ሐዋርያት ሥራ 3 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 3:1-26

ጴጥሮስ ሽባውን ለማኝ ፈወሰ

1አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ፣ ይኸውም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር። 2ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት እንዲለምን፣ ሰዎች በየዕለቱ ተሸክመው “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ የሚያስቀምጡት አንድ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበረ፤ 3እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ አይቶ ምጽዋት ለመናቸው። 4ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋር ወደ እርሱ ትኵር ብሎ አየውና፣ “እስቲ ወደ እኛ ተመልከት” አለው። 5ሰውየውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለማግኘት አስቦ በትኵረት ተመለከታቸው።

6ጴጥሮስ ግን፣ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ነገር ግን ያለኝን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ በእግርህ ተመላለስ” አለው፤ 7ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውም እግሩና ቍርጭምጭሚቱ በረታ፤ 8ዘልሎም ቀጥ ብሎ ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ወዲህ ወዲያ እየሄደና እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ገባ። 9ሕዝቡም ሁሉ እየተራመደና እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ ባዩት ጊዜ፣ 10ይህ ሰው ቀደም ሲል “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በእርሱ ላይ ከተፈጸመውም ነገር የተነሣ በመደነቅና በመገረም ተሞሉ።

ጴጥሮስ ሰውየው ሲፈወስ ላየው ሕዝብ ንግግር አደረገ

11የተፈወሰውም ሰው ከጴጥሮስና ዮሐንስ ጋር ጥብቅ ብሎ አብሯቸው ሳለ፣ ሕዝቡ ሁሉ በመገረም እነርሱ ወደ ነበሩበት “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደተባለው ስፍራ እየሮጡ መጡ። 12ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞም በእኛ ኀይል ወይም በእኛ ጽድቅ ይህ ሰው ድኖ እንዲመላለስ እንዳደረግነው በመቍጠር፣ ለምን ወደ እኛ አትኵራችሁ ትመለከታላችሁ? 13የአባቶቻችን አምላክ፣ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው፤ እናንተ ግን እንዲሞት አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ጲላጦስ ሊፈታው ቢፈልግም እናንተ በእርሱ ፊት ካዳችሁት፤ 14ቅዱሱንና ጻድቁን ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ፤ 15የሕይወት መገኛ የሆነውን ገደላችሁት፤ እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው፤ እኛም ለዚህ ምስክሮች ነን። 16ይህ የምታዩትና የምታውቁት ሰው የበረታው በኢየሱስ ስም በማመን ነው፤ ሁላችሁም እንደምታዩት ፍጹም ፈውስ እንዲያገኝ ያደረገው የኢየሱስ ስምና በእርሱ አማካይነት የሚገኘው እምነት ነው።

17“አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ እናንተ ይህን ያደረጋችሁት እንደ አለቆቻችሁ ሁሉ ባለማወቅ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ። 18እግዚአብሔር ግን የእርሱ የሆነው ክርስቶስ3፥18 ወይም መሲሕ፤ እንዲሁም በ20 መከራን እንዲቀበል አስቀድሞ በነቢያቱ ሁሉ አፍ የተናገረውን ፈጽሟል። 19እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤ 20ደግሞም አስቀድሞ ለእናንተ የተመደበውን ክርስቶስን፣ እርሱም ኢየሱስን ይልክላችኋል። 21እግዚአብሔር አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረ፣ ሁሉን ነገር እስከሚያድስበት ዘመን ድረስ እርሱ በሰማይ ይቈይ ዘንድ ይገባል። 22ሙሴም እንዲህ ብሏል፤ ‘ጌታ አምላካችሁ ከእናንተው መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱ የሚነግራችሁን ሁሉ ስሙት፤ 23ይህን ነቢይ የማትሰማ ነፍስ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይታ ትጥፋ።’

24“በርግጥም ከሳሙኤል ጀምሮ የተነሡት ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ጊዜያት ተናግረዋል። 25እናንተም የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ‘በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ የገባው ኪዳን ወራሾች ናችሁ። 26እግዚአብሔር ብላቴናውን ባስነሣ ጊዜ፣ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ መልሶ ይባርካችሁ ዘንድ አስቀድሞ ወደ እናንተ ላከው።”

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

使徒行傳 3:1-26

彼得醫治瘸腿的乞丐

1一天,在下午三點禱告的時間,彼得約翰去聖殿。 2有一個生來瘸腿的人天天被人抬到聖殿美門的外面,向進殿的人乞討。 3他看見彼得約翰要進殿,就求他們施捨。 4二人定睛看他,彼得說:「看著我們!」 5那人就緊盯著他們,期盼能有所收穫。

6彼得說:「金子、銀子我都沒有,但是我把我有的給你。我奉拿撒勒人耶穌基督的名,命令你起來行走!」

7彼得拉著他的右手扶他起來,那人的腳和踝骨立刻變得強健有力。 8他跳了起來,站穩後開始行走,跟著彼得約翰進入聖殿,走著跳著讚美上帝。 9大家看見他一邊走一邊讚美上帝, 10認出他就是那個在美門外面的乞丐,都為發生在他身上的事而感到驚奇、詫異。 11那乞丐緊緊拉著彼得約翰的手走到所羅門廊,眾人都跑過來,嘖嘖稱奇。

彼得傳揚基督

12彼得看見這情形,就對大家說:「以色列人啊,何必驚奇呢?為什麼一直盯著我們呢?你們以為我們是憑自己的能力和虔誠叫這人行走嗎? 13亞伯拉罕以撒雅各的上帝,就是我們祖先的上帝,已經使祂的僕人耶穌得了榮耀。你們把耶穌交給彼拉多,儘管彼拉多想釋放祂,你們卻在彼拉多面前棄絕祂! 14你們棄絕了那聖潔公義者,竟然要求彼拉多釋放一個兇手。 15你們殺了生命之主,上帝卻使祂從死裡復活了。我們都是這事的見證人。 16你們認識的這個乞丐因為相信耶穌的名,得到了醫治。你們都看見了,他能痊癒是因為他信耶穌。

17「弟兄們,我知道你們的所作所為是出於無知,你們的官長也是一樣。 18但是上帝早已藉眾先知預言基督要受害,這事果然應驗了。 19所以你們要悔改,歸向上帝,祂將除去你們一切的罪惡, 20賜給你們煥然一新的日子,也將差遣祂預先為你們選立的基督耶穌降臨。 21基督必須留在天上,直到萬物更新的時候,這是上帝自古以來藉聖先知的口說的。 22摩西曾經說,『主——你們的上帝將要在你們中間興起一位像我一樣的先知。你們要留心聽祂的話, 23凡不聽的,必將他從民中剷除。』

24「從撒母耳到後來的所有先知都宣告過這些日子。 25你們是先知的子孫,也承受了上帝和你們祖先所立的約。上帝曾對亞伯拉罕說,『天下萬族必因你的後裔而蒙福。』 26上帝興起祂的僕人,首先差遣祂到你們中間賜福給你們,使你們脫離罪惡。」