ማሕልየ መሓልይ 5 – NASV & NIV

New Amharic Standard Version

ማሕልየ መሓልይ 5:1-16

ሙሽራው

1እኅቴ ሙሽራዬ፣ ወደ አትክልት ቦታዬ መጥቻለሁ፤

ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ፤

የማር እንጀራዬን ከነወለላው በልቻለሁ፤

ወይኔንና ወተቴንም ጠጥቻለሁ።

ባልንጀሮቿ

ወዳጆች ሆይ፤ ብሉ፤ ጠጡ፤

እናንት ፍቅረኞች ሆይ፤ እስክትረኩ ጠጡ።

ሙሽራዪቱ

2እኔ ተኝቻለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቷል፤

ስሙ! ውዴ በር ያንኳኳል፤ እንዲህ ይላል፤

“እኅቴ ወዳጄ፣ ርግቤ፣

አንቺ እንከን የሌለብሽ፤ ክፈቺልኝ።

ራሴ በጤዛ፣

ጠጕሬም በሌሊቱ ርጥበት ረስርሷል።”

3ቀሚሴን አውልቄአለሁ፤

ታዲያ እንዴት እንደ ገና ልልበስ?

እግሬን ታጥቤአለሁ፤

እንዴት እንደ ገና ላቈሽሸው?

4ውዴ እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾለከ፤

ልቤም ስለ እርሱ ይታወክ ጀመር።

5ለውዴ ልከፍትለት ተነሣሁ፤

በከርቤ ነጠብጣብ የራሱት እጆቼ፣

በከርቤም ፈሳሽ የተነከሩት ጣቶቼ፣

የመወርወሪያውን እጀታ ያዙ።

6ለውዴ ከፈትሁለት፤

ውዴ ግን አልነበረም፤ ሄዷል፤

በመሄዱም ልቤ ደነገጠ፤5፥6 ወይም በተናገረ ጊዜ ልቤ ወደ እርሱ ሄደ

ፈለግሁት፤ ነገር ግን አላገኘሁትም፤

ጠራሁት፤ ነገር ግን አልመለሰልኝም።

7የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣

በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤

እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣

ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤

ልብሴንም ገፈፉኝ።

8እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤

እማጠናችኋለሁ፤

ውዴን ካገኛችሁት፣

ምን ትሉት መሰላችሁ?

በፍቅሩ መታመሜን ንገሩት።

ባልንጀሮቿ

9አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተዋብሽ ሆይ፤

ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?

እስከዚህ የምትማጠኚንስ፣

ውድሽ ከሌሎች እንዴት ቢበልጥ ነው?

ሙሽራዪቱ

10ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤

ከዐሥር ሺሆችም የሚልቅ ነው።

11ራሱ የጠራ ወርቅ፣

ጠጕሩ ዞማ፣

እንደ ቍራም የጠቈረ ነው።

12ዐይኖቹ፣

በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣

በወተት የታጠቡ፣

እንደ ዕንቍም ጕብ ጕብ ያሉ ናቸው።

13ጕንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣

የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤

ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣

ውብ አበቦች ናቸው።

14ክንዶቹ በዕንፈርጥ ያጌጠ፣

የወርቅ ዘንግን ይመስላሉ፤

ሰውነቱም በሰንፔር ፈርጥ5፥14 ወይም ላፒስ ላዙሊ ያጌጠ፣

አምሮ የተሠራ የዝኆን ጥርስን ይመስላል።

15እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣

የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤

መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤

እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው።

16አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤

ሁለንተናውም ያማረ ነው።

እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤

ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው።

New International Version

Song of Songs 5:1-16

He

1I have come into my garden, my sister, my bride;

I have gathered my myrrh with my spice.

I have eaten my honeycomb and my honey;

I have drunk my wine and my milk.

Friends

Eat, friends, and drink;

drink your fill of love.

She

2I slept but my heart was awake.

Listen! My beloved is knocking:

“Open to me, my sister, my darling,

my dove, my flawless one.

My head is drenched with dew,

my hair with the dampness of the night.”

3I have taken off my robe—

must I put it on again?

I have washed my feet—

must I soil them again?

4My beloved thrust his hand through the latch-opening;

my heart began to pound for him.

5I arose to open for my beloved,

and my hands dripped with myrrh,

my fingers with flowing myrrh,

on the handles of the bolt.

6I opened for my beloved,

but my beloved had left; he was gone.

My heart sank at his departure.5:6 Or heart had gone out to him when he spoke

I looked for him but did not find him.

I called him but he did not answer.

7The watchmen found me

as they made their rounds in the city.

They beat me, they bruised me;

they took away my cloak,

those watchmen of the walls!

8Daughters of Jerusalem, I charge you—

if you find my beloved,

what will you tell him?

Tell him I am faint with love.

Friends

9How is your beloved better than others,

most beautiful of women?

How is your beloved better than others,

that you so charge us?

She

10My beloved is radiant and ruddy,

outstanding among ten thousand.

11His head is purest gold;

his hair is wavy

and black as a raven.

12His eyes are like doves

by the water streams,

washed in milk,

mounted like jewels.

13His cheeks are like beds of spice

yielding perfume.

His lips are like lilies

dripping with myrrh.

14His arms are rods of gold

set with topaz.

His body is like polished ivory

decorated with lapis lazuli.

15His legs are pillars of marble

set on bases of pure gold.

His appearance is like Lebanon,

choice as its cedars.

16His mouth is sweetness itself;

he is altogether lovely.

This is my beloved, this is my friend,

daughters of Jerusalem.