ሐዋርያት ሥራ 27 – NASV & CRO

New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 27:1-44

ጳውሎስ በመርከብ ወደ ሮም ተወሰደ

1ወደ ኢጣሊያ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎቹን እስረኞች የንጉሠ ነገሥቱ ክፍለ ጦር አባል ለሆነው፣ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቧቸው። 2ከአድራሚጢስ ተነሥቶ በእስያ አውራጃ ባሕር ዳርቻ ላይ ወዳሉት ወደቦች በሚሄደው መርከብ ተሳፍረን የባሕር ጕዞ ጀመርን፤ በተሰሎንቄ ይኖር የነበረው የመቄዶንያ ሰው፣ አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ነበረ።

3በሚቀጥለው ቀን ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስም ለጳውሎስ ደግነት በማሳየት ወደ ወዳጆቹ ሄዶ ርዳታ እንዲቀበል ፈቀደለት። 4ከዚያም ተነሥተን በባሕር ተጓዝን፤ ነፋስ ከፊት ለፊት ስለ ገጠመን፣ የቆጵሮስን ደሴት ተገን አድርገን ዐለፍን። 5በኪልቅያና በጵንፍልያ ዳርቻ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላ በሉቅያ አገር ሙራ የተባለ ቦታ ደረስን። 6ከዚያም የመቶ አለቃው ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ የእስክንድርያ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን። 7ብዙ ቀን በዝግታ እየተጓዝን ቀኒዶስ አካባቢ በጭንቅ ደረስን፤ ነፋሱም ወደ ፊት እንዳንሄድ በከለከለን ጊዜ፣ በሰልሙና አጠገብ አድርገን በቀርጤስ ተተግነን ሄድን፤ 8ጥግ ጥጉንም ይዘን፣ በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው፣ “መልካም ወደብ” ወደ ተባለ ስፍራ በጭንቅ ደረስን።

9ብዙ ጊዜ ባክኖ፤ የጾሙ ጊዜ ስላለፈ27፥9 የስርየትን ዕለት ያሳያል። በመርከብ መጓዙ አደገኛ ሆኖ ነበርና ጳውሎስ፣ 10“እናንት ሰዎች፤ ጕዞው አደገኛ እንደሚሆን፣ በመርከቡና በጭነቱ እንዲሁም በእኛ በራሳችን ላይ እንኳ ትልቅ ጕዳት እንደሚደርስ ይታየኛል” ብሎ አስጠነቀቃቸው። 11የመቶ አለቃው ግን ከጳውሎስ ምክር ይልቅ የመርከቡ መሪና የመርከቡ ባለቤት ያሉትን ይሰማ ነበር። 12ክረምቱንም በዚያ ለማሳለፍ ወደቡ አመቺ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ፍንቄ ወደተባለው ወደብ ደርሰው በዚያ ለመክረም ተስፋ በማድረግ ጕዟችንን እንድንቀጥል ውሳኔ አስተላለፉ፤ ወደቡም በቀርጤስ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትይዩ የሚገኝ ነበር።

የባሕሩ ማዕበል

13መጠነኛ የደቡብ ነፋስ በነፈሰ ጊዜም እንዳሰቡት የሆነላቸው መስሏቸው መልሕቁን ነቅለው፣ የቀርጤስን ዳርቻ በመያዝ ተጓዙ። 14ብዙም ሳይቈይ ግን፣ “ሰሜናዊ ምሥራቅ” የሚሉት ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ከደሴቲቱ ተነሥቶ ቍልቍል መጣባቸው። 15መርከቢቱም በማዕበሉ ስለ ተያዘች፣ ወደ ነፋሱ መግፋት አልቻለችም፤ ስለዚህ መንገድ ለቅቀን በነፋሱ ተነዳን። 16ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተገን አድርገን በማለፍ፣ የመርከቧን ሕይወት አድን ጀልባ በብዙ ድካም ለማትረፍ ቻልን፤ 17ጀልባዋንም ወደ ላይ ጐትተው ካወጧት በኋላ መርከቧ እንዳትፈራርስ ዙሪያዋን በገመድ ጠምጥመው አሰሯት፤ ስርቲስ ከተባለው አሸዋማ ደለል ጋር ሄደው እንዳይላተሙ ስለ ፈሩም፣ የመርከቧን ሸራ አውርደው እንዲሁ በዘፈቀደ እንድትነዳ አደረጉ። 18ማዕበሉም ክፉኛ ስላንገላታን፣ በማግስቱም ጭነቱን እያነሡ ወደ ባሕር ይጥሉ ጀመር፤ 19በሦስተኛውም ቀን፣ የመርከቧን ሸራ ማውጫና ማውረጃ መሣሪያ በገዛ እጃቸው ነቃቅለው ወደ ባሕር ጣሉት። 20ብዙ ቀን፣ ፀሓይንም ከዋክብትንም ማየት ስላልተቻለና ነፋስ ስለ በረታብን፣ ለመትረፍ የነበረን ተስፋ ሁሉ ተሟጠጠ።

