ሕዝቅኤል 12 – NASV & TNCV

New Amharic Standard Version

ሕዝቅኤል 12:1-28

ምርኮው በትእምርት መቅረቡ

1የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 2“የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐመፀኛ ሕዝብ መካከል ተቀምጠሃል፤ የሚያዩበት ዐይን አላቸው፤ ነገር ግን አያዩም፤ የሚሰሙበትም ጆሮ አላቸው፤ ነገር ግን አይሰሙም፤ ዐመፀኛ ሕዝብ ናቸውና።

3“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፤ እነርሱ እያዩህ በቀን ጓዝህን ጠቅልለህ ለመሰደድ ተዘጋጅ፤ ካለህበትም ስፍራ ተነሥተህ ወደ ሌላ ቦታ ሂድ፤ ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም ምናልባት ይህን ያስተውሉታል። 4በቀን እያዩ ጓዝህን እንደ ስደተኛ ጓዝ አውጣው፤ በምሽትም እያዩህ ስደተኛ እንደሚወጣ ውጣ። 5እነርሱ እያዩ ግንቡን ነድለህ ጓዝህን በዚያ አሹልክ። 6በፊታቸው ጓዝህን በትከሻህ ላይ አስቀምጥ፣ በምሽትም ተሸክመህ ውጣ። ለእስራኤል ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።”

7እኔም በታዘዝሁት መሠረት አደረግሁ፤ በቀን ጓዜን ጠቅልዬ እንደ ስደተኛ ጓዝ አወጣሁ፤ በምሽትም ግንቡን በእጄ ነደልሁት፤ እያዩኝም በምሽት ጓዜን በትከሻዬ ላይ ተሸክሜ አወጣሁ።

8በማግስቱም ጧት የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 9“የሰው ልጅ ሆይ፤ ዐመፀኛው የእስራኤል ቤት፣ ‘ይህ የምታደርገው ምንድን ነው?’ ብለው ጠይቀውህ አልነበረምን?

10“እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህ የትንቢት ቃል በኢየሩሳሌም ለሚኖረው መስፍንና በዚያ ለሚገኙት ለእስራኤል ቤት ሁሉ ነው።’ 11‘እኔ ምልክታችሁ ነኝ’ በላቸው።

“እኔ እንዳደረግሁት፤ እንዲሁ በእነርሱ ይደረግባቸዋል፤ በምርኮኛነትም ተሰድደው ይሄዳሉ።

12“በመካከላቸው ያለው መስፍን በምሽት ጓዙን በትከሻው ተሸክሞ ይወጣል፤ ሾልኮ እንዲሄድ ግንቡ ይነደልለታል፤ ምድሪቱንም እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል። 13መረቤን በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ነገር ግን እርሷን ሳያያት በዚያ ይሞታል። 14በዙሪያው ያሉትን ረዳቶቹንና ወታደሮቹን ሁሉ ወደ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፤ በተመዘዘም ሰይፍ አሳድዳቸዋለሁ።

15“በአሕዛብ መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 16ነገር ግን በሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ስለ ጸያፍ ተግባራቸው ይናገሩ ዘንድ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከሰይፍ ከራብና ከቸነፈር አተርፋለሁ። በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”

17የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 18“የሰው ልጅ ሆይ፤ ምግብህን በድንጋጤ ብላ፤ ውሃህንም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ ጠጣ። 19ለምድሪቱ ሕዝብ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በእስራኤል ምድር ስለሚኖሩት እንዲህ ይላል፤ በዚያ ከሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ዐመፅ የተነሣ ምድራቸው ስለምትራቈት፣ ምግባቸውን በጭንቀት ይመገባሉ፤ ውሃቸውንም በፍርሀት ይጠጣሉ። 20ሰው ይኖርባቸው የነበሩ ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”

21የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 22“የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል ምድር፣ ‘ዘመኑ ረዝሟል፤ ራእዩ ሁሉ ከንቱ ሆኗል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው? 23እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህን አባባል እሽራለሁ፤ በእስራኤልም ምድር ዳግመኛ በንግግራቸው አይጠቀሙበትም”። እንዲህም በላቸው፤ “ራእዩ ሁሉ የሚፈጸምበት ጊዜ ቀርቧል፤ 24በእስራኤል ሕዝብ መካከል ከእንግዲህ ሐሰተኛ ራእይና አሳሳች ሟርት አይገኝምና። 25ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ሳይዘገይ ይፈጸማል፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ፤ የተናገርሁትን ሁሉ በዘመናችሁ እፈጽማለሁ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

26የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ 27“የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት፣ ‘ይህ ሰው የሚያየው ራእይ ገና ለሩቅ ዘመን የሚሆን ነው፤ የሚናገረውም ትንቢት የረዥም ጊዜ ትንቢት ነው’ ይላሉ።

28“ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከተናገርሁት ቃል ከእንግዲህ የሚዘገይ የለም፤ የምለው ሁሉ ይፈጸማል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

Thai New Contemporary Bible

เอเสเคียล 12:1-28

สัญลักษณ์ของการตกเป็นเชลย

1พระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงข้าพเจ้าความว่า 2“บุตรมนุษย์เอ๋ย เจ้าอาศัยอยู่ท่ามกลางคนชอบกบฏ ซึ่งมีตาแต่มองไม่เห็น มีหูแต่ไม่ได้ยิน เพราะพวกเขาเป็นคนชอบกบฏ

3“ฉะนั้น บุตรมนุษย์เอ๋ย จงเก็บข้าวของเตรียมตัวอพยพในเวลากลางวัน ในขณะที่พวกเขาเฝ้าดูอยู่ จงออกเดินทางจากที่ที่เจ้าอยู่ไปยังอีกที่หนึ่ง เผื่อบางทีพวกเขาจะเข้าใจ แม้พวกเขาจะเป็นพงศ์พันธุ์ที่ชอบกบฏ 4ในเวลากลางวัน ขณะที่พวกเขาเฝ้าดูอยู่ จงนำข้าวของสัมภาระที่เจ้าเก็บไว้เพื่อการอพยพออกมา และในตอนเย็น ขณะที่พวกเขาเฝ้าดูอยู่ จงออกเดินทางไปเหมือนคนที่ถูกกวาดต้อนไปเป็นเชลย 5ขณะที่พวกเขาเฝ้าดูอยู่ จงเจาะช่องที่กำแพงบ้านและแบกสัมภาระลอดกำแพงไป 6จงหอบสัมภาระขึ้นบ่าขณะที่พวกเขากำลังเฝ้าดูอยู่ และแบกไปยามพลบค่ำ จงคลุมหน้าเจ้าไว้เพื่อเจ้าจะมองไม่เห็นแผ่นดิน เพราะเราทำให้เจ้าเป็นหมายสำคัญแก่พงศ์พันธุ์อิสราเอล”

7ดังนั้นข้าพเจ้าจึงปฏิบัติตามพระบัญชา ข้าพเจ้านำข้าวของออกมาจัดหีบห่อเตรียมอพยพในตอนกลางวัน ครั้นตกเย็นข้าพเจ้าเจาะกำแพงบ้านด้วยมือ พอพลบค่ำข้าพเจ้าก็หอบสัมภาระใส่บ่าแบกออกไปขณะที่พวกเขาเฝ้าดูอยู่

8เช้าวันรุ่งขึ้นพระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงข้าพเจ้าความว่า 9“บุตรมนุษย์เอ๋ย พงศ์พันธุ์อิสราเอลที่ชอบกบฏถามเจ้าไม่ใช่หรือว่า ‘เจ้ากำลังทำอะไร?’

10“จงบอกพวกเขาว่า ‘พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตตรัสดังนี้ว่า พระดำรัสนี้พยากรณ์ถึงเจ้านายคนนั้นในเยรูซาเล็มกับพงศ์พันธุ์อิสราเอลทั้งปวงที่นั่น’ 11จงกล่าวแก่พวกเขาว่า ‘ข้าพเจ้าเป็นหมายสำคัญสำหรับท่าน’

“สิ่งนี้จะต้องเกิดขึ้นกับพวกเขาอย่างที่ข้าพเจ้าได้ทำให้เห็นนั้น พวกเขาจะต้องอพยพไปในฐานะเชลย

