ሕዝቅኤል 29 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 29:1-21

በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት

1በዐሥረኛው ዓመት፣ በዐሥረኛው ወር፣ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈርዖን አዙር፤ በእርሱና በግብፅ ሁሉ ላይ ትንቢት ተናገር፤ 3እንዲህም ብለህ ተናገረው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።

“ ‘በወንዞችህ መካከል የምትተኛ አንተ ታላቅ አውሬ፣

የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ።

“የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤

ለራሴም ሠርቼዋለሁ” ትላለህ።

4ነገር ግን በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፤

የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋር አጣብቃለሁ፤

ቅርፊትህ ላይ ከተጣበቁት ዓሦች ሁሉ ጋር፣

ከወንዞችህ ጐትቼ አወጣሃለሁ።

5አንተንና በወንዞችህ ያለውን ዓሣ ሁሉ፣

በምድረ በዳ እጥላለሁ።

በገላጣ መሬት ላይ ትወድቃለህ፤

የሚሰበስብህ፣ የሚያነሣህም አይኖርም።

ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች፣

ምግብ እንድትሆን አሳልፌ እሰጥሃለሁ።

6ከዚያም በግብፅ የሚኖሩ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

“ ‘ለእስራኤል ቤት የሸንበቆ በትር ነበርህ፤ 7በእጃቸው ሲይዙህ ተሰንጥረህ ትከሻቸውን ወጋህ፤ ሲደገፉህም ተሰብረህ ጀርባቸውን አጐበጥህ።29፥7 በሱርስቱም (በተጨማሪ ሰብዐ ሊቃናትና ቩልጌትን ይመ) እንዲሁ ሲሆን ዕብራይስጡ ግን ጀርባቸውን ቀጥ አደረግህ ይላል

8“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰይፍ አመጣብሃለሁ፤ ሰዎችህንና እንስሶቻቸውን እገድላለሁ። 9ግብፅ ባድማና ምድረ በዳ ትሆናለች፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

“ ‘ “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ እኔም ሠርቼዋለሁ” ብለሃልና፤ 10ስለዚህ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ በወንዞችህ ላይ ተነሥቻለሁ፤ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል እስከ አስዋን ከዚያም እስከ ኢትዮጵያ ወሰን ድረስ ፍርስራሽና ባድማ አደርጋታለሁ። 11የሰው እግርም ሆነ የእንስሳ ኰቴ በውስጧ አያልፍም፤ እስከ አርባ ዓመት ማንም አይኖርባትም። 12የግብፅን ምድር ከጠፉት ምድሮች መካከል እንደ አንዱ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከተሞቿም በፈራረሱት ከተሞች መካከል አርባ ዓመት ባድማ ይሆናሉ፤ ግብፃውያንንም በአሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ።

13“ ‘ያም ሆኖ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከአርባ ዓመት በኋላ ግብፃውያንን ከተበተኑበት አገሮች መካከል እሰበስባቸዋለሁ። 14ከተማረኩበት አመጣቸዋለሁ፤ ወደ አባቶቻቸው ምድር ወደ ጳትሮስ እመልሳቸዋለሁ። 15ከመንግሥታት ሁሉ አነስተኛ ትሆናለች፤ ከሌሎችም አሕዛብ በላይ ራሷን ከፍ ማድረግ አትችልም። እጅግ ደካማ አደርጋታለሁ፤ ስለዚህ ሌሎችን አሕዛብ እንደ ገና መግዛት አትችልም። 16ግብፅ ከእንግዲህ ለእስራኤል ሕዝብ መታመኛ አትሆንም፤ ለርዳታ ወደ እርሷ ዘወር ባሉ ጊዜ ላደረጉት ኀጢአት ግን መታሰቢያ ትሆናለች። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”

