መዝሙር 138 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 138:1-8

መዝሙር 138

የምስጋና መዝሙር

የዳዊት መዝሙር።

1እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤

በአማልክት ፊት በመዝሙር አወድስሃለሁ።

2ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤

ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣

ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤

ስምህንና ቃልህን፣

ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

3በጠራሁህ ቀን መልስ ሰጠኸኝ፤

ነፍሴን በማደፋፈርም ብርቱ አደረግኸኝ።

4እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፍህን ቃል በሰሙ ጊዜ፣

የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመስግኑህ።

5የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና፣

ስለ እግዚአብሔር መንገድ ይዘምሩ።

6እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤

ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል።

7በመከራ መካከል ብሄድም፣

አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤

በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤

በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ።

8እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለውን ዐላማ ይፈጽማል፤

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ለዘላለም ነው።

የእጅህንም ሥራ ቸል አትበል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 138:1-8

第 138 篇

感恩的禱告

大衛的詩。

1耶和華啊,

我全心全意地稱謝你,

在眾神明面前歌頌你。

2我要向你的聖殿下拜,

稱謝你的名,

因為你是慈愛信實的,

你顯明自己的尊名和應許偉大無比。

3我禱告的時候,你就應允我;

你使我剛強壯膽。

4耶和華啊,世上所有的君王聽見你的話都要稱謝你。

5他們要歌唱耶和華的作為,

因為耶和華榮耀無比。

6耶和華雖在高天之上,

仍看顧卑微的人,

祂對驕傲的人也瞭若指掌。

7耶和華啊,雖然我身陷患難,

你必保護我的性命,

伸手攻擊惱怒的仇敵,

用右手拯救我。

8耶和華必成就祂為我所定的計劃;

耶和華啊,你的慈愛永遠長存。

求你不要撇棄你親手所造的。