21ሰዎቹ እህል ሳይቀምሱ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ፣ ጳውሎስ በመካከላቸው ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንት ሰዎች ሆይ፤ የነገርኋችሁን ሰምታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ ከቀርጤስ ባልተነሣችሁና ይህ ጕዳትና ጥፋት ባልደረሰባችሁ ነበር። 22አሁንም ቢሆን አይዟችሁ፤ መርከቧ እንጂ ከእናንተ አንዲት ነፍስ እንኳ አትጠፋምና። 23በትላንትናዋ ሌሊት፣ የእርሱ የሆንሁትና የማመልከው እግዚአብሔር የላከው መልአክ በአጠገቤ ቆሞ፣ 24‘ጳውሎስ ሆይ፤ አትፍራ፤ በቄሳር ፊት መቆም ይገባሃል፤ ከአንተ ጋር የሚጓዙትንም ሰዎች ሕይወት እግዚአብሔር አትርፎልሃል’ አለኝ። 25ስለዚህ፣ እናንት ሰዎች ሆይ፤ አይዟችሁ እርሱ እንደ ነገረኝ እንደዚያው እንደሚሆን በእግዚአብሔር አምናለሁና። 26ይሁን እንጂ፣ ወደ አንዲት ደሴት በነፋስ ተወስደን እዚያ መጣላችን አይቀርም።”

በመርከቡ አደጋ መድረሱ

27በዐሥራ አራተኛው ሌሊት በአድርያ27፥27 በጥንት ጊዜ ይህ ስም ሰፊውን የኢጣሊያ ደቡባዊ ክፍል ያመለክታል። ባሕር ላይ ከወዲያ ወዲህ ስንገላታ፣ እኩለ ሌሊት ገደማ መርከበኞቹ ወደ መሬት የተቃረቡ መሰላቸው፤ 28የጥልቀት መለኪያውን ገመድ ወደ ታች ጥለው ሲመለከቱት የውሃው ጥልቀት አርባ ሜትር ያህል ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ደግመው ሲጥሉ ጥልቀቱ፣ ሠላሳ ሜትር ያህል ሆነ። 29ከቋጥኞቹም ጋር እንዳንላተም በመፍራት፣ አራት መልሕቆች ከመርከቡ በስተ ኋላ ጣሉ፤ ምነው በነጋ እያሉም ይለምኑ ነበር። 30መርከበኞቹም ከመርከቡ በስተ ፊት መልሕቅ የሚጥሉ መስለው፣ ትንሿን ጀልባ በማውረድ ከመርከቧ ሊያመልጡ ሞከሩ። 31ጳውሎስም የመቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች መርከቡ ላይ ካልቈዩ እናንተም ልትተርፉ አትችሉም” አላቸው። 32በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ገመዶቹን ቈርጠው ትንሿ ጀልባ ባሕሩ ላይ ተንሳፍፋ እንድትቀር ለቀቋት።

