ሕዝቅኤል 42 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 42:1-20

ለካህናት የተመደቡ ክፍሎች

1ከዚያም ያ ሰው በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ ውጩ አደባባይ በማምጣት፣ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ትይዩና በሰሜን በኩል ባለው ግንብ ትይዩ ወደ አሉት ክፍሎች አመጣኝ። 2በሩ በሰሜን ትይዩ የሆነው ሕንጻ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ ወርዱም አምሳ ክንድ ነበር። 3ከውስጠኛው አደባባይ ሃያ ክንድ ርቀት ላይና በአንጻሩም ከውጩ አደባባይ የንጣፍ ድንጋይ ፊት ለፊት ርቀት ላይ በሦስት ደርቦች ትይዩ የሆኑ ሰገነቶች ነበሩ። 4ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ወርዱ ዐሥር ክንድ፣ ርዝመቱ አንድ መቶ ክንድ42፥4 ሰብዐ ሊቃናቱና ሱርስቱ እንዲሁ ሲሆኑ ዕብራይስጡ ግን …አንድ ክንድ ይላል የሆነ መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበር። የክፍሎቹም በሮች በሰሜን በኩል ነበሩ። 5የላይኞቹ ክፍሎች ጠበብ ያሉ ናቸው፤ ምክንያቱም ሰገነቶቹ ታችና መካከል ላይ ካሉት ከሕንጻው ክፍሎች ይልቅ ሰፋ ያሉ ቦታዎች ይዘውባቸዋልና። 6አደባባዮቹ ዐምዶች ሲኖሯቸው፣ በሦስተኛው ደርብ ላይ ያሉት ክፍሎች ግን ዐምድ የላቸውም። ስለዚህ የወለላቸው ስፋት በታችኛውና በመካከለኛው ደርብ ካሉት ክፍሎች ይልቅ ጠበብ ያለ ነው። 7ከክፍሎቹና፣ ከውጩ አደባባይ ትይዩ የሆነ የውጪ ግንብ አለ፤ ይህም በክፍሎቹ ፊት ለፊት ሆኖ አምሳ ክንድ ይረዝማል። 8ከውጩ አደባባይ ቀጥሎ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት አምሳ ክንድ ሲሆን፣ ከቤተ መቅደሱ አጠገብ ያሉት መደዳ ክፍሎች ርዝመት ደግሞ አንድ መቶ ክንድ ነበር። 9ከውጩ አደባባይ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ በስተ ምሥራቅ የታችኞቹ ክፍሎች መግቢያ ይገኛል።

10በደቡብ በኩል42፥10 ሰብዐ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን በስተ ምሥራቅ ይላል የውጩን አደባባይ ግንብ ተከትሎ፣ ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ጋር የተያያዙና ከውጩ ግንብ ጋር ትይዩ የሆኑ ክፍሎች አሉ፤ 11ከፊት ለፊታቸውም መተላለፊያ መንገድ አለ። እነዚህ በሰሜን በኩል ካሉት ክፍሎች ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ ርዝመትና ወርዳቸው፣ መውጫና መጠናቸው አንድ ዐይነት ነበር፤ በሰሜን በኩል እንዳሉት በሮች፣ 12በደቡብ በኩል ያሉት ክፍሎች በሮች መጠናቸው ተመሳሳይ ነበር። ከመመላለሻው መነሻ ላይ መግቢያ በር አለ፤ መመለሻውም ፊት ለፊት ካለው ወደ ምሥራቅ ከሚያመራው ግንብ ጋር ተጓዳኝ ነው።

13ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ከቤተ መቅደሱ አደባባይ ፊት ለፊት ያሉት የሰሜኑና የደቡቡ ክፍሎች የካህናቱ ሲሆኑ፣ እነዚህም በእግዚአብሔር ፊት የሚቀርቡት ካህናት እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች የሚበሉባቸው ናቸው። በዚያም እጅግ የተቀደሱትን ቍርባኖች ማለት የእህሉን ቍርባን፣ የኀጢአቱን ቍርባን፣ የበደሉን ቍርባን ያስቀምጣሉ፤ ቦታው ቅዱስ ነውና። 14ካህናቱ አንድ ጊዜ ወደ ተቀደሰው ቦታ ከገቡ በኋላ፣ ያገለገሉበትን ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጩ አደባባይ መውጣት አይችሉም፤ የተቀደሰ ነውና፤ ወደ ሕዝቡ ቦታ ከመምጣታቸው በፊት ሌላውን ልብሳቸውን መልበስ አለባቸው።”

15በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያለውን ስፍራ ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፣ በምሥራቅ በር በኩል ወደ ውጩ አወጣኝ፤ በዙሪያው ያለውንም ስፍራ ሁሉ ለካ፤ 16በምሥራቅ ያለውንም በመለኪያው ዘንግ ለካ፤ አምስት መቶ ክንድ42፥16 ከሰብዐ ሊቃናት 17ን ይመ፤ ዕብራይስጡ ግን ዘንጎች ይለዋል፤ እንዲሁም 18 እና 19 ሆነ። 17ሰሜኑንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ42፥17 ሰብዐ ሊቃናቱም እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ዘንጎች ይላል ሆነ። 18ደቡቡንም ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ ሆነ። 19ከዚያም ወደ ምዕራብ ጐን ዞሮ ለካ፤ በመለኪያው ዘንግ አምስት መቶ ክንድ ሆነ። 20ስለዚህ በአራቱም ማእዘን ለካው፤ የተቀደሰውን ስፍራ ከሌላው የሚለይ በዙሪያው ግንብ ነበረ፤ የግንቡም ርዝመት አምስት መቶ ክንድ ሲሆን፣ ወርዱ አምስት መቶ ክንድ ነበር።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 42:1-20

祭司用的厢房

1那人带我出了圣殿,向北来到外院的厢房,一排在空地对面,一排在北边的建筑物对面。 2厢房长五十米,宽二十五米,有北门。 3内院十米宽的空地和外院的铺石地对面有三层高的走廊彼此相对。 4在两排厢房之间有一条五米宽、五十米长的通道,厢房的门都向北。 5上层的厢房比下层和中层的窄,因为上层走廊占去较大的面积。 6这建筑物不像外院那样有柱子,所以上层比中层和下层窄。 7厢房旁边的外墙与厢房及外院平行,长二十五米。 8靠近外院的厢房长二十五米,靠近圣殿的厢房则长五十米。 9下层厢房的东面有一道门,可以从外院进入。

10南面42:10 南面”希伯来文是“东面”。的院墙有两排厢房,一排在空地对面,一排在南面的建筑物对面, 11厢房前面有通道。这些厢房与北面的厢房一样,长宽相同,出入口和结构也一样。 12厢房的东面通道的前端有一道门。

13他对我说:“这些在南北两面对着圣殿空地的厢房都是圣洁的,供事奉耶和华的祭司在那里吃至圣的祭物,并放置素祭、赎罪祭和赎过祭,因为这是圣洁的地方。 14祭司在圣所供职后,不可直接到外院,要先在这些厢房里脱下供职时所穿的圣衣,换上普通衣服,才可以到外面的百姓那里。”

15他量完圣殿里面,便带我出了东门,量圣殿外围。 16他用量竿量了东面,长二百五十米; 17又量了北面,长二百五十米; 18又量了南面,长二百五十米; 19然后又去量西面,长二百五十米。 20他量了圣殿四围的墙,长宽都是二百五十米,这墙是为了把圣地和俗地隔开。