መዝሙር 43 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

መዝሙር 43:1-5

መዝሙር 4343 በብዙ የዕብራይስጥ ቅጆች መዝሙር 42 እና 43 አንድ መዝሙር ነው።

በስደት ላይ ያለ ሌዋዊ ልቅሶ

1አምላክ ሆይ፤ ፍረድልኝ፤

ከጽድቅ ከራቀ ሕዝብ ጋር ተሟገትልኝ፤

ከአታላዮችና ከክፉዎች ሰዎችም አድነኝ።

2አምላክ ሆይ፤ አንተ ብርታቴ ነህና፣

ለምን ተውኸኝ?

ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣

ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?

3ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፤

እነርሱ ይምሩኝ፤

ወደ ተቀደሰው ተራራህ፣

ወደ ማደሪያህ ያድርሱኝ።

4እኔም ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ አቀናለሁ፤

ፍጹም ደስታዬ ወደ ሆነው አምላክ እሄዳለሁ፤

እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣

በበገና አመሰግንሃለሁ።

5ነፍሴ ሆይ፤ ለምን ትተክዢያለሽ?

ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ?

ተስፋሽን በአምላክ ላይ አድርጊ፤

አዳኜና አምላኬን፣

ገና አመሰግነዋለሁና።