መዝሙር 117 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

መዝሙር 117:1-2

መዝሙር 117

የምስጋና ጥሪ

1አሕዛብ ሁላችሁ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤

ሕዝቦችም ሁሉ፤ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት፤

2እርሱ ለእኛ ያሳየው ምሕረት ታላቅ ነውና፤

የእግዚአብሔርም ታማኝነት ጸንቶ ይኖራል።

ሃሌ ሉያ።117፥2 አንዳንዶች እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።