መዝሙር 85 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 85:1-13

መዝሙር 85

ስለ ሰላም የቀረበ ጸሎት

ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ ለምድርህ በጎ ውለሃል፤

የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።

2የሕዝብህን በደል ይቅር አልህ፤

ኀጢአታቸውንም ሁሉ ሸፈንህ። ሴላ

3መዓትህን ሁሉ አራቅህ፤

ከብርቱ ቍጣህም ተመለስህ።

4መድኀኒታችን የሆንህ አምላክ ሆይ፤ መልሰን፤

በእኛ ላይ የተቃጣውን ቍጣህን መልሰው።

5የምትቈጣን ለዘላለም ነውን?

ቍጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?

6ሕዝብህ በአንተ ሐሤት ያደርግ ዘንድ፣

መልሰህ ሕያዋን አታደርገንምን?

7እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህን አሳየን፤

ማዳንህን ለግሰን።

8እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤

ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤

ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።

9ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣

ማዳኑ ለሚፈሩት በርግጥ ቅርብ ነው።

10ምሕረትና ታማኝነት ተገናኙ፤

ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።

11ታማኝነት ከምድር በቀለች፤

ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች።

12እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።

13ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤

ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 85:1-13

第 85 篇

為國家求福

可拉後裔的詩,交給樂長。

1耶和華啊,你賜福了你的土地,

使雅各的子孫重返家園。

2你赦免了你子民的罪過,

遮蓋了他們所有的過犯。(細拉)

3你收回自己的怒氣,

不發烈怒。

4拯救我們的上帝啊,

求你復興我們,

止息你對我們的怒氣。

5你要向我們永遠發怒嗎?

你的怒氣要延續到萬代嗎?

6你不再復興我們,

使你的子民靠你歡喜嗎?

7耶和華啊,求你向我們施慈愛,拯救我們。

8我要聽耶和華上帝所說的話,

因為祂應許賜平安給祂忠心的子民。

但我們不可再犯罪。

9祂拯救敬畏祂的人,

好讓祂的榮耀常駐在我們的地上。

10慈愛和忠信同行,

公義與平安相親。

11忠信從地而生,

公義從天而現。

12耶和華賜下祝福,

我們的土地就出產豐富。

13公義要行在祂面前,為祂開路。