12“เจ้านายในหมู่พวกเขาจะหอบข้าวของใส่บ่ายามพลบค่ำ และออกเดินทางผ่านช่องซึ่งขุดไว้ในกำแพง เขาจะคลุมหน้าไว้เพื่อเขาจะมองไม่เห็นแผ่นดิน 13เราจะกางตาข่ายดัก แล้วเขาจะติดกับของเรา เราจะนำเขาไปยังบาบิโลนดินแดนแห่งชาวเคลเดีย แต่เขาจะไม่ได้เห็นมันและเขาจะตายที่นั่น 14เราจะทำให้ผู้รับใช้และทหารทุกคนที่อยู่รอบตัวเขากระจัดกระจายไปกับสายลม และเราจะส่งดาบมารุกไล่พวกเขา

15“พวกเขาจะรู้ว่าเราคือพระยาห์เวห์เมื่อเราขับไล่พวกเขาไปยังชนชาติต่างๆ และทำให้พวกเขากระจัดกระจายไปยังนานาประเทศ 16แต่เราจะไว้ชีวิตพวกเขาบางคนให้รอดจากสงคราม การกันดารอาหาร และโรคระบาด เพื่อขณะที่พวกเขาอยู่ท่ามกลางชนชาติต่างๆ พวกเขาจะสำนึกถึงการกระทำอันน่าชิงชังทั้งสิ้นของตน แล้วพวกเขาจะรู้ว่าเราคือพระยาห์เวห์”

17พระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงข้าพเจ้าว่า 18“บุตรมนุษย์เอ๋ย จงตัวสั่นงันงกขณะที่เจ้ากินอาหาร และสั่นสะท้านด้วยความกลัวขณะดื่มน้ำ 19จงกล่าวแก่ประชากรในแผ่นดินนั้นว่า ‘พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตตรัสว่า บรรดาผู้อาศัยอยู่ในเยรูซาเล็มและในแผ่นดินอิสราเอลจะกินอาหารอย่างวิตกกังวลและดื่มน้ำอย่างสิ้นหวัง เพราะทุกสิ่งในดินแดนของตนจะถูกริบไป เนื่องด้วยความทารุณอำมหิตของบรรดาคนอาศัยอยู่ที่นั่น 20เมืองที่อาศัยอยู่จะถูกทำลายและแผ่นดินจะถูกทิ้งร้าง เมื่อนั้นเจ้าจะรู้ว่าเราคือพระยาห์เวห์’ ”

21พระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงข้าพเจ้าความว่า 22“บุตรมนุษย์เอ๋ย ภาษิตในอิสราเอลที่ว่า ‘วันคืนผ่านไป ไม่เห็นมีสักนิมิตที่เป็นจริง’ นั้นเจ้าหมายความว่าอะไร? 23จงกล่าวแก่คนทั้งหลายว่า ‘พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตตรัสดังนี้ว่า เรากำลังจะยุติภาษิตนี้ คนทั้งหลายจะไม่อ้างภาษิตนี้ในอิสราเอลอีกต่อไป’ จงกล่าวแก่พวกเขาว่า ‘วันคืนที่ทุกนิมิตจะเป็นจริงใกล้เข้ามาแล้ว 24เพราะจะไม่มีนิมิตเท็จหรือคำทำนายประจบประแจงในหมู่ชนชาติอิสราเอลอีกต่อไป 25แต่เรา พระยาห์เวห์จะพูดในสิ่งที่เราประสงค์ และจะเป็นจริงตามนั้นโดยไม่ล่าช้า พงศ์พันธุ์ที่ชอบกบฏเอ๋ย ในชั่วอายุของเจ้านี่แหละ เราจะทำสิ่งที่เราพูดไว้ให้สำเร็จ พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตประกาศดังนั้น’ ”

26พระดำรัสขององค์พระผู้เป็นเจ้ามาถึงข้าพเจ้าความว่า 27“บุตรมนุษย์เอ๋ย พงศ์พันธุ์อิสราเอลกล่าวว่า ‘นิมิตที่เขาเห็นเป็นเรื่องอีกหลายปีข้างหน้า เขาพยากรณ์ถึงเรื่องอนาคตที่ยังห่างไกล’

28“ฉะนั้นจงบอกพวกเขาว่า ‘พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตตรัสดังนี้ว่าเราจะไม่ยืดเวลาให้อีกต่อไปแล้ว ทุกสิ่งที่เราลั่นวาจาไว้จะถูกทำให้สำเร็จครบถ้วน พระยาห์เวห์องค์เจ้าชีวิตประกาศดังนั้น’ ”