ሕዝቅኤል 38 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 38:1-23

በጎግ ላይ የተነገረ ትንቢት

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን በማጎግ ምድር በሚገኘው፣ በሞሳሕና በቶቤል ዋና አለቃ38፥2 ወይም የሮሽ አለቃ በጎግ ላይ አድርግ፤ በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገር፤ 3እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሞሳሕና የቶቤል ዋና አለቃ38፥3 ወይም የሮሽ አለቃ ጎግ ጎግ ሆይ፤ ተነሥቼብሃለሁ። 4ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ መንጋጋህ ውስጥ መንጠቆ አስገብቼ ከመላው ሰራዊትህ ጋር፣ ፈረሶችህን፣ ፈረሰኞችህን ከነሙሉ ትጥቃቸው፣ ትልቅና ትንሽ ሰይፍ የያዙትን ሁሉ፣ ሰይፋቸውንም የወለወሉትን ሁሉ አስወጣለሁ። 5ጋሻ የያዙና የራስ ቍር የደፉት ሁሉ፣ ፋርስ፣ ኢትዮጵያና ፉጥ ከእነርሱ ጋር ይሆናሉ። 6ደግሞም ጎሜርን ከወታደሮቹ ጋር፣ ራቅ ካለው ሰሜንም የቴርጋማን ቤት ከወታደሮቹ ሁሉ ጋር ብዙ ሕዝቦችን ከአንተ ጋር አስወጣለሁ።”

7“ ‘አንተና በዙሪያህ የተሰበሰቡት ሁሉ ተነሡ፤ ተዘጋጁ፤ አንተም መሪያቸው ሁን። 8ከብዙ ቀን በኋላ ለጦርነት ትጠራለህ። በኋለኛው ዘመንም ከጦርነት ያገገመችውን፣ ሕዝቧ ከአያሌ አሕዛብ መካከል ወጥቶ የተሰበሰበውን፣ ለብዙ ጊዜ ባድማ በነበረው በእስራኤል ተራሮች ላይ የሰፈረውን ወገን ትወርራለህ። ከሕዝቦች መካከል ወጥተው፣ አሁን ሁሉም በሰላም ይኖራሉ። 9አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋር ያሉት ብዙ ሕዝቦች እንደ ማዕበል ትወጣላችሁ፤ ምድርን እንደሚሸፍን ደመናም ትሆናላችሁ።

10“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በዚያ ቀን ሐሳብ ወደ አእምሮህ ይመጣል፤ ክፋትንም ታውጠነጥናለህ። 11እንዲህም ትላለህ፤ “ቅጥር የሌላቸውን መንደሮች ምድር እወራለሁ፤ ሁሉም ያለ ቅጥር፣ ያለ በርና ያለ ብረት መወርወሪያ የሚኖረውን፣ ሰላማዊና ያለ ሥጋት የተቀመጠውን ሕዝብ እወጋለሁ፤ 12እዘርፋለሁ፤ እነጥቃለሁ፤ እንዲሁም ከአሕዛብ ተሰባስቦ እንደ ገና በሰፈረው፣ በከብትና በሸቀጥ በከበረው፣ በምድሪቱም መካከል በሚኖረው ሕዝብ ላይ እጄን አነሣለሁ።” 13ሳባና ድዳን፣ የተርሴስ ነጋዴዎችና መንደሮቿም ሁሉ38፥13 ወይም ጠንካራ መንደሮቿ እንዲህ ይሉሃል፤ “ልትዘርፍ መጣህን? ሰራዊትህን ያሰባሰብኸው ለመበዝበዝ፣ ወርቅና ብሩን አጋብሶ ለመሄድ፣ ከብቱንና ሸቀጡን ለመውሰድ፣ ብዙ ምርኮ ይዞ ለመመለስ ነውን?” ’

14“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል በሰላም መቀመጡን ዐውቀህ አትንቀሳቀስምን? 15በስተ ሰሜን ርቆ ከሚገኘው ቦታ ትመጣለህ፤ አንተና ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝቦች፣ እጅግ ታላቅ ኀያል ሰራዊትም በፈረሶች ላይ ሆናችሁ ትመጣላችሁ። 16ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ሆነህ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ትወጣለህ። ጎግ ሆይ፤ በፊታቸው ቅድስናዬን ስገልጥ ሕዝቦች እኔን ያውቁ ዘንድ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ አመጣሃለሁ።”

