መዝሙር 95 – NASV & JCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 95:1-11

መዝሙር 95

የየዕለቱ መዝሙር

1ኑ፤ ደስ እያለን ለእግዚአብሔር እንዘምር፤

በድነታችንም ዐለት እልል እንበል።

2ምስጋና ይዘን ፊቱ እንቅረብ፤

በዝማሬም እናወድሰው።

3እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፤

ከአማልክትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው።

4የምድር ጥልቆች በእጁ ናቸው፤

የተራራ ጫፎችም የእርሱ ናቸው።

5እርሱ ፈጥሯታልና ባሕር የእርሱ ናት፤ እጁም የብስን አበጀ።

6ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤

በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤

7እርሱ አምላካችን ነውና፤

እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣

የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።

ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

8በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣95፥8 ማሳህ ፈተና ማለት ነው።

በመሪባም95፥8 መሪባ ጠብ ማለት ነው። እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።

9ሥራዬን ቢያዩም፣

አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።

10ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤

እኔም፣ “ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤

መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።

11ስለዚህ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብዬ፣

በቍጣዬ ማልሁ።

Japanese Contemporary Bible

詩篇 95:1-11

95

1さあ、主をたたえましょう。

救いの岩である神に向かって、

喜びの声を上げましょう。

2感謝の思いを込めて御前に近づき、

賛美の歌をささげましょう。

3主は、どんな神にもまさる偉大な王であられます。

4主は地中深いところも、そびえ立つ高い山々も、

支配しておられます。

すべてのものは主のものです。

5主は海と陸をお造りになりました。

それらは主のものです。

6さあ、創造主である主の前に出て、

ひざまずきましょう。

7私たちは神の羊であり、神は羊飼いなのです。

今日、呼びかけられる声を聞いたなら、

神のもとへ行きましょう。

8荒野のメリバやマサでのイスラエル国民のように、

強情になってはいけません(出エジプト17・7参照)。

9あの時、あなたがたの先祖は、

わたしの奇跡を何度も目にしながら、

信じようとしなかった。

わたしがどこまで忍耐するかを試そうとするように、

彼らは不平やぐちを言い続けた。

10「この四十年間、

わたしは苦々しい思いで民を見すえてきた。

心も思いも遠く離れているこの民は、

わたしのおきてに見向きもしなかった。

11だから、わたしは激しい怒りを込めて誓った。

彼らに約束した安息の地へ、

彼らが入ることは決してない。」