መዝሙር 54 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 54:1-7

መዝሙር 54

ለፍትሕ አምላክ የቀረበ አቤቱታ

ለመዘምራን አለቃ፤ በበገናዎች፤ ዜፋውያን ወደ ሳኦል መጥተው፣ “ዳዊት በእኛ ዘንድ ተደብቋል” ባሉት ጊዜ፤ የዳዊት ትምህርት54 ርእሱ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ ወይም የመዝሙሩን ሁኔታ የሚያሳይ ሊሆን ይችላል።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በስምህ አድነኝ፤

በኀይልህም ፍረድልኝ።

2እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማልኝ፤

የአፌንም ቃል አድምጥ።

3ባዕዳን ተነሥተውብኛልና፤

ግፈኞች ነፍሴን ሽተዋታል፤

እግዚአብሔርንም ከምንም አልቈጠሩም። ሴላ

4እነሆ፤ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፤

ጌታም ደግፎ ይይዘኛል።

5የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤

በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው።

6በበጎ ፈቃድ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ መልካም ነውና፣

ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤

7ከመከራ ሁሉ ታድጎኛልና፤

ዐይኔም የጠላቶቼን ውድቀት ለማየት በቅቷል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 54:1-7

第 54 篇

祈求上帝的拯救

西弗人去告訴掃羅:「大衛藏在我們那裡」,那時大衛作了這首訓誨詩,交給樂長,用弦樂器。

1上帝啊,

求你憑你的名拯救我!

求你用你的大能為我伸冤!

2上帝啊,求你垂聽我的禱告,

留心我口中的話。

3因為傲慢的人起來攻擊我,

目無上帝的暴徒正尋索我的性命。(細拉)

4看啊,上帝幫助我,主扶持我,

5祂必使我的仇敵自作自受。

信實的上帝啊,

求你毀滅他們。

6耶和華啊,

我甘心樂意獻上祭物,

我要讚美你的名,

因為你的名是美善的。

7你拯救我脫離一切艱難,

讓我傲視仇敵。