17“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በቀደመው ዘመን በባሪያዎቼ በእስራኤል ነቢያት ስለ እርሱ የተናገርሁለት ያ ሰው አንተ አይደለህምን? በዚያን ወቅት አንተን በእነርሱ ላይ እንደማመጣባቸው ለብዙ ዓመታት ትንቢት ተናገሩ።” 18በዚያን ጊዜ እንዲህ ይሆናል፤ “ጎግ የእስራኤልን ምድር ሲወጋ፣ ብርቱ ቍጣዬ ይነሣሣል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር19በዚያን ጊዜ በቅናቴና በሚያስፈራው ቍጣዬ በእስራኤል ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ይሆናል ብዬ ተናግሬአለሁ። 20የባሕር ዓሦች፣ የሰማይ ወፎች፣ የምድር አራዊት፣ በምድር ላይ የሚሳብ ማንኛውም ፍጡር፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ፣ በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ፤ ተራሮች ይገለባበጣሉ፤ ገደሎች ይናዳሉ፤ 21በተራሮቼም ሁሉ በጎግ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእያንዳንዱም ሰው ሰይፍ በወንድሙ ላይ ያርፋል። 22በቸነፈርና በደም መፋሰስ እፈርድበታለሁ፤ የዝናብ ዶፍ፣ የበረዶ ድንጋይ፣ የሚያቃጥል ድኝ፣ በእርሱና በወታደሮቹ፣ ከእርሱም ጋር ባሉት ሕዝቦች ላይ አወርዳለሁ። 23በዚህም ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦች ፊት ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ’

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

以西结书 38:1-23

对歌革的预言

1耶和华对我说: 2“人子啊,你要面向玛各地区的歌革,就是米设土巴的首领,说预言斥责他, 3告诉他,主耶和华这样说,‘米设土巴的首领歌革啊,我要与你为敌。 4我要把你调转过来,用钩子钩住你的腮,把你和你那些全副武装、拿着大小盾牌、挥动刀剑的军队、马匹和骑兵都拖出来。 5你的军队中有拿着盾牌、戴着头盔的波斯人、古实人和人, 6还有歌篾的军队和从遥远的北方来的陀迦玛军队。许多国家的军队都与你在一起。

7“‘你和你的联军都要预备好,你要做他们的统帅。 8再过多日,你必被征召出战。在以后的岁月,你将去攻打一片从战争中恢复的土地,以色列久已荒凉的山上有从各国招聚来的百姓。他们从列国中被领回来,如今都在那里安然居住。 9你和你的军队以及各国的联军一起上来,如暴风来临,又如密云覆盖大地。’

10“‘主耶和华说,“那时你必心起歹念,筹划恶谋。 11你必说,我要攻打那没有围墙和城门保护的乡村,毁灭那毫无戒备、安然居住的百姓。 12我要抢掠他们的财物,下手攻击那曾是废墟的城邑和从各国归来的百姓。他们住在世界的中心,牲畜货物甚多。 13示巴人、底但人以及他施的客商和首领都必问,你是来抢掠吗?你聚集军队是来抢夺金银财宝,掳掠牲畜和货物吗?”’

14“人子啊,你要发预言告诉歌革,主耶和华这样说,‘到那天,当我的以色列子民安然居住的时候,难道你会不知道吗? 15你召集各国联军,组成庞大的军队,骑着马从遥远的北方来。 16歌革啊,你必如密云一样遮天蔽日,前来攻击我的以色列子民。将来,我要领你来攻击我的土地,我要在列国面前借着你彰显我的圣洁,使他们认识我。’

17“主耶和华说,‘歌革啊,我从前借我的仆人——以色列的先知所预言的那位就是你,那时他们预言我要领你上来攻击以色列18歌革上来攻击以色列的时候,我必发烈怒。这是主耶和华说的。 19我要在义愤和烈怒中宣告,那天在以色列必有大地震。 20海里的鱼,空中的鸟,田野的走兽,地上的一切动物和人类都要在我面前战栗。山岭必倒塌,悬崖必崩裂,墙垣必坍塌。 21我要在我的山岭上叫刀剑攻击歌革人,使他们自相残杀。这是主耶和华说的。 22我要用瘟疫、杀戮、暴雨、冰雹、烈火和硫磺惩罚他们和他们的联军。 23我要彰显我的权能和圣洁,使各国的人都认识我。这样他们就知道我是耶和华。’