Loading…
መዝሙር 131
በእግዚአብሔር መታመን
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ።
1እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ አልታበየም፤
ዐይኔ ከፍ ከፍ አላለም፤
ሐሳቤ ለዐጕል ትልቅነት አልተነሣሣም፤
ከዐቅሜም በላይ አልተንጠራራሁም።
2ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሰኘኋት፤
ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣
ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።
3እስራኤል ሆይ፤ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣
በእግዚአብሔር ተስፋ አድርግ።
어린아이와 같은 신뢰
(다윗의 시. 성전에 올라가는 노래)
1여호와여,
나는 교만하거나
거만하지 않으며
나에게 과분한 일이나
내가 감당할 수 없는 일을
생각하지 않습니다.
2오히려 내 마음이
고요하고 평온하니
젖 뗀 아기가 자기 어머니 품에
고요히 누워 있는 것 같습니다.
3이스라엘아, 지금부터 영원히
여호와를 신뢰하라.