መሳፍንት 2 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

መሳፍንት 2:1-23

የእግዚአብሔር መልአክ በቦኪም

1የእግዚአብሔር መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፤ “ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ለቀደሙትም አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልሁ፤ ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤ 2እናንተም ከዚህች ምድር ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን አታድርጉ፤ መሠዊያቸውንም አፍርሱ፤ እናንተ ግን አልታዘዛችሁኝም፤ ይህን ያደረጋችሁት ለምንድን ነው? 3ስለዚህ አሁንም ከፊታችሁ አሳድጄ እንደማላስወጣቸው እነግራችኋለሁ፤ ነገር ግን እነርሱ የጐን ውጋት፣ አማልክታቸውም ወጥመድ ይሆኑባችኋል።”

4የእግዚአብሔርም መልአክ ይህን ቃል ለእስራኤላውያን ሁሉ በተናገረ ጊዜ፣ ሕዝቡ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ 5ያንን ስፍራ ቦኪም2፥5 ቦኪም ማለት አልቃሽ ማለት ነው። ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ።

ያለ መታዘዝ ውጤት

6ኢያሱ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ምድሪቱን ለመውረስ ወደየርስቱ ሄደ። 7ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ዘመን ሁሉ እንዲሁም ከእርሱ በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ያዩ አለቆች በነበሩበት ዘመን ሁሉ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አመለከ።

8የእግዚአብሔር አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ በመቶ ዐሥር ዓመቱ ሞተ። 9እነርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በምትገኘው ከገዓስ ተራራ በስተ ሰሜን ባለችው በራሱ ርስት ላይ በተምናሔሬስ ቀበሩት።

10ያ ሁሉ ትውልድ ወደ አባቶቹ ከተከማቸ በኋላ እግዚአብሔርንም ሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሣ። 11ከዚያም እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ የበኣል አማልክትንም አመለኩ። 12ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፤ በዙሪያቸው ያሉት ሕዝቦች የሚያመልኳቸውን አማልክት ተከተሉ፤ ሰገዱላቸውም። እግዚአብሔርንም አስቈጡት፤ 13እርሱን ትተው በኣልንና አስታሮትን አምልከዋልና 14እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ በመቈጣቱ ለሚዘርፏቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸው ላሉ ጠላቶቻቸው ሸጣቸው። 15እስራኤላውያን ለውጊያ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀድሞ በእነርሱ ላይ እንደ ተናገረውና እንደ ማለው ይሸነፉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ እጅግ ተጨነቁ።

16እግዚአብሔርም ከእነዚህ ወራሪዎች የሚያድኗቸውን መሳፍንት2፥16 በዚህም ከ17-19 ባለው ክፍል መሪ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። አስነሣ፤ 17እስራኤላውያን ግን ሌሎችን አማልክት ተከትለው አመነዘሩ፤ ሰገዱላቸውም እንጂ መሳፍንታቸውን አልሰሙም። አባቶቻቸው እግዚአብሔርን በመታዘዝ በሄዱበት መንገድ ሳይሆን፣ አባቶቻቸው የእግዚአብሔርን ሕግ በመከተል ከሄዱበት መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ። 18እግዚአብሔር መሳፍንትን ባሰነሣላቸው ቍጥር ከመስፍኑ ጋር ስለሚሆን፣ እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ እግዚአብሔር ከጠላቶቻቸው ያድናቸው ነበር፤ ከጠላቶቻቸው ሥቃይና መከራ ሲደርስባቸው በሚጮኹበት ጊዜ እግዚአብሔር ይራራላቸው ነበር። 19መስፍኑ ከሞተ በኋላ ግን ሕዝቡ ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ እነርሱን በማገልገልና በማምለክ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ክፉ መንገድ ተመለሱ፤ ክፉ ሥራቸውንና የእልኸኝነት መንገዳቸውንም አይተውም ነበር።

20ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እንዲህም አለ፤ “ይህ ሕዝብ ለቀደሙ አባቶቹ የሰጠሁትን ቃል ኪዳን ስለ ተላለፈ፣ እኔንም ስላልሰማ፣ 21ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም እንኳ በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም። 22ይህን የማደርገውም አባቶቻቸው እንዳደረጉት ሁሉ፣ እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን መንገድ የሚጠብቁ መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ እፈትናቸው ዘንድ እነርሱን መሣሪያ ለማድረግ ነው።” 23ስለዚህ እግዚአብሔር እነዚያን ሕዝቦች በዚያው እንዲኖሩ አደረገ፤ በኢያሱ እጅ አሳልፎ በመስጠት ወዲያውኑ አሳድዶ አላስወጣቸውም።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

士師記 2:1-23

耶和華責備以色列人

1耶和華的天使從吉甲來到波金,對以色列人說:「我帶你們離開埃及,領你們去我起誓要賜給你們祖先的土地。我說,『我永不廢棄跟你們立的約, 2你們不可跟這裡的居民立約,要毀掉他們的祭壇。』可是你們為什麼不聽呢? 3因此,我告訴你們,我必不趕走這裡的居民,他們必成為你們肋旁的刺,他們的神明必成為你們的網羅。」 4以色列人聽了耶和華的天使說的話,就放聲大哭, 5他們稱那地方為波金2·5 波金」意思是「哭泣」。,在那裡向耶和華獻祭。

約書亞去世

6約書亞遣散以色列人後,他們便各自去攻佔所分得的土地。 7約書亞在世的時候,以色列人都事奉耶和華。他死後,那些目睹耶和華為以色列人行大事的長老還在世的時候,以色列人仍然事奉耶和華。 8耶和華的僕人、的兒子約書亞去世時享年一百一十歲。 9以色列人把他葬在他自己的土地上,在迦實山以北、以法蓮山區的亭拿·希烈10那一代人都去世後,新一代不認識耶和華,也不知道耶和華為以色列人所行的事。

11以色列人做耶和華視為惡的事,祭拜巴力12他們背棄了領他們祖先離開埃及的上帝耶和華,追隨、祭拜鄰邦的各種神明,因而惹耶和華發怒。 13他們背棄耶和華,去祭拜巴力亞斯她錄14耶和華向他們發怒,使他們遭到掠奪者的攻擊和四周仇敵的壓制,毫無抵抗之力。 15他們每次出戰,耶和華都與他們為敵,使他們戰敗,正如祂的誓言。他們苦不堪言。

16後來,耶和華使士師2·16 士師」意思是「首領」。興起,從掠奪者手中拯救他們。 17但他們不聽從士師的話,與其他神明苟合,祭拜它們,很快偏離他們祖先的道路,沒有像他們的祖先那樣遵行耶和華的命令。 18耶和華見他們因敵人的壓迫和苦待而哀號,就憐憫他們,使士師陸續興起,並與每位士師同在。士師在世之日,耶和華從仇敵手中拯救他們。 19士師去世以後,他們又故態復萌,追隨、祭拜其他神明,比他們的祖先更敗壞。他們執迷不悟,怙惡不悛。 20耶和華向他們發怒,說:「這百姓違背了我跟他們祖先所立的約,不聽從我的話。 21因此,我不再逐出約書亞去世時還沒有趕走的外族人, 22我要藉此試驗以色列人,看他們是否像他們祖先一樣謹遵我的道。」 23這就是為什麼耶和華留下那些外族人,沒有立刻把他們趕走,也沒有把他們交在約書亞手中。