድ ቤት በራፍ መንገድ ላይ የአህያ ውርንጫ ታስሮ አገኙ፤ ፈቱትም። 5በዚያ ከቆሙት አንዳንድ ሰዎች፣ “ውርንጫውን የምትፈቱት ለምንድን ነው?” አሏቸው። 6ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ ያላቸውን ለሰዎቹ በነገሯቸው ጊዜ ፈቀዱላቸው። 7ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሳቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። 8ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ ለምለም የዛፍ ቅርንጫፍ እየቈረጡ ያነጥፉ ነበር። 9ከፊቱ የቀደሙትና ከኋላው የተከተሉትም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ይሉ ነበር፤

“ሆሣዕና!”11፥9 በዕብራይስጡ አድን! ማለት ሲሆን፣ ምስጋናን የሚገልጽ አባባል ነው፤ እንዲሁም 10 ይመ።

“በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!”

10“የምትመጣው የአባታችን የዳዊት መንግሥት የተባረከች ናት!”

“ሆሣዕና በአርያም!”

11ኢየሱስም ኢየሩሳሌም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ ተመለከተ፤ ቀኑም ስለ መሸ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ወጣ።

ኢየሱስ ቤተ መቅደስን አጸዳ

11፥12-14 ተጓ ምብ – ማቴ 21፥18-22

11፥15-18 ተጓ ምብ – ማቴ 21፥12-16ሉቃ 19፥45-47ዮሐ 2፥13-16

12በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጡ ኢየሱስ ተራበ።

13እርሱም ቅጠል ያላት የበለስ ዛፍ ከሩቅ አየ፤ ምናልባት ፍሬ ይገኝባት እንደ ሆነ ብሎ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን የበለስ ወራት አልነበረምና ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። 14ከዚያም ዛፏን፣ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ፍሬ ከአንቺ አይብላ” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ይህን ሲናገር ሰሙ።

15ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ፤ ከዚያም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ፣ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያስወጣ ጀመር። የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛና የርግብ ሻጮችን መቀመጫ ገለባበጠ፤ 16ማንም ዕቃ ተሸክሞ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳያልፍ ከለከለ። 17ሲያስተምራቸውም፣

“ ‘ቤቴ ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል’

ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት!” አላቸው።

18የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም፣ ይህን ሲሰሙ እንዴት እንደሚያጠፉት መንገድ ይፈልጉ ጀመር፤ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ በመገረማቸው ፈርተውታልና።

19በመሸም ጊዜ ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ11፥19 አንዳንድ ቅጆች ወጥቶ ሄደ ይላሉ።

የበለሷ ዛፍ ደረቀች

11፥20-24 ተጓ ምብ – ማቴ 21፥19-22

20በማግስቱም ጧት በመንገድ ሲያልፉ፣ በለሲቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ። 21ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፤ እነሆ፤ የረገምሃት በለስ ደርቃለች” አለው።

22ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “በእግዚአብሔር እመኑ11፥22 አንዳንድ የጥንት ቅጆች በእግዚአብሔር ላይ እምነት ካላችሁ ይላሉ።23እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና ይህንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል። 24ስለዚህ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደ ተቀበላችሁት አድርጋችሁ ብታምኑ ይሆንላችኋል። 25እንዲሁም ለጸሎት በምትቆሙበት ጊዜ፣ የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲልላችሁ፣ እናንተም በሰው ላይ ያላችሁን ሁሉ ይቅር በሉ። 26ይቅር ባትሉ ግን የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።11፥26 አንዳንድ ቅጆች 26 የላቸውም።

በኢየሱስ ሥልጣን ላይ ጥያቄ ተነሣ

11፥27-33 ተጓ ምብ – ማቴ 21፥23-27ሉቃ 20፥1-8

27እንደ ገና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚዘዋወርበት ጊዜ፣ የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ ቀርበው፣ 28“እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? እነዚህን እንድታደርግስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” አሉት።

29ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እስቲ እኔም አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፤ መልሱልኝ፤ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ። 30የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበረችን ወይስ ከሰው? መልሱልኝ።”

31እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “ ‘ከሰማይ ነው’ ብንል፣ ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 32‘ታዲያ፣ ከሰው ነው’ እንበልን?” ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስ እውነተኛ ነቢይ መሆኑን ያምኑ ስለ ነበር ፈሩ።

33ስለዚህ ለኢየሱስ “አናውቅም” ብለው መለሱለት።

ኢየሱስም፣ “እንግዲያው እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።

King James Version

Mark 11:1-33

1And when they came nigh to Jerusalem, unto Bethphage and Bethany, at the mount of Olives, he sendeth forth two of his disciples, 2And saith unto them, Go your way into the village over against you: and as soon as ye be entered into it, ye shall find a colt tied, whereon never man sat; loose him, and bring him. 3And if any man say unto you, Why do ye this? say ye that the Lord hath need of him; and straightway he will send him hither. 4And they went their way, and found the colt tied by the door without in a place where two ways met; and they loose him. 5And certain of them that stood there said unto them, What do ye, loosing the colt? 6And they said unto them even as Jesus had commanded: and they let them go. 7And they brought the colt to Jesus, and cast their garments on him; and he sat upon him. 8And many spread their garments in the way: and others cut down branches off the trees, and strawed them in the way. 9And they that went before, and they that followed, cried, saying, Hosanna; Blessed is he that cometh in the name of the Lord: 10Blessed be the kingdom of our father David, that cometh in the name of the Lord: Hosanna in the highest. 11And Jesus entered into Jerusalem, and into the temple: and when he had looked round about upon all things, and now the eventide was come, he went out unto Bethany with the twelve.

12¶ And on the morrow, when they were come from Bethany, he was hungry: 13And seeing a fig tree afar off having leaves, he came, if haply he might find any thing thereon: and when he came to it, he found nothing but leaves; for the time of figs was not yet. 14And Jesus answered and said unto it, No man eat fruit of thee hereafter for ever. And his disciples heard it.

15¶ And they come to Jerusalem: and Jesus went into the temple, and began to cast out them that sold and bought in the temple, and overthrew the tables of the moneychangers, and the seats of them that sold doves; 16And would not suffer that any man should carry any vessel through the temple. 17And he taught, saying unto them, Is it not written, My house shall be called of all nations the house of prayer? but ye have made it a den of thieves. 18And the scribes and chief priests heard it, and sought how they might destroy him: for they feared him, because all the people was astonished at his doctrine. 19And when even was come, he went out of the city.

20¶ And in the morning, as they passed by, they saw the fig tree dried up from the roots. 21And Peter calling to remembrance saith unto him, Master, behold, the fig tree which thou cursedst is withered away. 22And Jesus answering saith unto them, Have faith in God. 23For verily I say unto you, That whosoever shall say unto this mountain, Be thou removed, and be thou cast into the sea; and shall not doubt in his heart, but shall believe that those things which he saith shall come to pass; he shall have whatsoever he saith. 24Therefore I say unto you, What things soever ye desire, when ye pray, believe that ye receive them, and ye shall have them. 25And when ye stand praying, forgive, if ye have ought against any: that your Father also which is in heaven may forgive you your trespasses. 26But if ye do not forgive, neither will your Father which is in heaven forgive your trespasses.

27¶ And they come again to Jerusalem: and as he was walking in the temple, there come to him the chief priests, and the scribes, and the elders, 28And say unto him, By what authority doest thou these things? and who gave thee this authority to do these things? 29And Jesus answered and said unto them, I will also ask of you one question, and answer me, and I will tell you by what authority I do these things. 30The baptism of John, was it from heaven, or of men? answer me. 31And they reasoned with themselves, saying, If we shall say, From heaven; he will say, Why then did ye not believe him? 32But if we shall say, Of men; they feared the people: for all men counted John, that he was a prophet indeed. 33And they answered and said unto Jesus, We cannot tell. And Jesus answering saith unto them, Neither do I tell you by what authority I do these things.