መክብብ 9 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

መክብብ 9:1-18

የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ

1ስለዚህ ይህን ሁሉ በልቤ አስቤ እንዲህ አልሁ፤ ጻድቃንና ጠቢባን የሚሠሩትም ሥራ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ነገር ግን ፍቅር ይሁን ወይም ጥላቻ የሚጠብቀውን ማንም አያውቅም። 2ጻድቃንና ኀጥኣን፣ ደጎችና ክፉዎች9፥2 ሰብዓ ሊቃናት (አቍዊላ) ቨልጌትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ፣ ዕብራይስጡ ግን ክፉዎች የሚለው የለም፣ ንጹሓንና ርኩሳን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡና የማያቀርቡ፣ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው።

ለደጉ ሰው እንደ ሆነው ሁሉ፣

ለኀጢአተኛውም እንዲሁ ነው፤

ለሚምሉት እንደ ሆነው ሁሉ፣

መሐላን ለሚፈሩትም እንዲሁ ነው።

3ከፀሓይ በታች በሁሉም ላይ የሚሆነው ክፋት ይህ ነው፤ የሁሉም የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ አንድ ነው። በዚህም ላይ የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፤ በሕይወት እያሉም በልባቸው ውስጥ እብደት አለ፤ በመጨረሻም ወደ ሙታን ይወርዳሉ። 4በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው9፥4 ወይም ታዲያ የሚመረጠው ምንድን ነው? ለሕያዋን ሁሉ ተስፋ አለ፤ በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና!

5ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤

ሙታን ግን ምንም አያውቁምና፤

መታሰቢያቸው ይረሳል፤

ምንም ዋጋ የላቸውም።

6ፍቅራቸው፣ ጥላቻቸው፣

ቅናታቸውም ከጠፋ ቈይቷል፤

ከፀሓይ በታች በሚሆነው ነገር ሁሉ፣

ፈጽሞ ዕጣ ፈንታ አይኖራቸውም።

7ሂድ፤ ምግብህን በደስታ ብላ፤ ወይንህንም ልብህ ደስ ብሎት ጠጣ፤ ባደረግኸው ነገር እግዚአብሔር ደስ ብሎታልና። 8ዘወትር ልብስህ ነጭ ይሁን፤ ራስህንም ዘወትር በዘይት ቅባ። 9እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጕም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና። 10እጅህ የሚያገኘውን ሥራ ሁሉ በሙሉ ኀይልህ ሥራው፤ ልትሄድበት ባለው መቃብር9፥10 በዕብራይስጥ ሲኦል ማለት ነው ውስጥ መሥራትም ሆነ ማቀድ፣ ዕውቀትም ሆነ ጥበብ የለምና።

11ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤

ሩጫ ለፈጣኖች፣

ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤

እንጀራ ለጥበበኞች፣

ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣

ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤

ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።

12ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤

ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣

ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣

ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣

በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

ጥበብ ከሞኝነት ይበልጣል

13እንዲሁም እጅግ ያስገረመኝን ይህን የጥበብ ምሳሌ ከፀሓይ በታች አየሁ፤ 14ጥቂት ሰዎች የሚኖሩባት አንዲት ትንሽ ከተማ ነበረች፤ አንድ ኀያል ንጉሥም መጣባት፤ ከበባት፤ በላይዋም ትልቅ ምሽግ ሠራባት። 15በዚያችም ከተማ ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ይኖር ነበር፤ በጥበቡም ከተማዋን አዳናት፤ ነገር ግን ያን ድኻ ማንም አላስታወሰውም። 16ስለዚህ፣ “ጥበብ ከኀይል ይበልጣል” አልሁ፤ ሆኖም የድኻው ጥበብ ተንቋል፤ ቃሉም አልተሰማም።

17ሞኞችን ከሚያስተዳድር ገዥ ጩኸት ይልቅ፣

ጠቢብ በዝግታ የሚናገረው ቃል ይደመጣል።

18ጥበብ ከጦር መሣሪያ ይበልጣል፤

ነገር ግን አንድ ኀጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።

New International Version – UK

Ecclesiastes 9:1-18

A common destiny for all

1So I reflected on all this and concluded that the righteous and the wise and what they do are in God’s hands, but no-one knows whether love or hate awaits them. 2All share a common destiny – the righteous and the wicked, the good and the bad,9:2 Septuagint (Aquila), Vulgate and Syriac; Hebrew does not have and the bad. the clean and the unclean, those who offer sacrifices and those who do not.

As it is with the good,

so with the sinful;

as it is with those who take oaths,

so with those who are afraid to take them.

3This is the evil in everything that happens under the sun: The same destiny overtakes all. The hearts of people, moreover, are full of evil and there is madness in their hearts while they live, and afterwards they join the dead. 4Anyone who is among the living has hope9:4 Or What then is to be chosen? With all who live, there is hope – even a live dog is better off than a dead lion!

5For the living know that they will die,

but the dead know nothing;

they have no further reward,

and even their name is forgotten.

6Their love, their hate

and their jealousy have long since vanished;

never again will they have a part

in anything that happens under the sun.

7Go, eat your food with gladness, and drink your wine with a joyful heart, for God has already approved what you do. 8Always be clothed in white, and always anoint your head with oil. 9Enjoy life with your wife, whom you love, all the days of this meaningless life that God has given you under the sun – all your meaningless days. For this is your lot in life and in your toilsome labour under the sun. 10Whatever your hand finds to do, do it with all your might, for in the realm of the dead, where you are going, there is neither working nor planning nor knowledge nor wisdom.

11I have seen something else under the sun:

The race is not to the swift

or the battle to the strong,

nor does food come to the wise

or wealth to the brilliant

or favour to the learned;

but time and chance happen to them all.

12Moreover, no-one knows when their hour will come:

As fish are caught in a cruel net,

or birds are taken in a snare,

so people are trapped by evil times

that fall unexpectedly upon them.

Wisdom better than folly

13I also saw under the sun this example of wisdom that greatly impressed me: 14there was once a small city with only a few people in it. And a powerful king came against it, surrounded it and built huge siege works against it. 15Now there lived in that city a man poor but wise, and he saved the city by his wisdom. But nobody remembered that poor man. 16So I said, ‘Wisdom is better than strength.’ But the poor man’s wisdom is despised, and his words are no longer heeded.

17The quiet words of the wise are more to be heeded

than the shouts of a ruler of fools.

18Wisdom is better than weapons of war,

but one sinner destroys much good.