የዲቦራ መዝሙር
1በዚያን ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤
2“በእስራኤል ያሉ መሳፍንት ሲመሩ፣
ሕዝቡም በፈቃዱ ራሱን ሲያስገዛ፣
እግዚአብሔርን አመስግኑ።
3“እናንት ነገሥታት ይህን ስሙ፤
ገዦችም አድምጡ፤
ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ደግሜም
ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ።
4“እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣
ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣
ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤
ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።
5ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣
በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ።
6“በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣
በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤
ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።
7ለእስራኤል እናት ሆኜ
እኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስ
በእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤
8አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣
ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤
ጋሻም ሆነ ጦር፣
በአርባ ሺሕ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም።
9ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣
ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤
እግዚአብሔር ይመስገን።
10“እናንት በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣
በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣
በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣
በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣
11የዝማሬ ድምፅ5፥11 ወይም ቀስተኞች ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። ስሙ።
ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣
ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።
“ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣
ወደ ከተማዪቱ5፥11 ወይም ወደ መንደሮቹ ተብሎ መተርጐም ይቻላል። በሮች ወረዱ።
12‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤
ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤
የአቢኒኤል ልጅ ባራቅ ሆይ፤ ተነሣ፤
ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ።
13“የቀሩትም ሰዎች፣
ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ፣ እንደ ኀያል ጦረኛ ወደ እኔ መጣ።
14መሠረታቸው ከአማሌቅ የሆነ አንዳንዶች
ከኤፍሬም መጡ፤ ብንያም አንተን ከተከተሉ ሰዎች ጋር ነበር፤
የጦር አዛዦች ከማኪር፣
የሥልጣን በትር የያዙም ከዛብሎን ወረዱ።
15የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋር ነበሩ፤
ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላው
በመከተል፣ ከባርቅ ጋር ነበረ።
በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ
ምርምር ነበር።
16በበጎች ጕረኖ5፥16 ወይም በኮርቻ ላይ ተብሎ መተርጐም ይቻላል። መካከል ለምን ተቀመጥህ?
መንጎችን የሚጠራውን ፉጨት ለመስማት ነውን?
በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ
ምርምር ነበር።
17ገለዓድ ከዮርዳኖስ ማዶ ተቀመጠ፤
ዳን ለምን በመርከብ ውስጥ ዘገየ?
አሴር በጠረፍ ቀረ፤
በባሕሩ ዳርቻም ተቀመጠ።
18የዛብሎን ሰዎች ሕይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ፤
የንፍታሌም ሰዎች እንደዚሁ በምድሪቱ ኰረብታዎች አደረጉ።
19“ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤
የከነዓን ነገሥታት፣ በመጊዶ ውሆች
አጠገብ በታዕናክ ተዋጉ፤
ብርም ሆነ ሌላ ምርኮ ተሸክመው አልሄዱም።
20ከሰማያት ከዋክብት ተዋጉ፤
በአካሄዳቸውም ሲሣራን ገጠሙት።
21ጥንታዊው ወንዝ፣ የቂሶን ወንዝ፣
የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው፤
ነፍሴ ሆይ፤ በኀይል ገሥግሺ
22የፈረሶች ኰቴ ድምፅ በኀይል ተሰማ፤
ጋለቡ፤ በኀይልም ፈጥነው ጋለቡ።
23የእግዚአብሔር መልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’
‘ሕዝቧንም አብራችሁ ርገሙ፤
ከኀያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት፣
በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ።
24“የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፣
ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን፤
በድንኳን ከሚኖሩ ሴቶች ሁሉ የተባረከች ትሁን።
25ውሃ ለመነ፤ ወተት ሰጠችው፤
ለመኳንንት በሚገባ ዕቃ፣ እርጎ አቀረበችለት።
26እጇ ካስማ ያዘ፤
ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤
ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤
ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።
27በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤
በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤
ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤
ሞተም።
28“የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤
በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤
‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ?
የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።
29ብልኅተኞች ወይዛዝርቷም መለሱላት፤
እርሷ ግን ለራሷ እንዲህ አለች፤
30‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣
እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን?
ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶች
ለሲሣራ ደርሰውት፣
በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለዐንገቴ
ይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’
31“እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤
አንተን የሚወድዱህ ግን፣ የንጋት ፀሓይ
በኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።”
ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።
底波拉和巴拉之歌
1那一天,底波拉和巴拉高唱凯歌:
2“以色列的首领身先士卒,
民众前仆后继,
你们要赞美耶和华!
3君王和首领啊,请留心细听!
我要向耶和华歌唱,
我要歌颂以色列的上帝耶和华。
4耶和华啊,当你从西珥出来,
走过以东时,
大地震动,
天上降雨。
5在西奈山的耶和华面前,
在以色列的上帝耶和华面前,
群山震动。
6在亚拿的儿子珊迦与雅亿的时代,
大路行人绝迹,
旅客绕道而行。
7我底波拉做以色列之母以前,
以色列的乡村人烟稀少。
8以色列人选择新的神明,
便战祸临门,
四万以色列人中找不到一矛一盾。
9我的心追随以色列的首领,
追随民中踊跃出征的人。
你们要赞美耶和华!
10“你们骑白驴的、坐绣花毯子的、步行的,
都要倾听。
11歌乐手聚集在井旁,
传扬耶和华和祂以色列子民的胜利。
耶和华的子民都来到城门口。
12“底波拉啊,来吧,来吧,
歌唱吧!
亚比挪庵的儿子巴拉啊,来吧,
带走你的战俘吧!
13幸存的以色列人响应他们的首领,
耶和华的子民为我攻击勇士。
14他们有些来自原属亚玛力人的以法莲,
有些来自便雅悯,
统领出自玛吉,
将官出自西布伦。
15以萨迦的首领与底波拉同往,
以萨迦人随巴拉同去,
众人一起冲进山谷,
吕便人却犹豫不决。
16吕便人为什么坐在羊圈中听悠悠笛声?
他们举棋不定。
17基列人留在约旦河对岸。
但人为什么停留在船上?
亚设人在海岸静坐,
在港口逗留。
18但西布伦人和拿弗他利人却拼死鏖战沙场。
19“迦南诸王来战,
来到米吉多河边的他纳交战,
却没有掠走金银。
20星辰从天上、从它们的轨道攻击西西拉。
21古老的基顺河冲走了敌人。
我的心啊,要奋勇向前!
22蹄声隆隆,
骏马疾驰!
23“耶和华的天使说,
‘要咒诅米罗斯,
要重重地咒诅米罗斯的居民,
因为他们没有帮助耶和华,
没有帮助耶和华攻击强敌。’
24“基尼人希百的妻子雅亿是妇人中最有福的,
是住帐篷的妇人中最有福的。
25西西拉求水,
雅亿给他奶喝,
用珍贵的碗盛上奶酪。
26雅亿左手拿起橛子,
右手拿起工匠的锤子,
猛击西西拉,
打碎了他的头,
刺透了他的太阳穴。
27西西拉屈身倒下,
死在她脚前,
一动不动地躺在那里。
28“他母亲凭窗远眺,
隔着窗棂喊道,
‘为什么他的战车迟迟不回?
为什么还听不到车轮声?’
29聪明的宫女安慰她,
她却依然自言自语,
30‘莫非他们在搜索、瓜分战利品?
也许每人得到一两个少女,
西西拉也会分得从俘虏身上夺来的绣花彩巾。’
31耶和华啊,
愿你的敌人都像西西拉一样灭亡!
愿爱你的人如升起的太阳,
光辉熠熠!”
此后,以色列安享太平四十年。