33ልክ ሊነጋጋ ሲል፣ ጳውሎስ ሁሉም ምግብ እንዲበሉ እንዲህ ሲል ለመናቸው፤ “ዐሥራ አራት ቀን ሙሉ ልባችሁ ተንጠልጥሎ ምንም ሳትቀምሱ ጦማችሁን ሰነበታችሁ፤ 34ስለዚህ፣ ስለሚያበረታችሁ አሁን እህል እንድትቀምሱ እለምናችኋላሁ፤ ከእናንተ መካከል ከራሱ ጠጕር አንዲት እንኳ የሚነካበት ማንም የለምና።” 35ይህን ካለ በኋላም፣ እንጀራ ይዞ በሁሉም ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ቈርሶም ይበላ ጀመር። 36ሁሉም ተበራቱና እንጀራውን ራሳቸው ወስደው በሉ። 37በመርከቡም ላይ በአጠቃላይ ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሰዎች ነበርን። 38በልተውም ከጠገቡ በኋላ ስንዴውን ወደ ባሕር በመጣል የመርከቡን ክብደት አቃለሉ።

39በነጋም ጊዜ፣ ወደ የብስ መቅረባቸውን አላወቁም ነበር፤ ነገር ግን ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባሕር ሰርጥ አይተው፣ ቢቻላቸው መርከቡን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ። 40ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ። 41ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቍልል ጋር ተላትሞ መሬት ነካ፤ የፊተኛው ክፍሉም አሸዋው ውስጥ ተቀርቅሮ አልነቃነቅ አለ፤ የኋለኛው ክፍሉም በማዕበሉ ክፉኛ ስለ ተመታ ይሰባበር ጀመር።

42ወታደሮቹም ከእስረኞች ማንም ዋኝቶ ለማምለጥ ቢሞክር ለመግደል ተስማሙ። 43የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስ እንዲተርፍ ስለ ፈለገ፣ ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ ከለከላቸው፤ መዋኘት የሚችሉ ከመርከብ እየዘለሉ አስቀድመው ከባሕሩ ወደ ምድር እንዲወጡ፣ 44የተቀሩት ደግሞ በሳንቃዎች ወይም በመርከቡ ስብርባሪ እየተንጠላጠሉ እንዲወጡ አዘዘ። በዚህ መንገድ ሁሉም በደኅና ወደ ምድር ደረሱ።

Knijga O Kristu

Djela Apostolska 27:1-44

Pavao plovi u Rim

1Odlučeno je da odjedrimo u Italiju. Pavla i nekolicinu drugih zatvorenika predali su stotniku carske čete Juliju. 2Ukrcali smo se na neku adramitsku lađu koja je plovila u azijska mjesta te otplovili. S nama je bio i neki Makedonac, Aristarh iz Soluna.

3Sutradan smo doplovili u Sidon. Julije je s Pavlom vrlo ljubazno postupao. Dopustio mu je posjetiti prijatelje, da se pobrinu za njegove potrebe. 4Otplovili smo dalje jedreći sjeverno uz Cipar između otoka i kopna jer su puhali suprotni vjetrovi. 5Prošli smo uz cilicijsku i pamfilijsku obalu te stigli u grad Miru u Liciji. 6Ondje stotnik pronađe neku lađu što je iz Aleksandrije plovila u Italiju, pa nas ukrca na nju.

7Nekoliko smo dana sporo plovili i jedva došli do Knida. Kako od vjetra nismo mogli pristati, otplovili smo pod Kretu, do Salmone, 8pa na jedvite jade uz nju do nekoga mjesta zvanog Dobra pristaništa, blizu grada Laseje. 9Mnogo smo vremena izgubili. Plovidba je postala vrlo opasnom jer je već bila jesen,27:9 U grčkome: jer je post (obično koncem rujna ili početkom listopada) već prošao. a Pavao upozori:

10“Ljudi, vidim da će plovidba biti pogibeljna i da ćemo pretrpjeti veliku štetu—ne samo u teretu nego i u našim životima.” 11Ali stotnik je više vjerovao kormilaru i vlasniku broda nego Pavlu. 12Kako luka nije bila prikladna za zimovanje, većina je ljudi predlagala da otplove i pokušaju doći do luke Feniks na Kreti, otvorenoj prema jugozapadu i sjeverozapadu, te da ondje prezimimo.

