መዝሙር 48 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

መዝሙር 48:1-14

መዝሙር 48

የእግዚአብሔር ተራራ ጽዮን

ዝማሬ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።

1እግዚአብሔር ታላቅ ነው፤

በአምላካችን ከተማ በተቀደሰው ተራራ ከፍ ያለ ምስጋና ይገባዋል።

2የምድር ሁሉ ደስታ የሆነው፣

በሰሜን በኩል48፥2 ጻፎን የሚለው የዕብራይስጡ ቃል የተቀደሰ ተራራን ወይም የሰሜንን አቅጣጫ ሊያመለክት ይችላል። በርቀት የሚታየው፣

በከፍታ ላይ አምሮ የደመቀው የጽዮን ተራራ፣

የታላቁ ንጉሥ ከተማ ነው።

3እግዚአብሔር በአዳራሾቿ ውስጥ ሆኖ፤

ብርቱ ምሽግ እንደ ሆናት አስመስክሯል።

4እነሆ፤ ነገሥታት ተባብረው መጡ፤

አንድ ላይ ሆነውም ገሠገሡ።

5አይተውም ተደነቁ፤

ደንግጠውም ፈረጠጡ።

6ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣

በዚያ ብርክ ያዛቸው።

7የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣

አንተ አብረከረክሃቸው።

8እንደ ሰማን፣

በሰራዊት አምላክ ከተማ፣

በአምላካችን ከተማ፣

እንዲሁ አየን፤

እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ

9አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣

ምሕረትህን እናስባለን።

10አምላክ ሆይ፤ ምስጋናህ እንደ ስምህ፣

እስከ ምድር ዳርቻ ይዘልቃል፤

ቀኝ እጅህም ጽድቅን የተሞላች ናት።

11ስለ ፍርድህ፣

የጽዮን ተራራ ሐሤት ታድርግ፤

የይሁዳ መንደሮችም ደስ ይበላቸው።

12በጽዮን አካባቢ ተመላለሱ፤ ዙሪያዋንም ሂዱ፤

የጥበቃ ግንቦቿንም ቍጠሩ፤

13ለሚቀጥለው ትውልድ ትናገሩ ዘንድ፣

መከላከያ ዕርዶቿን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤

መጠበቂያ ማማዎቿን እዩ።

14ይህ አምላክ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላካችን ነውና፤

እስከ መጨረሻው የሚመራንም እርሱ ነው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

诗篇 48:1-14

第 48 篇

上帝的城——锡安

可拉后裔的诗。

1耶和华何等伟大!

我们的上帝在祂的城中,

在祂的圣山上当大受颂赞。

2北面的锡安山雄伟壮丽,

令世人欢喜,

是伟大君王的城。

3上帝在城内的宫中,

祂亲自做这城的庇护。

4世上的君王一同聚集,前来攻城。

5他们看见这城后,

大惊失色,慌忙逃跑。

6他们被恐惧笼罩,

痛苦如分娩的妇人。

7你毁灭他们,

如同东风摧毁他施的船只。

8我们曾经听说,如今在万军之耶和华的城中,

在我们上帝的城中亲眼看见:

上帝要坚立这城,直到永远。(细拉)

9上帝啊,我们在你的殿中默想你的慈爱。

10上帝啊,你秉公行义,

你的名普世皆知,

颂赞你的声音响彻地极。

11因你的审判,

锡安山欢喜,

犹大的城邑充满快乐。

12你们要绕着锡安数点她的城楼,

13留意她的城墙,

观看她的殿宇,

好告诉子孙后代。

14因为上帝永永远远是我们的上帝,

祂必引领我们,

直到我们离世之日。