ሐዋርያት ሥራ 16 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ሐዋርያት ሥራ 16:1-40

ጢሞቴዎስ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተሰማራ

1ጳውሎስ ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራን ደረሰ። በዚያም እናቱ አይሁዳዊት ሆና በጌታ ያመነች፣ አባቱ ግን የግሪክ ሰው የሆነ፣ ጢሞቴዎስ የተባለ አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ። 2እርሱም በልስጥራንና በኢቆንዮን በነበሩት ወንድሞች ዘንድ መልካም ምስክርነት ነበረው። 3ጳውሎስም ይህ ሰው ከእርሱ ጋር እንዲሄድ ፈለገ፤ ስለዚህ በዚያ አካባቢ በነበሩ አይሁድ ምክንያት ይዞ ገረዘው፤ እነዚህ አይሁድ በሙሉ የጢሞቴዎስ አባት የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና። 4እነርሱም ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላው በሚያልፉበት ጊዜ፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በኢየሩሳሌም ያሳለፉትን ውሳኔ ተቀብለው እንዲጠብቁ ለምእመናኑ ይሰጡ ነበር። 5አብያተ ክርስቲያናትም በእምነት እየበረቱና ዕለት ዕለትም በቍጥር እየጨመሩ ይሄዱ ነበር።

ጳውሎስ ስለ መቄዶንያው ሰው ያየው ራእይ

6ጳውሎስና ባልደረቦቹ ቃሉን በእስያ እንዳይሰብኩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው፣ በፍርግያና በገላትያ አገር ዐልፈው ሄዱ። 7ወደ ሚስያም በተቃረቡ ጊዜ፣ ወደ ቢታኒያ ሊገቡ ሞከሩ፤ ነገር ግን የኢየሱስ መንፈስ አልፈቀደላቸውም። 8ስለዚህ በሚስያ በኩል አድርገው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ። 9ጳውሎስም ሌሊት በራእይ አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” ብሎ ሲለምነው አየ። 10ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ፣ እግዚአብሔር ወንጌልን እንድንሰብክላቸው ጠርቶናል ብለን በመወሰን ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን።

ልድያ በፊልጵስዩስ በጌታ አመነች

11ከጢሮአዳ በመርከብ ተነሥተን በቀጥታ ተጕዘን ወደ ሳሞትራቄ መጣን፤ በማግስቱም ጕዟችንን ወደ ናጱሌ ቀጠልን፤ 12ከዚያም የሮማውያን ቅኝና የአካባቢው የመቄዶንያ ግዛት ዋና ከተማ ወደሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ ገባን፤ በዚያም አያሌ ቀን ተቀመጥን።

13በሰንበት ቀንም፣ የጸሎት ስፍራ በመፈለግ፣ ከከተማዪቱ በር ወጥተን ወደ አንድ ወንዝ ወረድን፤ በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩት ሴቶች መናገር ጀመርን። 14ከሚያዳምጡትም ሴቶች መካከል ልድያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም እግዚአብሔርን የምታመልክና ከትያጥሮን ከተማ የመጣች የቀይ ሐር ነጋዴ ነበረች። ጌታም፣ ጳውሎስ የሚናገረውን በማስተዋል ትሰማ ዘንድ ልቧን ከፈተላት። 15እርሷና ቤተ ሰዎቿ ከተጠመቁ በኋላም፣ “በጌታ ማመኔን በርግጥ ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ጥቂት ተቀመጡ” በማለት አጥብቃ ለመነችን።

ጳውሎስና ሲላስ በወህኒ ቤት

16አንድ ቀን ወደ ጸሎት ስፍራ ስንሄድ፣ በጥንቈላ መንፈስ ትንቢት የምትናገር አንዲት የቤት አገልጋይ አገኘችን፤ እርሷም በዚህ የጥንቈላ ሥራዋ ለአሳዳሪዎቿ ብዙ ገንዘብ ታስገኝላቸው ነበር። 17ይህችው አገልጋይ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የመዳንን መንገድ የሚነግሯችሁ፣ የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው!” በማለት ትጮኽ ነበር፤ 18ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመችው፤ ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ በመታወኩ ዘወር ብሎ ያን መንፈስ፣ “ከእርሷ እንድትወጣ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝዝሃለሁ” አለው፤ መንፈሱም በዚያው ቅጽበት ወጣላት።