17በሃያ ሰባተኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 18“የሰው ልጅ ሆይ፤ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አስቸጋሪ በሆነ ዘመቻ ሰራዊቱን በጢሮስ ላይ አንቀሳቀሰ፤ የሁሉም ራስ ተመልጧል፤ የሁሉም ትከሻ ተልጧል፤ ይሁን እንጂ እርሱና ሰራዊቱ በጢሮስ ላይ ካደረጉት ዘመቻ ያተረፉት ነገር የለም። 19ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ግብፅን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጣለሁ፤ ሀብቷን ሁሉ ያግዛል፤ ለሰራዊቱም ደመወዝ ይሆን ዘንድ ምድሪቱን ይበዘብዛል፤ ይመዘብራልም። 20እርሱና ሰራዊቱ ለእኔ በመልፋታቸው፣ ግብፅን ለድካሙ ዋጋ ሰጥቼዋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር

21“በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድ29፥21 ቀንድ በዚህ ቦታ ጥንካሬን ያመለክታል አበቅላለሁ፤ በመካከላቸውም አፍህን እከፍታለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”

New International Reader’s Version

Ezekiel 29:1-21

A Prophecy Against Egypt

1It was the tenth year since King Jehoiachin had been brought to Babylon as a prisoner. On the 12th day of the tenth month, a message from the Lord came to me. The Lord said, 2“Son of man, turn your attention to Pharaoh Hophra. He is king of Egypt. Prophesy against him and the whole land of Egypt. 3Tell him, ‘The Lord and King says,

“ ‘ “Pharaoh Hophra, I am against you.

King of Egypt, you are like a huge monster

lying among your streams.

You say, ‘The Nile River belongs to me.

I made it for myself.’

4But I will put hooks in your jaws.

I will make the fish in your streams

stick to your scales.

I will pull you out from among your streams.

All the fish will stick to your scales.

5I will leave you out in the desert.

All the fish in your streams

will be there with you.

You will fall down in an open field.

You will not be picked up.

I will feed you to the wild animals

and to the birds in the sky.

6Then everyone who lives in Egypt will know that I am the Lord.

“ ‘ “You have been like a walking stick made out of a papyrus stem. The people of Israel tried to lean on you. 7They took hold of you. But you broke under their weight. You tore open their shoulders. The people of Israel leaned on you. But you snapped in two. And their backs were broken.” ’ ”

8So the Lord and King says, “I will send Nebuchadnezzar’s sword against you. He will kill people and animals alike. 9Egypt will become a dry and empty desert. Then your people will know that I am the Lord.

“You said, ‘The Nile River belongs to me. I made it for myself.’ 10So I am against you and your streams. I will destroy the land of Egypt. I will turn it into a dry and empty desert from Migdol all the way to Aswan. I will destroy everything as far as the border of Cush. 11No people or animals will travel through Egypt. No one will even live there for 40 years. 12Egypt will be more empty than any other land. Its destroyed cities will lie empty for 40 years. I will scatter the people of Egypt among the nations. I will send them to other countries.”

13But here is what the Lord and King says. “At the end of 40 years I will gather the Egyptians together. I will bring them back from the nations where they were scattered. 14I will bring them back from where they were taken as prisoners. I will return them to Upper Egypt. That is where their families came from. There they will be an unimportant kingdom. 15Egypt will be the least important kingdom of all. It will never place itself above the other nations again. I will make it very weak. Then it will never again rule over the nations. 16The people of Israel will no longer trust in Egypt. Instead, Egypt will remind them of how they sinned when they turned to it for help. Then they will know that I am the Lord and King.”

17It was the 27th year since King Jehoiachin had been brought to Babylon as a prisoner. On the first day of the first month, a message from the Lord came to me. Here is what the Lord said. 18“Son of man, King Nebuchadnezzar drove his army in a hard military campaign. The campaign was against Tyre. Their helmets rubbed their heads bare. The heavy loads they carried made their shoulders raw. But he and his army did not gain anything from the campaign he led against Tyre. 19So I am going to give Egypt to Nebuchadnezzar, the king of Babylon. He will carry off its wealth. He will take away anything else they have. He will give it to his army. 20I have given Egypt to him as a reward for his efforts. After all, he and his army attacked Egypt because I told them to,” announces the Lord and King.

21“When Nebuchadnezzar wins the battle over Egypt, I will make the Israelites strong again. Ezekiel, I will open your mouth. And you will be able to speak to them. Then they will know that I am the Lord.”