መዝሙር 88 – NASV & NAV

New Amharic Standard Version

መዝሙር 88:1-18

መዝሙር 88

ሰቈቃ

ማሕሌት፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት የሚዘመር፤ የይዝራኤላዊው የኤማን ትምህርት።

1አዳኜ የሆንህ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤

በቀንና በሌሊት በፊትህ እጮኻለሁ።

2ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤

ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፤

3ነፍሴ በመከራ ተሞልታለችና፤

ሕይወቴም ወደ ሲኦል88፥3 መቃብር የሚሉ አሉ። ተቃርባለች።

4ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱት ጋር ተቈጠርሁ፤

ዐቅምም ዐጣሁ።

5በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣

ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣

አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣

ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ።

6በዐዘቅት ጥልቀት ውስጥ ጣልኸኝ፤

በጨለማ ጕድጓድ ውስጥ ከተትኸኝ።

7የቍጣህ ክብደት በላዬ ዐርፏል፤

በማዕበልህም ሁሉ አጥለቅልቀኸኛል። ሴላ

8የሚቀርቡኝ ባልንጀሮቼን ከእኔ አራቅህ፤

እንዲጸየፉኝም አደረግህ፤

ተከብቤአለሁ፤ ማምለጥም አልችልም፤

9ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ።

እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤

እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።

10ድንቅ ሥራህን ለሙታን ታሳያለህን?

የሙታንስ መናፍስት ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? ሴላ

11ምሕረትህ በመቃብር ውስጥ፣

ታማኝነትህስ እንጦርጦስ88፥11 በዕብራይስጥ አባዶን ማለት ነው፤ የመውደሚያ ስፍራ ነው። ይነገራልን?

12ድንቅ ሥራህ በጨለማ ስፍራ፣

ጽድቅህስ በመረሳት ምድር ትታወቃለችን?

13እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤

በጧትም ጸሎቴን በፊትህ አደርሳለሁ።

14እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምን ታርቀኛለህ?

ፊትህንስ ከእኔ ለምን ትሰውራለህ?

15እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ችግረኛና ለሞት የተቃረብሁ ነበርሁ፤

መዓትህ አሠቃየኝ፤ ግራም ተጋባሁ።

16ቍጣህ በላዬ ላይ ተከነበለ፤

መዓትህም አጠፋኝ።

17ቀኑን ሙሉ እንደ ጐርፍ ከበቡኝ፤

በአንድነትም ዙሪያዬን ዐጥረው ያዙኝ።

18ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤

ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።

Ketab El Hayat

مزمور 88:1-18

الْمَزْمُورُ الثَّامِنُ وَالثَّمَانُونَ

تَسْبِيحَةٌ: مَزْمُورٌ لِبَنِي قُورَحَ. لِقَائِدِ الْمُنْشِدِينَ عَلَى النَّايِ الْحَزِينِ لِلْغِنَاءِ الْخَافِتِ. قَصِيدَةٌ تَعْلِيمِيَّةٌ لِهَيْمَانَ الأَزْرَاحِيِّ

1يَا رَبُّ يَا إِلَهَ خَلاصِي، أَمَامَكَ أَصْرُخُ نَهَاراً وَلَيْلاً. 2لِتَأْتِ صَلاتِي أَمَامَكَ، أَمِلْ أُذُنَكَ إِلَى صَرْخَتِي، 3فَإِنَّ نَفْسِي شَبِعَتْ مَصَائِبَ، وَحَيَاتِي تَقْتَرِبُ مِنَ الْمَوْتِ. 4حُسِبْتُ فِي عِدَادِ الْهَابِطِينَ إِلَى قَعْرِ هُوَّةِ الْمَوْتِ، وَكَرَجُلٍ لَا قُوَّةَ لَهُ. 5تَرَكُونِي أَمُوتُ كَقَتْلَى الْحَرْبِ الْمُمَدَّدِينَ فِي الْقَبْرِ، الَّذِينَ لَا تَعُودُ تَذْكُرُهُمْ وَتَكُفُّ يَدَكَ عَنْ إِغَاثَتِهِمْ. 6قَدْ طَرَحْتَنِي فِي الْهُوَّةِ السُّفْلَى، فِي الأَمَاكِنِ الْمُظْلِمَةِ وَالْعَمِيقَةِ. 7اسْتَقَرَّ علَيَّ غَضَبُكَ، وَبِأَمْوَاجِكَ الطَّامِيَةِ ذَلَّلْتَنِي. 8أَبْعَدْتَ عَنِّي أَصْحَابِي، وَجَعَلْتَنِي عَاراً عِنْدَهُمْ. قَدْ حُبِسْتُ فَلَا نَجَاةَ لِي. 9كَلَّتْ عَيْنَايَ مِنْ فَرْطِ البُكَاءِ. إِيَّاكَ يَا رَبُّ دَعَوْتُ كُلَّ يَوْمٍ بَاسِطاً إِلَيْكَ يَدَيَّ.

10هَلْ تَصْنَعُ عَجَائِبَ لِلأَمْوَاتِ، أَمْ تَقُومُ أَشْبَاحُ الْمَوْتَى فَتُمَجِّدَكَ؟ 11أَفِي الْقَبْرِ تُعْلَنُ رَحْمَتُكَ، وَفِي الْهَاوِيَةِ أَمَانَتُكَ؟ 12هَلْ فِي الظَّلامِ تُعْرَفُ عَجَائِبُكَ، وَفِي أَرْضِ النِّسْيَانِ يَظْهَرُ بِرُّكَ؟

13أَمَّا أَنَا فَإِلَيْكَ أَصْرُخُ مُسْتَغِيثاً يَا رَبُّ، وَفِي الصَّبَاحِ تَمْثُلُ صَلاتِي أَمَامَكَ. 14لِمَاذَا يَا رَبُّ تَرْفُضُ نَفْسِي، وَتَحْجُبُ عَنِّي وَجْهَكَ؟ 15إِنَّنِي مِسْكِينٌ، وَمُشْرِفٌ عَلَى الْمَوْتِ مُنْذُ صِبَايَ، وَقَدْ قَاسَيْتُ أَهْوَالَكَ، وَذُهِلْتُ. 16اجْتَاحَنِي غَضَبُكَ الشَّدِيدُ وَأَفْنَتْنِي أَهْوَالُكَ. 17أَحَاطَتْ بِي طُولَ النَّهَارِ كَالْمِيَاهِ وَأَطْبَقَتْ عَلَيَّ كُلُّهَا. 18فَرَّقْتَ عَنِّي الأَصْدِقَاءَ فَصَارَ الظَّلامُ مُلازِماً لِي.