19አሳዳሪዎቿም የገንዘብ ማግኛ ተስፋቸው ወጥቶ መሄዱን በተረዱ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው እየጐተቱ ባለ ሥልጣኖች ወዳሉበት ወደ ገበያ ቦታ አመጧቸው። 20ገዦቹም ፊት አቅርበዋቸው እንዲህ አሉ፤ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ፣ ከተማችንን አውከዋል፤ 21ደግሞም እኛ ሮማውያን መቀበል ወይም መፈጸም የማይገባንን ልማድ በሕዝቡ መካከል ይነዛሉ።”

22ሕዝቡም ተባብረው በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተነሡባቸው፤ ገዦቹም ልብሳቸው ተገፍፎ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ። 23ክፉኛ ከተደበደቡ በኋላም ወደ ወህኒ ቤት አስገቧቸው፤ የወህኒ ቤት ጠባቂውም ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። 24እርሱም ይህን የመሰለ ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፣ ወደ ወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰራቸው።

25እኩለ ሌሊት አካባቢ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎቹ እስረኞችም ያዳምጧቸው ነበር። 26ድንገትም የወህኒ ቤቱን መሠረት የሚያናውጥ ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ሆነ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፈቱ፤ የሁሉም እስራት ተፈታ። 27የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ፣ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ለመግደል ሰይፉን መዘዘ። 28ጳውሎስ ግን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እኛ ሁላችን እዚሁ ስላለን፣ በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርስ!” ብሎ ጮኸ።

29የወህኒ ቤቱ ጠባቂም መብራት ለምኖ ወደ ውስጥ ዘልሎ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ላይ ወደቀ። 30ይዟቸው ከወጣ በኋላ፣ “እናንት ሰዎች፤ እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” አላቸው።

31እነርሱም፣ “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት። 32ከዚያም ለእርሱና በቤቱ ላሉት ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ። 33የወህኒ ቤት ጠባቂውም ሌሊት በዚያኑ ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን ዐጠበላቸው፤ ወዲያውም እርሱና ቤተ ሰቡ ሁሉ ተጠመቁ። 34የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ወደ ቤቱ ወስዶ ማእድ አቀረበላቸው፤ ከቤተ ሰቡም ሁሉ ጋር በእግዚአብሔር በማመኑ በደስታ ተሞላ።

35ሲነጋም፣ ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ፈተህ ልቀቃቸው” ብለው መኰንኖቻቸውን ላኩበት። 36የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ አዝዘዋል፤ ስለዚህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።

37ጳውሎስ ግን፣ “እኛ የሮም ዜጎች ሆነን ሳለን፣ በሕዝብ ፊት ያለ ፍርድ ደብድበው ወደ እስር ቤት ወረወሩን፤ ታዲያ አሁን በስውር ሊያስወጡን ይፈልጋሉ? ይህማ አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” አላቸው።

38መኰንኖቹም ይህንኑ ቃል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ እነርሱም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጎች መሆናቸውን ሲሰሙ ደነገጡ፤ 39እነርሱ ራሳቸውም መጥተው ይቅርታ ጠይቀው ከወህኒ ቤቱ አወጧቸው፤ ከተማውንም ለቅቀው እንዲሄዱ ለመኗቸው። 40ጳውሎስና ሲላስ ከእስር ቤቱ ከወጡ በኋላ ወደ ልድያ ቤት ሄዱ፤ በዚያም ወንድሞችን አግኝተው አበረታቷችው፤ ከዚያም በኋላ ሄዱ።

New International Reader’s Version

Acts 16:1-40

Timothy Joins Paul and Silas

1Paul came to Derbe. Then he went on to Lystra. A believer named Timothy lived there. His mother was Jewish and a believer. His father was a Greek. 2The believers at Lystra and Iconium said good things about Timothy. 3Paul wanted to take him along on the journey. So he circumcised Timothy because of the Jews who lived in that area. They all knew that Timothy’s father was a Greek. 4Paul and his companions traveled from town to town. They reported what the apostles and elders in Jerusalem had decided. The people were supposed to obey what was in the report. 5So the churches were made strong in the faith. The number of believers grew every day.

