ሐጌ 2 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሐጌ 2:1-23

ቃል የተገባው የአዲሱ ቤት ክብር

1በሰባተኛው ወር፣ በሃያ አንደኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤ 2“ለይሁዳ ገዥ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፣ ለሊቀ ካህናቱ ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ፣ ከምርኮ ለተረፈውም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ እንዲህም ብለህ ጠይቃቸው፤ 3‘ይህን ቤት በቀድሞ ክብሩ ሳለ ያየ ከመካከላችሁ ማን አለ? አሁንስ ምን መስሎ ይታያችኋል? ይህ በፊታችሁ ምንም እንዳይደለ የሚቈጠር አይደለምን?’ 4እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ፤ በርታ፤ የሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፤ በርታ፤ እናንተም የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በርቱ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ሥሩ’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር5‘ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ የገባሁላችሁ ቃል ይህ ነው፤ መንፈሴም በመካከላችሁ ይሆናልና አትፍሩ።’

6“ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘በቅርብ ጊዜ እንደ ገና ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕሩንና የብሱን አንድ ጊዜ አናውጣለሁ። 7ሕዝቦችን ሁሉ አናውጣለሁ፤ የሕዝቦችም ሀብት ሁሉ ወደዚህ ይመጣል፤ ይህንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር8‘ብሩ የእኔ ነው፤ ወርቁም የእኔ ነው’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ጸባኦት፤ 9‘የዚህ የአሁኑ ቤት ክብር ከቀድሞው ቤት ክብር ይበልጣል’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ጸባኦት፤ ‘በዚህም ቦታ ሰላምን እሰጣለሁ’ ይላል ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ጸባኦት።”

ተግሣጽና በረከት

10ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር፣ በሃያ አራተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል እንዲህ ሲል መጣ፤ 11እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘ሕጉ ምን እንደሚል ካህናቱን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፤ 12አንድ ሰው የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፣ ያም ዕጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይም ሌላ ምግብ ቢነካ የተቀደሰ ይሆናልን?’ ”

ካህናቱም፣ “የተቀደሰ አይሆንም” ብለው መለሱ።

13ሐጌም፣ “ሬሳ በመንካቱ የረከሰ ሰው፣ ከእነዚህ አንዱን ቢነካ፣ የተነካው ነገር ይረክሳልን?” ሲል ጠየቀ።

ካህናቱም፣ “አዎን፣ ይረክሳል” ሲሉ መለሱ።

14ከዚያም ሐጌ እንዲህ አለ፤ “ ‘ይህ ሕዝብና ይህ ወገንም በፊቴ እንደዚሁ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የእጃቸው ሥራና የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው’።

15“ ‘እንግዲህ ከዛሬ ጀምራችሁ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት የነበረውን ሁኔታ አስተውሉ።2፥15 ወይም ላለፉት ቀናት እንደ ማለት ነው። 16አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ ወደሚሆን የእህል ክምር በመጣ ጊዜ ዐሥር ብቻ አገኘ፤ አምሳ ማድጋ የወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው በሄደ ጊዜ ሃያ ብቻ አገኘ። 17የእጃችሁን ሥራ ሁሉ በዋግ፣ በአረማሞና በበረዶ መታሁት፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም’ ይላል እግዚአብሔር18‘ከዚህ ቀን ጀምሮ፣ ይኸውም ከዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ጀምሮ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት እስከ ተጣለበት ቀን ድረስ ያለውን ዘመን አስተውሉ፤ ልብ ብላችሁም አስቡ፤ 19በጐተራ የቀረ ዘር አሁንም ይገኛልን? የወይኑና የበለሱ ዛፍ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ እስካሁን አላፈሩም።

“ ‘ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’ ”

እግዚአብሔር ለዘሩባቤል የሰጠው ተስፋ

20በወሩ ሃያ አራተኛ ቀን የእግዚአብሔር ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ሐጌ መጣ፤ 21“ለይሁዳ ገዥ ለዘሩባቤል ሰማያትንና ምድርን እንደማናውጥ ንገረው፤ 22የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የባዕዳንን መንግሥታት ኀይል አጠፋለሁ፤ ሠረገሎችንና ሠረገለኞችን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸውም በገዛ ወንድሞቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።

23“ እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ ‘በዚያን ቀን ባሪያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፤ እኔ እወስድሃለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘እንደ ማተሚያ ቀለበቴ አደርግሃለሁ፤ እኔ መርጬሃለሁና’ ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

哈该书 2:1-23

对新殿的应许

1七月二十一日,耶和华对先知哈该说: 2“你去告诉撒拉铁的儿子犹大省长所罗巴伯约撒答的儿子大祭司约书亚和所有的余民, 3‘你们当中有谁见过这殿昔日的荣耀呢?现在你们看这殿如何?看上去岂不是一文不值吗? 4所罗巴伯啊,你要刚强,这是耶和华说的。约撒答的儿子大祭司约书亚啊,你要刚强;这地方的所有百姓啊,你们要刚强。这是耶和华说的。你们要动工,因为我与你们同在。这是万军之耶和华说的。 5这是你们离开埃及时我对你们的应许。不要惧怕,我的灵仍住在你们当中。

6“‘万军之耶和华说,不久,我要再次震动天、地、海洋和旱地。 7万军之耶和华说,我要震动万国,万国的珍宝都要送到这殿,我要使这殿充满荣耀。 8万军之耶和华说,金子是我的,银子也是我的。 9万军之耶和华说,我要使这殿比从前更加荣耀。万军之耶和华说,我要在这地方赐下平安。’”

指出百姓的罪

10大流士王执政第二年九月二十四日,耶和华对先知哈该说: 11“万军之耶和华说,‘你去问祭司, 12如果有人用衣服兜着祭肉,而衣服碰到饼、汤、酒、油或其他食物,这些被衣服碰到的食物会成为圣洁之物吗?’”祭司们答道:“不会。” 13哈该又说:“如果因碰过尸体而变得不洁净的人接触这些食物,这些食物会变得不洁净吗?”祭司答道:“会变得不洁净。” 14于是哈该说:“耶和华说,‘这百姓和这国家在我面前也是如此。他们手中的各样工作和他们在那里所献的都不洁净。’

耶和华应许赐福

15“‘从今以后,你们要回想重建耶和华殿之前的光景。 16那时,有人盼望得到二十斗谷物,却只有十斗。有人盼望得到五十桶酒,榨酒池中却只有二十桶。 17我曾用虫灾、霉灾和冰雹毁灭你们的作物,你们仍没有归向我。这是耶和华说的。 18九月二十四日是我的殿奠定根基的日子。你们要思想这个日子,要认真思想。 19虽然粮仓里没有种子,葡萄树、无花果树、石榴树和橄榄树没结果子,但从今以后,我要赐福给你们。’”

拣选所罗巴伯

20同一天,耶和华第二次对哈该说: 21“你告诉犹大省长所罗巴伯,‘我必震动天地, 22推翻君王的宝座,消灭列国的势力,掀翻他们的战车和驾车的人,使战马跌倒、骑士自相残杀。 23万军之耶和华说,我的仆人撒拉铁的儿子所罗巴伯啊,到那日,我必使你像我盖印的戒指,因为我拣选了你。这是万军之耶和华说的。’”