ሐዋርያት ሥራ 9 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 9:1-43

የሳውል ማመን

9፥1-19 ተጓ ምብ – ሐሥ 22፥3-1626፥9-18

1ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት ለመግደል አሁንም እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤ 2የጌታን መንገድ የሚከተሉትን ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን በዚያ ካገኘ አስሮ ወደ ኢየሩሳሌም ለመውሰድ እንዲችል፣ በደማስቆ ለነበሩት ምኵራቦች ደብዳቤ እንዲሰጠው ሊቀ ካህናቱን ለመነው። 3ደማስቆ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው፣ ብርሃን ከሰማይ ድንገት በዙሪያው አንጸባረቀበት፤ 4እርሱም በምድር ላይ ወደቀ፤ በዚያ ጊዜም “ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ።

5ሳውልም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?” አለው።

እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔማ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። 6አሁንም ተነሥተህ ወደ ከተማዪቱ ግባ፤ ማድረግ የሚገባህም ይነገርሃል።”

7ከሳውል ጋር ይጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንንም ባላዩ ጊዜ፣ አፋቸውን ይዘው ቆሙ። 8ሳውልም ከወደቀበት ተነሥቶ ዐይኑን ሲገልጥ ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት። 9ሦስት ቀንም ታወረ፤ እህል ውሃም አልቀመሰም።

10በደማስቆ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበር፤ ጌታም በራእይ፣ “ሐናንያ” ብሎ ጠራው።

እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፤ እነሆኝ” አለ።

11ጌታም እንዲህ አለው፤ “ተነሣና ‘ቀጥተኛ ጐዳና’ በተባለው መንገድ ይሁዳ ወደ ተባለ ሰው ቤት ሂድ፤ እዚያም ሳውል የሚባል አንድ የጠርሴስ ሰው እየጸለየ ነውና ፈልገው፤ 12ምክንያቱም ሐናንያ የሚባል ሰው እርሱ ወዳለበት መጥቶ እጁን እንደሚጭንበትና ዐይኑ እንደሚበራለት በራእይ አይቷል።”

13ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ ሰው እኮ በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳንህ ላይ ምን ያህል ጕዳት እንዳደረሰ ከብዙ ሰው ሰምቻለሁ፤ 14ወደዚህም የመጣው ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብሎ ነው።”

15ጌታም እንዲህ አለው፤ “ሂድ፤ ይህ ሰው በአሕዛብና በነገሥታት ፊት እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ስሜን እንዲሸከም የተመረጠ ዕቃዬ ነው፤ 16እኔም ስለ ስሜ ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበት አሳየዋለሁ።”

17ሐናንያ ሄዶ፣ ወደተባለውም ቤት ገባ፤ በሳውልም ላይ እጁን ጭኖ፣ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፤ ወደዚህ ስትመጣ በመንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ፣ ዐይንህ እንዲበራና በመንፈስ ቅዱስም እንድትሞላ እኔን ልኮኛል” አለው። 18ወዲያውም ከሳውል ዐይን ላይ ቅርፊት የመሰለ ነገር ወደቀ፤ እንደ ገና ማየት ቻለ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፤ 19ምግብም በልቶ በረታ።

ሳውል በደማስቆና በኢየሩሳሌም

ሳውል በደማስቆ ከነበሩት ደቀ መዛሙርት ጋር አያሌ ቀን ተቀመጠ። 20ወዲያውም፣ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በየምኵራቦቹ መስበክ ጀመረ። 21የሰሙትም ሁሉ በመገረም፣ ይህ ሰው “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሲያጠፋ የነበረ አይደለምን? ደግሞም ወደዚህ የመጣው እነርሱን አስሮ ወደ ካህናት አለቆች ሊወስዳቸው አልነበረምን?” አሉ። 22ሳውል ግን እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆ ለሚኖሩትም አይሁድ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ9፥22 ወይም መሲሕ መሆኑን ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር።

23ከብዙ ቀንም በኋላ፣ አይሁድ ሳውልን ለመግደል አሤሩ፤ 24እርሱ ግን ዕቅዳቸውን ዐውቆ ነበር፤ እነርሱም ሊገድሉት የከተማዋን በር ቀንና ሌሊት ይጠብቁ ነበር፤ 25የእርሱ ተከታዮች ግን በሌሊት በከተማዋ ቅጥር ቀዳዳ አሹልከው በቅርጫት አወረዱት።

