ሕዝቅኤል 47 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 47:1-23

ከቤተ መቅደሱ ተነሥቶ የሚፈውስ ወንዝ

1ከዚያም ያ ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ መልሶ አመጣኝ፤ ከቤተ መቅደሱ መድረክ ሥር ውሃ እየወጣ፣ ወደ ምሥራቅ ይፈስስ ነበር፤ ቤተ መቅደሱ ለምሥራቅ ትይዩ ነበርና። ውሃው ከቤተ መቅደሱ በስተ ደቡብ በኩል፣ በመሠዊያው ደቡብ በኩል፣ ሥር ሥሩን ይወርዳል። 2ከዚያም በሰሜኑ በር በማውጣት በውጭ አዙሮ በምሥራቅ አቅጣጫ ወዳለው የውጭ በር መራኝ፤ ውሃውም በደቡብ በኩል ይፈስስ ነበር። 3ያም ሰው የመለኪያውን ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ በመሄድ፣ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ ከዚያም እስከ ቍርጭምጭሚት በሚደርሰው ውሃ ውስጥ መራኝ፤ 4ቀጥሎም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ጕልበት ወደሚደርስም ውሃ መራኝ፤ ከዚያም ሌላ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ወገብ ወደሚደርስም ውሃ መራኝ። 5እንደ ገናም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ አሁን ግን ልሻገረው የማልችል ወንዝ ሆነ፤ ምክንያቱም ውሃው ስለ ሞላና ጥልቅ ስለ ነበረ፣ በዋና ካልሆነ በስተቀር በእግር ሊሻገሩት የማይቻል ነበረ። 6እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን ታየዋለህን?” ሲል ጠየቀኝ።

ከዚያም መልሶ ወደ ወንዙ ዳር መራኝ፤ 7እዚያም በደረስሁ ጊዜ፣ በወንዙ ግራና ቀኝ ብዙ ዛፍ አየሁ። 8እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ይህ ውሃ ወደ ምሥራቅ ምድር ይፈስሳል፤ ወደ ባሕሩ ወደሚገባበት ወደ ዓረባ47፥8 ወይም ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም47፥8 ሙት ባሕርን ያመለክታል። ሲፈስስ፣ በዚያ የነበረው ውሃ ንጹሕ ይሆናል። 9ወንዙ በሚፈስስበት ስፍራ ሁሉ ብዙ ሕያዋን ፍጡራን ይኖራሉ። ይህ ውሃ በዚያ ስለሚፈስስና ጨውማ የሆነውን ውሃ ንጹሕ ስለሚያደርገው፣ ዓሣ በብዛት ይኖራል፤ ስለዚህ ወንዙ በሚፈስስበት ስፍራ ሁሉ ማንኛውም ነገር በሕይወት ይኖራል። 10ዓሣ አጥማጆች በወንዙ ዳር ይቆማሉ፤ ከዓይንጋዲ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ ያለው ቦታ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣውም እንደ ታላቁ ባሕር47፥10 ሜድትራኒያንን ያመለክታል፤ እንዲሁም 19 እና 20 ዓሣ፣ የተለያየ ዐይነት ይሆናል። 11ነገር ግን ረግረጉና ዕቋሪው ውሃ ንጹሕ አይሆንም፤ ጨው እንደ ሆነ ይቀራል። 12በወንዙም ዳርና ዳር፣ ፍሬ የሚያፈሩ የዛፍ ዐይነቶች ሁሉ ይበቅላሉ፤ ቅጠላቸው አይደርቅም፤ ፍሬ አልባም አይሆኑም። ከመቅደሱ የሚወጣው ውሃ ስለሚፈስላቸው በየወሩ ያፈራሉ፤ ፍሬያቸው ለምግብ፣ ቅጠላቸውም ለፈውስ ይሆናል።”

የምድሪቱ ወሰን

13ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ምድሪቱን ርስት አድርገህ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ የምታከፋፍሉባቸው ወሰኖች እነዚህ ናቸው፤ ዮሴፍ ሁለት ዕጣ ይኑረው። 14እኩል አድርጋችሁ ከፋፍሉት፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ በተዘረጋች እጅ ስለ ማልሁ፣ ምድሪቱ ርስታችሁ ትሆናለች።

