መክብብ 8 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መክብብ 8:1-17

1ነገሮችን መግለጽ የሚችል፣

እንደ ጠቢብ ያለ ሰው ማን ነው?

ጥበብ የሰውን ፊት ታበራለች፤

የከበደ ገጽታውንም ትለውጣለች።

ንጉሥን ታዘዝ

2በእግዚአብሔር ፊት መሐላ ስለ ፈጸምህ፣ የንጉሥን ትእዛዝ አክብር እልሃለሁ። 3ከንጉሥ ፊት ተጣድፈህ አትውጣ፤ የወደደውንም ማድረግ ስለሚችል ለጥፋት አትሰለፍ። 4የንጉሥ ቃል የበላይ ስለሆነ እርሱን፣ “ምን ታደርጋለህ?” ማን ሊለው ይችላል?

5እርሱን የሚታዘዝ ሁሉ አይጐዳም፤

ጥበበኛም ልብ ትክክለኛውን ጊዜና ተገቢውን አሠራር ያውቃል።

6የሰው መከራ እጅግ ቢጫነውም፣

ለሁሉም ነገር ትክክለኛ ጊዜና ተገቢ አሠራር አለው።

7ሰው የወደ ፊቱን ስለማያውቅ፣

ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?

8ሰው ነፋስን መቈጣጠር አይችልም8፥8 ወይም መንፈሱን ለማቈየት አይችልም

በዕለተ ሞቱም ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፤

በጦርነት ጊዜ ማንም ከግዴታ ነጻ እንደማይሆን፣

ክፋትም የሚለማመዷትን አትለቃቸውም።

9ከፀሓይ በታች የተሠራውን ሁሉ በአእምሮዬ መርምሬ፣ ይህን ሁሉ አየሁ። ሰው ሰውን ለመጕዳት ገዥ የሚሆንበት ጊዜ አለ። 10እንዲሁም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ይመጡና ይሄዱ የነበሩት ክፉዎች ተቀብረው አየሁ፤ ይህን ባደረጉበት ከተማም ይመሰገኑ ነበር8፥10 አንዳንድ የዕብራይስጥ ቅጆችና ሰብዓ ሊቃናት (አቍዊላ) እንዲሁ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ የዕብራይስጥ ቅጆች ግን ተረስተዋል ይላሉ።፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።

11በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል። 12ኀጥእ መቶ ወንጀል ሠርቶ ዕድሜው ቢረዝምም፣ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ፣ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው ሰዎች መልካም እንደሚሆንላቸው ዐውቃለሁ። 13ነገር ግን ክፉዎች እግዚአብሔርን ስለማይፈሩ መልካም አይሆንላቸውም፤ ዕድሜያቸው እንደ ጥላ አይረዝምም።

14በምድር ላይ የሚከሠት ሌላም ከንቱ ነገር አለ፤ ጻድቃን ለክፉዎች የሚገባውን፣ ክፉ ሰዎችም ለጻድቃን የሚገባውን ይቀበላሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ነው አልሁ። 15ለሰው፣ ከፀሓይ በታች ከመብላት፣ ከመጠጣትና ከመደሰት ሌላ የተሻለ ነገር ስለሌለ፣ በሕይወት ደስ መሰኘት መልካም ነው አልሁ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከፀሓይ በታች በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሥራው ደስታ ይኖረዋል።

16ጥበብን ለማወቅና ሌት ተቀን እንቅልፍ የማያውቀውን በምድር ያለውን የሰውን ድካም ለመገንዘብ በአእምሮዬ ስመረምር፣ 17እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ አየሁ። ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ማንም ሊያውቅ አይችልም፤ ሰው ለመመርመር ብዙ ቢጥርም፣ ትርጕሙን ማግኘት አይችልም፤ ጠቢብም እንኳ ዐውቀዋለሁ ቢል፣ ፈጽሞ ሊገነዘበው አይችልም።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

傳道書 8:1-17

1誰像有智慧的人呢?

誰知道事情的原委呢?

智慧能使人容光煥發,

使冷酷的面孔柔和。

2我勸你遵守王的命令,因為你曾在上帝面前這樣發誓。 3不要在王面前魯莽行事,也不要參與惡行,因為王可以隨意行事。 4況且,王的命令至高無上,誰敢質問他呢? 5遵從王命的必免遭禍患,因為智者心裡懂得做事的時機和方法。 6儘管人面臨重重困難,但做任何事都有時機和方法。 7無人知道未來的事,誰能告訴人將來的事呢? 8無人能掌管生命8·8 生命」也可譯作「風」或「氣息」。,留住生命,也無人能掌管死期。無人能免於這場爭戰,邪惡也救不了作惡者。 9這一切我都見過了,我用心思考日光之下的一切事。有時人欺壓人、傷害人。 10我看見惡人生前出入聖所,死後安葬,還在他們作惡的城中受到稱讚,這也是虛空。 11對犯罪者的刑罰不迅速執行,世人便盡情作惡。 12雖然罪人作惡多端仍得長壽,我卻認為敬畏上帝的人必亨通。 13然而,惡人得不到祝福,他們必像幻影一樣不能長久,因為他們不敬畏上帝。 14世上有一件虛空的事,就是義人遭受了惡人當受的報應,惡人卻享受了義人該享的福樂。我認為這也是虛空。 15因此,我便讚賞享樂,因為在日光之下沒有什麼比吃喝快樂更好。這是人在上帝所賜的年日裡,從勞碌中當得的享受。 16我全心去尋求智慧,觀察世上所發生的事,甚至晝夜不眠, 17思想上帝所做的一切,便知道人無法理解日光之下所發生的事。儘管人努力不懈地去尋找,也不能明白;即使智者自以為明白,他其實仍不能參透。