መዝሙር 22 – NASV & NRT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 22:1-31

መዝሙር 22

የጻድቅ ሰው መከራና ተስፋ

ለመዘምራን አለቃ፤ “በንጋት አጋዘን” ዜማ የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር።

1አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?

እኔን ከማዳን፣

ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?

2አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ ጮኻለሁ፤

አንተ ግን አልመለስህልኝም፤

በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

3አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤22፥3 ወይም አንተ ግን ቅዱስ ነህ፤ በእስራኤል ምስጋና ላይ በዙፋን ተቀምጠሃል

የእስራኤልም ምስጋና ነህ።

4አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤

ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።

5ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤

በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።

6እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤

ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።

7የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤

ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤

8በእግዚአብሔር ተማምኗል፤

እንግዲህ እርሱ ያድነው፤

ደስ የተሰኘበትን፣

እስቲ ይታደገው።”

9አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤

በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።

10ከማሕፀን ስወጣም በአንተ ላይ ተጣልሁ፤

ከእናቴ ሆድ ጀምሮም አንተ አምላኬ ነህ።

11መከራ እየተቃረበ ነውና፣

የሚረዳኝም የለምና፣

ከእኔ አትራቅ።

12ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤

ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።

13እንደሚነጥቅና እንደሚያገሣ አንበሳ፣

አፋቸውን ከፈቱብኝ።

14እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤

ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤

ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤

በውስጤም ቀለጠ።

15ጕልበቴ እንደ ገል ደረቀ፤

ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣበቀ፤

ወደ ሞት ዐፈርም አወረድኸኝ።22፥15 ወይም …ዐፈር ውስጥ ተኛሁኝ

16ውሾች ከበቡኝ፤

የክፉዎች ሸንጎ በዙሪያዬ ተሰልፏል፤

እጆቼንና እግሮቼንም ቸነከሩኝ።22፥16 አንዳንድ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች፣ ሰብዓ ሊቃናትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ የጥንት ቅጆች እንደ አንበሳ ይላሉ።

17ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤

እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።

18ልብሶቼን ተከፋፈሉ፤

በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።

19አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ፤

ዐጋዤ ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

20ነፍሴን ከሰይፍ ታደጋት፤

ውድ ሕይወቴንም ከውሾች ጡጫ አድናት።

21ከአንበሶች አፍ አድነኝ፤

ከአውራሪስ ቀንድም ታደገኝ።22፥21 ወይም ሰምተኸኛል

22ስምህን ለወንድሞቼ እነግራለሁ፤

በጉባኤም መካከል አመሰግንሃለሁ።

23እናንተ እግዚአብሔርን የምትፈሩ፤

አወድሱት፤

እናንተ የያቆብ ዘር ሁላችሁ፤ አክብሩት፤

የእስራኤልም ዘር ሁላችሁ፤ እርሱን ፍሩት።

24እርሱ የተጨነቀውን ሰው ጭንቀት፣

አልናቀም፤ ቸልም አላለምና፤

ፊቱንም ከእርሱ አልሰወረም፤

ነገር ግን ድረስልኝ ብሎ ሲጮኽ ሰማው።

25በታላቅ ጉባኤ የማቀርበው ምስጋናዬ ከአንተ የመጣ ነው፤

እርሱን በሚፈሩት22፥25 ዕብራይስጡ እኔ በሚፈሩኝ ይላል። ፊት ስእለቴን እፈጽማለሁ።

26ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤

እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤

ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!

27የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤

ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤

የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣

በፊቱ ይሰግዳሉ።

28መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤

ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው።

29የምድር ከበርቴዎች ይበላሉ፤

ይሰግዱለታልም፤

ነፍሱን በሕይወት ማቈየት የማይችለው፣ ወደ ዐፈር

ተመላሽ የሆነው ሁሉ በፊቱ ይንበረከካል።

30የኋለኛው ትውልድ ያገለግለዋል፤

ለመጪው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል።

31ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣

ጽድቁን ይነግራሉ፤

እርሱ ይህን አድርጓልና።

New Russian Translation

Псалтирь 22:1-6

Псалом 22

1Псалом Давида.

Господь – Пастырь мой;

я ни в чем не буду нуждаться.

2Он покоит меня на зеленых пастбищах

и водит меня к тихим водам.

3Он душу мою оживляет

и ведет меня по путям праведности

ради имени Своего.

4Пусть пойду в темноте долины смерти,

не устрашусь я зла,

потому что Ты со мной;

Твой жезл и Твой посох –

они успокаивают меня.

5Ты приготовил мне пир

на виду у моих врагов,

умастил мне голову маслом,

и чаша моя полна.

6Так, благо и милость да будут со мною

все дни моей жизни,

и пребуду я в доме Господнем многие дни.