26ሳውልም ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርት ጋር ለመቀላቀል ሞከረ፤ እነርሱ ግን በርግጥ ደቀ መዝሙር መሆኑን ስላላመኑ ሁሉም ፈሩት። 27ይሁን እንጂ በርናባስ ወስዶ ወደ ሐዋርያት አመጣው፤ ሳውልም በጕዞው ላይ ሳለ ጌታን እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንዴት እንደ ተናገረው እንዲሁም በደማስቆ የጌታን ስም እንዴት በድፍረት እንደ ሰበከ ነገራቸው። 28ስለዚህ ሳውል አብሯቸው ተቀመጠ፤ በኢየሩሳሌምም በመዘዋወር በጌታ ስም በድፍረት ይናገር ነበር። 29ከግሪክ አገር ከመጡት አይሁድ ጋር እየተነጋገረ ይከራከር ነበር፤ እነርሱ ግን ሊገድሉት ጥረት ያደርጉ ነበር። 30ወንድሞችም ይህን ባወቁ ጊዜ፣ ወደ ቂሳርያ አውርደው ወደ ጠርሴስ ሰደዱት።

31በዚህ ጊዜ በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ ያለችው ቤተ ክርስቲያን በሰላም መኖር ጀመረች፤ ተጠናከረችም። ደግሞም እግዚአብሔርን በመፍራት እየተመላለሰችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቍጥር እየበዛች ሄደች።

ኤንያና ዶርቃ

32ጴጥሮስም ከአገር ወደ አገር በሚዘዋወርበት ጊዜ፣ በልዳ የሚኖሩትን ቅዱሳን ለመጐብኘት ወረደ። 33በዚያም ኤንያ የተባለ፣ ስምንት ዓመት የዐልጋ ቍራኛ የነበረ አንድ ሽባ ሰው አገኘ። 34ጴጥሮስም፣ “ኤንያ ሆይ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣና መኝታህን አንጥፍ” አለው። ኤንያም ወዲያውኑ ብድግ አለ። 35በልዳና በሰሮና የሚኖሩትም ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ተመለሱ።

36በኢዮጴ ጣቢታ የተባለች አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟም ትርጓሜ ዶርቃ9፥36 ጣቢታ በአረማይክ ሲሆን፣ ዶርቃ ደግሞ በግሪክ ነው፤ ትርጕሙም ፌቆ (ሚዳቋ) ማለት ነው። ማለት ነው። እርሷም ዘወትር በትጋት በጎ ነገር እያደረገችና ድኾችን እየረዳች ትኖር ነበር። 37በዚያ ጊዜም ታምማ ሞተች፤ ሰዎችም አስከሬኗን ዐጥበው በሰገነት ላይ ባለው ክፍል አስቀመጡት። 38ልዳ ለኢዮጴ ቅርብ ስለ ነበረች፣ ደቀ መዛሙርትም ጴጥሮስ በልዳ መሆኑን በሰሙ ጊዜ ሁለት ሰዎች ልከው፣ “እባክህ ፈጥነህ ወደ እኛ ና!” ሲሉ ለመኑት።

39ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ እዚያ በደረሰ ጊዜም ሰገነት ላይ ወዳለው ክፍል አወጡት። መበለቶቹም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር በነበረችበት ጊዜ ያደረገቻቸውን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩት ዙሪያውን ከብበው ያለቅሱ ነበር።

40ጴጥሮስም ሁሉንም ከክፍሉ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፤ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ፣ “ጣቢታ፤ ተነሺ” አለ። እርሷም ዐይኗን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች፤ 41እርሱም እጇን ይዞ አስነሣት፤ አማኞችንና መበለቶቹንም ጠርቶ ከነሕይወቷ አስረከባቸው። 42ይህም ነገር በመላው ኢዮጴ ታወቀ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ። 43ጴጥሮስም ስምዖን ከተባለ ከአንድ ቍርበት ፋቂ ጋር በኢዮጴ ብዙ ቀን ተቀመጠ።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

使徒行傳 9:1-43

掃羅歸主

1掃羅繼續用兇狠的話恐嚇主的門徒。他去見大祭司, 2要取得授權書到大馬士革的各會堂搜捕信耶穌的人,無論男女,都要把他們押回耶路撒冷

3當他快到大馬士革的時候,突然有一道光從天上射下來,四面照著他。 4他倒在地上,聽見有聲音對他說:「掃羅掃羅!你為什麼迫害我?」 5他說:「主啊,你是誰?」那聲音說:「我就是你所迫害的耶穌。 6起來!進城去,有人會告訴你該做的事。」

