መዝሙር 25 – NASV & CARS

New Amharic Standard Version

መዝሙር 25:1-22

መዝሙር 2525 ይህ መዝሙር እያንዳንዱ ጥቅስ ተከታታይ ፊደላት ባሉት የዕብራይስጥ ሆህያት የሚጀምር፣ ጅማሬው ወይም ጅማሬውና መጨረሻው ትርጕም የሚሰጥ ግጥም ነው።

በዐደጋ ጊዜ የቀረበ ጸሎት

የዳዊት መዝሙር።

1እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁ፤

2አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤

እባክህ አታሳፍረኝ፤

ጠላቶቼም አይዘባነኑብኝ።

3አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣

ከቶ አያፍሩም፤

ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣

ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤

መንገድህንም አስተምረኝ።

5አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣

በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤

ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።

6እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን ዐስብ፤

እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና።

7የልጅነቴን ኀጢአት፣

መተላለፌንም አታስብብኝ፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣

እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ።

8እግዚአብሔር መልካምና ቅን ነው፤

ስለዚህ ኀጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።

9ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤

ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።

10ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ፣

የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው።

11እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣

ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።

12እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው?

በተመረጠለት መንገድ ያስተምረዋል።

13ዘመኑን በተድላ ደስታ ያሳልፋል፤

ዘሩም ምድርን ይወርሳል።

14እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤

ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል።

15ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው፤

እግሮቼን ከወጥመድ የሚያላቅቃቸው እርሱ ነውና።

16እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ እንደ መሆኔ፣

ወደ እኔ ተመለስ፤ ምሕረትም አድርግልኝ።

17የልቤ መከራ በዝቷል፤

ከጭንቀቴ ገላግለኝ።

18ጭንቀቴንና መከራዬን ተመልከት፤

ኀጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።

19ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤

እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።

20ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤

መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።

21አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣

ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።

22አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን

ከመከራው ሁሉ አድነው።

Священное Писание

Забур 25:1-12

Песнь 25

Песнь Давуда.

1Вечный, оправдай меня,

ведь я жил непорочной жизнью.

Я уповал на Вечного,

не колеблясь.

2Проверь меня, Вечный, испытай меня,

исследуй сердце моё и разум.

3Ведь Твоя милость всегда предо мной;

я всегда пребываю в Твоей истине.

4Я не сижу с людьми лживыми

и с коварными не хожу.

5Я ненавижу сборище грешников

и с нечестивыми не сажусь.

6Буду омывать свои руки в невинности

и кругом обходить Твой жертвенник, о Вечный,

7вознося Тебе хвалу

и говоря о всех чудесах Твоих.

8Вечный, я люблю дом, в котором Ты обитаешь,

место, где слава Твоя живёт.

9Не погуби души моей с грешными,

жизни моей с кровожадными,

10которые творят злодеяния,

чьи правые руки полны взяток.

11А я живу беспорочно.

Избавь меня и помилуй!

12Ноги мои стоят на ровной земле;

в большом собрании восхвалю я Вечного.