መዝሙር 87 – NASV & PCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 87:1-7

መዝሙር 87

ጽዮን የሕዝቦች እናት

የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ ማሕሌት።

1መሠረቱን በተቀደሱ ተራሮች አቆመ፤

2እግዚአብሔር ከያዕቆብ ማደሪያዎች ሁሉ ይልቅ፣

የጽዮንን ደጆች ይወድዳል።

3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፤

ስለ አንቺ ክቡር የሆነ ነገር እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ ሴላ

4“ከሚያውቁኝ መካከል፣

ረዓብንና87፥4 የግብፅ ቅኔያዊ ስያሜ ነው። ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤

እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋር፣87፥4 ወይም ረዓብ ባቢሎን፣ ፍልስጥኤምና ኢትዮጵያ

‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”

5በርግጥም ስለ ጽዮን፣

“ይህም ያም ሰው በእርሷ ውስጥ ተወለዱ፤

ልዑልም ራሱ ያጸናታል” ይባላል።

6እግዚአብሔር ሕዝቡን ሲመዘግብ፣

“ይህ ሰው የተወለደው በዚያ ነው” ብሎ ይጽፋል። ሴላ

7የሚያዜሙም መሣሪያ የሚጫወቱም፣

“ምንጩ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛል” ይላሉ።

Persian Contemporary Bible

مزامير 87:1-7

تمجيد از اورشليم

1اورشليم بر کوههای مقدس بنا شده است. 2خداوند آن را بيش از ساير شهرهای اسرائيل دوست دارد. 3ای شهر خدا، به سخنانی كه خدا دربارهٔ تو گفته است گوش كن:

4«فلسطين و صور و حبشه به تو، ای اورشليم، تعلق دارند و مصر و بابل جزو ممالكی می‌باشند كه مرا می‌شناسند.»

5دربارهٔ اورشليم خواهند گفت كه تمام قومهای دنيا به آن تعلق دارند و اينكه خدای قادر متعال اورشليم را قوی خواهد ساخت. 6هنگامی كه خداوند اسامی قومها را ثبت نمايد، همهٔ آنها را به اورشليم نسبت خواهد داد. 7آن قومها سرودخوانان و رقص كنان خواهند گفت: «اورشليم سرچشمهٔ همهٔ بركات و خوشيهای ماست!»