መዝሙር 121 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መዝሙር 121:1-8

መዝሙር 121

የእስራኤል ጠባቂ

መዝሙረ መዓርግ።

1ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤

ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል?

2ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣

ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።

3እግርህ እንዲሸራተት አይፈቅድም፤

የሚጠብቅህም አይተኛም።

4እነሆ፤ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፤ አያንቀላፋምም።

5እግዚአብሔር ይጠብቅሃል፤

እግዚአብሔር በቀኝህ በኩል ይከልልሃል።

6ፀሓይ በቀን አያቃጥልህም፤

ጨረቃም በሌሊት ጕዳት አታመጣብህም።

7እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤

ነፍስህንም ይንከባከባታል።

8እግዚአብሔር ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣

መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

詩篇 121:1-8

第 121 篇

上帝是我的保護者

上聖殿朝聖之詩。

1我舉目觀看群山,

我的幫助從哪裡來?

2我的幫助來自創造天地的耶和華。

3祂必不讓你滑倒,

保護你的不會打盹。

4保護以色列的不打盹也不睡覺。

5耶和華保護你,

在你身邊蔭庇你。

6白天太陽不會傷你,

夜間月亮不會害你。

7耶和華必使你免受災害,

保護你的性命。

8不論你出或入,

耶和華都會保護你,從現在直到永遠。