መዝሙር 100 – New Amharic Standard Version NASV

New Amharic Standard Version

መዝሙር 100:1-5

መዝሙር 100

እግዚአብሔርን ለማመስገን የቀረበ ግብዣ

የምስጋና መዝሙር።

1ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤

2እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤

በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።

3እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤

እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤

እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።

4በምስጋና ወደ ደጆቹ፣

በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤

አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤

5እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤

ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።