መዝሙር 37 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 37:1-40

መዝሙር 3737 የዚህ መዝሙር እያንዳንዱ ጥቅስ ተከታታይ ፊደላት ባሉት የዕብራይስጥ ሆህያት የሚጀምር ሲሆን፣ ጅማሬው ወይም ጅማሬውና መጨረሻው ትርጕም የሚሰጥ ግጥም ነው።

የጻድቁና የክፉው ዕጣ ፈንታ

የዳዊት መዝሙር።

1ዐመፀኞችን በማየት አትሸበር፤

በክፉ አድራጊዎችም አትቅና፤

2እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፤

እንደ ለምለም ቅጠልም ይጠወልጋሉ።

3በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤

በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ።

4በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤

የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።

5መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤

በእርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤

6ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣

ያንተን ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።

7በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤

በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤

መንገዱ በተቃናለት፣

ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።

8ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤

ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።

9ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤

እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።

10ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤

ስፍራውንም ብታሥሥ አታገኘውም።

11ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤

በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

12ክፉዎች በጻድቃን ላይ ያሤራሉ፤

ጥርሳቸውንም ያፋጩባቸዋል።

13እግዚአብሔር ግን ይሥቅባቸዋል፣

ቀናቸው እንደ ደረሰ ያውቃልና።

14ድኾችንና ችግረኞችን ለመጣል፣

አካሄዳቸው ቀና የሆነውንም ለመግደል፣

ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፤

ቀስታቸውንም ገተሩ።

15ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤

ቀስታቸውም ይሰበራል።

16የጻድቅ ጥቂት ሀብት፣

ከክፉዎች ብዙ ጥሪት ይበልጣል።

17የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፣

ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል።

18እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤

ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።

19በክፉ ጊዜ ዐንገት አይደፉም፤

በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።

20ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤

የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይሆናሉ፤

ይጠፋሉ፤ እንደ ጢስም ተነው ይጠፋሉ።

21ኀጢአተኛ ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤

ጻድቅ ግን ይቸራል።

22እግዚአብሔር የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤

እርሱ የሚረግማቸው ግን ይጠፋሉ።

23የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤

በመንገዱ ደስ ይለዋል።

24ቢሰናከልም አይወድቅም፣

እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።

25ጕልማሳ ነበርሁ፤ አሁን አርጅቻለሁ፤

ነገር ግን ጻድቅ ሲጣል፣

ዘሩም እንጀራ ሲለምን አላየሁም።

26ሁልጊዜ ቸር ነው፤ ያበድራልም፤

ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ።

27ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፣

ለዘላለምም ትኖራለህ።

28እግዚአብሔር ፍትሕን ይወድዳልና፣

ታማኞቹንም አይጥልም፤

ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤

የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።

29ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤

በእርሷም ለዘላለም ይኖራሉ።

30የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤

አንደበቱም ፍትሐዊ ነገር ያወራል።

31የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤

አካሄዱም አይወላገድም።

32ክፉዎች ጻድቁን ይከታተሉታል፤

ሊገድሉትም ይሻሉ።

33እግዚአብሔር ግን በእጃቸው አይጥለውም፤

ፍርድ ፊት ሲቀርብም አሳልፎ አይሰጠውም።

34እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፤

መንገዱንም ጠብቅ፤

ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤

ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።

35ክፉና ጨካኙን ሰው፣

እንደ ሊባኖስ ዝግባ ለምልሞ አየሁት፤

36ዳግመኛ በዚያ ሳልፍ፣ እነሆ፣ በቦታው አልነበረም፤

ብፈልገውም አልተገኘም።

37ንጹሓንን ልብ በል፤ ቅኑንም አስተውል፤

የሰላም ሰው ተስፋ አለውና።37፥37 ወይም ዘር ይወጣለታል

38ኀጢአተኞች ግን በአንድነት ይጠፋሉ፤

የክፉዎችም ዘር37፥38 ወይም ትውልድ ይወገዳል።

39የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤

በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው።

40እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፤

ይታደጋቸዋልም፤

ከክፉዎች እጅ ነጥቆ ያወጣቸዋል፤

እርሱን መጠጊያ አድርገዋልና ያድናቸዋል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 37:1-40

第 37 篇

義人和惡人的結局

大衛的詩。

1不要因為惡人而煩惱,

也不要羡慕作惡之人,

2因為他們如瞬息枯萎的草芥,

又如轉眼消逝的綠草。

3要信靠耶和華,要行善,

要在這片土地上安然度日。

4要以耶和華為樂,

祂必成全你的願望。

5要把一切交托給耶和華,

信靠祂,祂必幫助你,

6使你的公義如晨光照耀,

你的仁義如日中天。

7要在耶和華面前安靜,

耐心等候祂,

不要因惡人道路通達、陰謀得逞而憤憤不平。

8你要抑制怒氣,除掉憤怒;

不要心懷不平,

那會導致你作惡。

9因為作惡的終必滅亡,

但等候耶和華的必承受土地。

10再過片刻,惡人必不復存在,

無處可尋。

11但謙卑人必承受土地,

得享太平。

12惡人謀害義人,

對他們咬牙切齒。

13但耶和華嗤笑邪惡人,

因為祂知道他們末日將臨。

14惡人拔劍張弓要消滅窮苦人,

殺戮正直人,

15但他們的劍必刺穿自己的心,

他們的弓必被折斷。

16義人淡泊一生強過惡人財富如山。

17因為惡人的勢力終必瓦解,

耶和華必扶持義人。

18耶和華天天看顧純全無過的人,

他們的產業永遠長存。

19他們在災難中不致絕望,

在饑荒時仍得飽足。

20但惡人必滅亡,

上帝的仇敵必像野地枯萎的花草,

消逝如煙。

21惡人借債不還,

義人慷慨給予。

22蒙耶和華賜福的人必承受土地,

被耶和華咒詛的人必遭剷除。

23耶和華引領義人的腳步,

喜悅他們所走的路。

24他們即使失腳,也不會跌倒,

因為耶和華的手扶持他們。

25從幼年到老年,

我從未見過義人遭棄,

也未見其後人討飯。

26他們樂善好施,

後代都蒙祝福。

27你要離惡行善,

就必永遠安居。

28因為耶和華喜愛正義,

不丟棄信靠祂的人,

永遠保護他們。

惡人的後代必被剷除。

29義人必承受土地,

在地上永遠安居。

30義人口出智慧,訴說正義,

31銘記上帝的律法,

從不失腳。

32惡人窺探義人,

伺機謀害。

33但耶和華不會讓惡人得逞,

也不會讓義人在審判時被定罪。

34要等候耶和華,

堅守祂的道,

祂必賜你土地,使你有尊榮。

你必親眼看見惡人被剷除。

35我見過邪惡殘暴之人,

乍看如蔥蘢的黎巴嫩香柏樹,

36再一看,

他已經消失得無影無蹤,

無處可尋。

37你看那純全正直、愛好和平的人,

他們前途美好。

38罪人必遭毀滅,

惡人必被剷除。

39耶和華拯救義人,

患難時作他們的庇護所。

40耶和華幫助他們,

拯救他們脫離惡人,

因為他們投靠祂。