Oluja na moru

13Tada puhne blagi južnjak te oni, misleći da bi mogli uspjeti u toj nakani, dignu sidro i zaplove uz samu obalu Krete. 14Ali ubrzo zatim silovito zapuše žestok vjetar zvani sjeveroistočnjak. 15Zahvati lađu tako da mu se nije mogla oteti, pa smo se prepustili da nas nosi.

16Kad smo prolazili uz neki otočić zvan Kauda, jedva smo na brod podignuli čamac za spašavanje koji smo vukli za sobom. 17Podignuli su ga da uporabe opremu za spašavanje i da konopcima potpašu lađu. Bojeći se da se ne nasuču na Sirtu uz afričku obalu, spuste plivajuće sidro te smo tako plovili dalje nošeni vjetrom.

18Kako nas je oluja silovito bacala, sutradan izbace s broda teret, 19a treći dan brodsku opremu i sve čega su se domogli. 20Strašna je oluja bjesnjela mnogo dana te se nisu mogli vidjeti ni sunce ni zvijezde. Gubili smo svaku nadu da ćemo se spasiti.

21Dugo već nismo ništa jeli. Pavao stane pred posadu i reče: “Trebali ste me, ljudi, poslušati i ne odlaziti s Krete pa biste izbjegli svu ovu nevolju i štetu. 22Ali sada vam kažem: budite odvažni jer nitko od nas neće stradati iako će lađa potonuti. 23Noćas mi se ukazao anđeo Boga kojemu pripadam i služim 24te mi rekao: ‘Ne boj se, Pavle, jer ćeš sigurno stići pred cara! A Bog ti daruje i da svi tvoji suputnici sigurno doputuju.’ 25Zato se, ljudi, razvedrite! Vjerujem Bogu. Bit će kako mi je rekao. 26Ali nasukat ćemo se na neki otok.”

Brodolom

27Četrnaeste noći oluje, oko ponoći, vjetar nas je gonio amo-tamo po Jadranu. Mornari naslute da se približava nekakvo kopno. 28Bace olovnicu i izmjere dvadeset hvati dubine. Malo zatim opet ju bace i izmjere petnaest hvati. 29Prestraše se da ne nalete na grebene pa bace s krme četiri sidra i počnu se moliti da se brzo razdani. 30Mornari su kanili pobjeći s lađe pa počnu spuštati čamac u more pod izlikom da kane spustiti sidra s pramca. 31Ali Pavao reče stotniku i vojnicima: “Ne ostanu li oni na lađi, nećete se spasiti!” 32Vojnici prerežu užad i puste da čamac padne u more.

33Sve do svanuća Pavao je molio ljude da jedu. “Četrnaest dana niste ni taknuli jelo”, reče. 34“Molim vas, pojedite što za vlastito dobro. Jer neće vam pasti ni vlas s glave.” 35Kad je to rekao, uzme kruh te pred svima zahvali Bogu, razlomi ga i počne jesti. 36Svi se razvedre i uzmu hranu. 37U lađi nas je bilo dvjesto sedamdeset šest duša. 38Kad su se najeli, počnu rasterećivati lađu bacajući žito u more.

39Kad se razdanilo, mornari nisu prepoznali obalu, ali opazili su neki zaljev ravne obale te odluče pokušati onamo zavesti lađu. 40Odvežu zato sidra i puste da padnu u more. Popuste konopce na kormilima i razviju prednje jedro prema vjetru te se usmjere prema obali. 41Ali nalete na plićak i brod se nasuče. Pramac nasjedne i ostane nepomičan, a krmu su razbijali žestoki valovi.

42Vojnici nakane poubijati zatvorenike da koji ne otpliva i ne pobjegne, 43ali im stotnik, želeći poštedjeti Pavla, ne dopusti da to učine. Zapovjedi da oni koji znaju plivati prvi skoče u more i otplivaju do obale, 44a ostalima reče da doplivaju na daskama i olupinama lađe. Tako su svi živi i zdravi dospjeli na kopno.