7同行的人站在那裡只聽見聲音,卻看不見人,嚇得張口結舌。 8掃羅爬起來,睜大眼睛,卻什麼也看不見,同伴拉著他的手進了大馬士革9一連三天,掃羅什麼也看不見,也不吃也不喝。

10這時候,在大馬士革有個門徒名叫亞拿尼亞,他在異象中聽見主呼喚他的名字,就回答說:「主啊,我在這裡。」

11主說:「起來,到直街的猶大家去見一個來自大數、名叫掃羅的人,他正在向我禱告。 12我讓他在異象中看見一個名叫亞拿尼亞的人去他那裡,把手按在他身上,使他恢復視力。」

13亞拿尼亞回答說:「主啊!我聽見許多人說他對耶路撒冷的信徒大加迫害。 14他來這裡是得到祭司長的授權,要拘捕所有求告你名的人。」

15主對亞拿尼亞說:「你放心去吧!他是我揀選的器皿,要向外族人、君王和以色列人宣揚我的名。 16我會讓他知道他必為我的名而受許多的苦。」

17亞拿尼亞去了,進了那家,就把手按在掃羅身上,說:「掃羅弟兄,在你來的路上向你顯現的主耶穌派我來使你重見光明、被聖靈充滿。」 18頓時,掃羅的眼睛上有鱗片似的東西脫落,他立刻恢復了視力,便起來接受了洗禮。 19他吃過東西之後,體力也恢復了。他和大馬士革的門徒住了幾天之後, 20便到各會堂去宣講:「耶穌是上帝的兒子。」

21聽的人都大吃一驚,說:「他不就是那在耶路撒冷迫害信徒的人嗎?他到這裡來不是要把大馬士革的信徒押去見祭司長嗎?」

22掃羅越發有能力,引經據典證明耶穌是基督,使大馬士革猶太人驚慌失措。

掃羅逃生

23過了一段日子,猶太人圖謀殺死掃羅24他們晝夜在城門守候,伺機下手,但這陰謀被掃羅知道了。 25他的門徒趁夜間用筐子把他從城牆上縋下去。

26掃羅逃到耶路撒冷後,曾設法與當地的門徒聯絡,可是他們都怕他,不相信他是門徒。 27只有巴拿巴接待他,帶他去見使徒,向他們陳述掃羅如何在路上遇見主,主如何對他說話,他又如何勇敢地在大馬士革奉耶穌的名傳道。 28於是,掃羅就在耶路撒冷與使徒一起出入來往,奉主的名放膽傳道。 29他常常跟那些講希臘話的猶太人辯論,於是他們打算殺掉他。 30弟兄姊妹知道這消息後,就把掃羅帶到凱撒利亞,然後送他到大數去。

31當時,猶太加利利撒瑪利亞各地的教會都很平安,得到了堅固。信徒們非常敬畏主,又得到聖靈的安慰,人數越來越多。

彼得醫治癱子

32彼得四處奔波,來到呂大探訪那裡的信徒, 33遇見一個已經臥床八年、名叫以尼雅的癱子。 34彼得對他說:「以尼雅,耶穌基督已經醫好你了,起來收拾你的墊子吧!」他立刻應聲而起。 35呂大沙崙的居民看見他,都歸向了主。

彼得使死人復活

36約帕有個樂善好施的女信徒名叫戴碧達希臘話叫多加,意思是「羚羊」。 37當時,她患病死了。有人將她的屍體洗乾淨後,停放在樓上。 38呂大約帕相距不遠,門徒聽說彼得呂大,就派兩個人趕去請他立刻來約帕39彼得便隨他們一同到了那裡,有人領他上樓。眾寡婦都站在彼得周圍哭,並把多加生前縫制的內衣、外衣給他看。

40彼得叫她們都出去,自己跪下禱告,然後轉身對死者說:「戴碧達,起來!」她便睜開了眼睛,看見彼得,就坐了起來。 41彼得伸手扶她起來後,叫那些在外面等候的門徒和寡婦進來,把活過來的多加交給他們。 42這事傳遍了整個約帕,許多人都信了主。 43彼得繼續留在約帕,在當地一個名叫西門的皮革匠家住了好些日子。