Paul’s Vision of the Man From Macedonia

6Paul and his companions traveled all through the area of Phrygia and Galatia. The Holy Spirit had kept them from preaching the word in Asia Minor. 7They came to the border of Mysia. From there they tried to enter Bithynia. But the Spirit of Jesus would not let them. 8So they passed by Mysia. Then they went down to Troas. 9During the night Paul had a vision. He saw a man from Macedonia standing and begging him. “Come over to Macedonia!” the man said. “Help us!” 10After Paul had seen the vision, we got ready at once to leave for Macedonia. We decided that God had called us to preach the good news there.

Lydia Becomes a Believer in Philippi

11At Troas we got into a boat. We sailed straight for Samothrace. The next day we went on to Neapolis. 12From there we traveled to Philippi, a Roman colony. It is an important city in that part of Macedonia. We stayed there several days.

13On the Sabbath day we went outside the city gate. We walked down to the river. There we expected to find a place of prayer. We sat down and began to speak to the women who had gathered together. 14One of the women listening was from the city of Thyatira. Her name was Lydia, and her business was selling purple cloth. She was a worshiper of God. The Lord opened her heart to accept Paul’s message. 15She and her family were baptized. Then she invited us to her home. “Do you consider me a believer in the Lord?” she asked. “If you do, come and stay at my house.” She succeeded in getting us to go home with her.

Paul and Silas Are Thrown Into Prison

16One day we were going to the place of prayer. On the way we were met by a female slave. She had a spirit that helped her tell people what was going to happen. She earned a lot of money for her owners by doing this. 17She followed Paul and the rest of us around. She shouted, “These men serve the Most High God. They are telling you how to be saved.” 18She kept this up for many days. Finally Paul became upset. Turning around, he spoke to the spirit that was in her. “In the name of Jesus Christ,” he said, “I command you to come out of her!” At that very moment the spirit left the woman.

19Her owners realized that their hope of making money was gone. So they grabbed Paul and Silas. They dragged them into the market place to face the authorities. 20They brought them to the judges. “These men are Jews,” her owners said. “They are making trouble in our city. 21They are suggesting practices that are against Roman law. These are practices we can’t accept or take part in.”

22The crowd joined the attack against Paul and Silas. The judges ordered that Paul and Silas be stripped and beaten with rods. 23They were whipped without mercy. Then they were thrown into prison. The jailer was commanded to guard them carefully. 24When he received these orders, he put Paul and Silas deep inside the prison. He fastened their feet so they couldn’t get away.

25About midnight Paul and Silas were praying. They were also singing hymns to God. The other prisoners were listening to them. 26Suddenly there was a powerful earthquake. It shook the prison from top to bottom. All at once the prison doors flew open. Everyone’s chains came loose. 27The jailer woke up. He saw that the prison doors were open. He pulled out his sword and was going to kill himself. He thought the prisoners had escaped. 28“Don’t harm yourself!” Paul shouted. “We are all here!”

29The jailer called out for some lights. He rushed in, shaking with fear. He fell down in front of Paul and Silas. 30Then he brought them out. He asked, “Sirs, what must I do to be saved?”

31They replied, “Believe in the Lord Jesus. Then you and everyone living in your house will be saved.” 32They spoke the word of the Lord to him. They also spoke to all the others in his house. 33At that hour of the night, the jailer took Paul and Silas and washed their wounds. Right away he and everyone who lived with him were baptized. 34The jailer brought them into his house. He set a meal in front of them. He and everyone who lived with him were filled with joy. They had become believers in God.

35Early in the morning the judges sent their officers to the jailer. They ordered him, “Let those men go.” 36The jailer told Paul, “The judges have ordered me to set you and Silas free. You can leave now. Go in peace.”

37But Paul replied to the officers. “They beat us in public,” he said. “We weren’t given a trial. And we are Roman citizens! They threw us into prison. And now do they want to get rid of us quietly? No! Let them come themselves and personally lead us out.”

38The officers reported this to the judges. When the judges heard that Paul and Silas were Roman citizens, they became afraid. 39So they came and said they were sorry. They led them out of the prison. Then they asked them to leave the city. 40After Paul and Silas came out of the prison, they went to Lydia’s house. There they met with the brothers and sisters. They told them to be brave. Then they left.