15“የምድሪቱ ወሰን ይህ ነው፤

“በሰሜን በኩል ከታላቁ ባሕር አንሥቶ በሔትሎን መንገድ በሐማት መተላለፊያ አድርጎ እስከ ጽዳድ ይደርሳል፤ 16ከዚያም ቤሮታን፣47፥15-16 ሰብዐ ሊቃናትንና ሕዝ 48፥1 ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን ወደ ዘዳድ የሚወስደው መንገድ፣ 16 ሐማት ቤሮታን… ይላል። በደማስቆና በሐማት ወሰን መካከል ያለውን ሲብራይምን ዐልፎ፣ በሐውራን ወሰን ላይ እስካለው እስከ ሐጸርሃቲኮን ይዘልቃል። 17ወሰኑ ከባሕሩ በመነሣት፣ በሰሜኑ የደማስቆ ድንበር አድርጎ፣ የሐማትንም ዳርቻ ወደ ሰሜን ትቶ እስከ ሐጸርዔናን47፥17 በዕብራይስጥ ዔኖን የዔናን አማራጭ ትርጕም ነው። ይዘልቃል።

18በምሥራቅ በኩል ወሰኑ በሐውራንና በደማስቆ መካከል፣ በገለዓድና በእስራኤል ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል፤ የምሥራቁ ድንበር እስከ ምሥራቁ ባሕር ይወርድና እስከ ታማር47፥18 ሰብዐ ሊቃናትና ሱርስት እንዲሁ ሲሆኑ ዕብራይስጡ ግን እስራኤል፤ ባሕሩን በምሥራቅ በኩል ትለካለህ፤ ይላል። ይዘልቃል፤ ይህም የምሥራቁ ወሰን ይሆናል።

19በደቡብ በኩል ወሰኑ ከታማር ይነሣና እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውሃ ይደርሳል፤ ከዚያም የግብፅን ደረቅ ወንዝ ተከትሎ እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል፤ ይህ የደቡቡ ወሰን ነው።

20በምዕራቡ በኩል ወሰኑ ከሐማት መግቢያ ፊት ለፊት እስካለው ቦታ ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል፤ ይህም የምዕራቡ ወሰን ይሆናል።

21“እነሆ፤ ይህችን ምድር በእስራኤል ነገድ ቍጥር ልክ ትከፋፈላላችሁ፤ 22ለራሳችሁ፣ በመካከላችሁ ለሚኖሩት ልጆች ላሏቸው መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ መድቡ፤ እነርሱንም እንደ እስራኤል ተወላጆች ቍጠሯቸው፤ እንደ እናንተ ከእስራኤል ነገዶች ርስት ይመደብላቸው። 23መጻተኛ በማንኛውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ፣ በዚያ ርስቱን ስጡት፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 47:1-23

从圣殿流出的水

1他又领我回到圣殿门口,我看见有水从圣殿的门槛下往东流去。殿的正面朝东,这水从殿的南侧经祭坛的南边往下流。 2随后他领我由北门出来,从外面绕到外院的东门,我见水从东门的南面涓涓流出。

3那人手拿量绳向东量了五百米,然后领我涉水前行,水深及踝。 4他又量了五百米,领我涉水前行,水深及膝。他又量了五百米,领我涉水前行,水深及腰。 5他又量了五百米,水已高涨成河,足可游泳,无法再涉水而行。 6他问我:“人子啊,你看见了什么?”

然后,他带我回到河边, 7我发现河的两岸长满了树木。 8他对我说:“这水向东流,经过亚拉巴流到盐海,使那里的咸水变为淡水。 9河水流经的地方,万物滋长,鱼产丰盛,因为河水使那里的咸水变成淡水了。 10渔夫要站在岸边捕鱼,从隐·基底隐·以革莲都是晒网的地方。那里的鱼就像大海的鱼一样种类繁多。 11但沼泽和湿洼之地却不会改变,留作产盐之地。 12沿河两岸长着各种果树,树的叶子不会枯干,果实也不会断绝。树必月月结出新果,不但果实可吃,叶子还可作药用,因为这水是从圣所流出来的。”

地界

13主耶和华说:“你要按照我划定的地界,把土地分给以色列的十二支派作产业,除约瑟支派47:13 约瑟支派”就是以法莲和玛拿西两支派。要得两份地业外, 14其他各支派都要均分,因为我曾起誓将这地方赐给你们祖先。这地方必成为你们的产业。

15“以下是这地方的地界:北界从地中海岸经希特伦哈马口、西达达16比罗他大马士革哈马边界中间的西伯莲,一直到浩兰边界的哈撒·哈提干17这样,北界是从地中海岸一直到大马士革边界的哈撒·以难,以哈马为界。

18“东界是从北界南下经浩兰大马士革、沿着基列以色列中间的约旦河为界,一直伸展到东部的海。

19“南界从他玛西经米利巴·加低斯泉和埃及小河直到地中海。

20“西界从南界沿地中海的海岸到北界哈马口对面的地方。

21“你们要按照以色列的各支派分这块地, 22用抽签的方法来分产业,也要分给在你们中间居住、生儿育女的外族人。你们要视他们如同以色列人,要让他们与你们同分产业。 23他们居住在哪一支派,哪一支派便要把产业分给他们。这是主耶和华说的。”