ሉቃስ 9 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሉቃስ 9:1-62

የዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መላክ

9፥3-5 ተጓ ምብ – ማቴ 10፥9-15ማር 6፥8-11

9፥7-9 ተጓ ምብ – ማቴ 14፥12ማር 6፥14-16

1ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያት በአንድነት ጠርቶ አጋንንትን ሁሉ እንዲያወጡ፣ ደዌንም እንዲፈውሱ ኀይልና ሥልጣን ሰጣቸው፤ 2ደግሞም የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩና የታመሙትን እንዲፈውሱ ላካቸው፤ 3እንዲህም አላቸው፤ “ለመንገዳችሁ በትር ቢሆን፣ ከረጢትም ቢሆን፣ እንጀራም ቢሆን፣ ገንዘብም ቢሆን፣ ሁለት ሁለት እጀ ጠባብም መያዝ አያስፈልጋችሁም። 4ከዚያ ከተማ እስከምትወጡ ድረስ መጀመሪያ በገባችሁበት በማንኛውም ቤት ቈዩ። 5የከተማው ሰዎች ሳይቀበሏችሁ ቀርተው ከተማቸውን ለቅቃችሁ ስትሄዱ፣ ምስክር እንዲሆንባቸው የእግራችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ።” 6እነርሱም በዚሁ መሠረት ወጥተው ወንጌልን እየሰበኩ በየቦታው ሁሉ ሕመምተኞችን እየፈወሱ በየመንደሩ ያልፉ ነበር።

7የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም፣ በዚህ ጊዜ የሆነውን ነገር ሁሉ ሰምቶ በሁኔታው ተደናገረ፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ዮሐንስ ከሙታን እንደ ተነሣ ያወሩ ነበር፤ 8ሌሎች ኤልያስ እንደ ተገለጠ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞዎቹ ነቢያት አንዱ ከሙታን እንደ ተነሣ ይናገሩ ነበር። 9ሄሮድስም፣ “መጥምቁ ዮሐንስን እኔው ራሴ ዐንገቱን አስቈርጬው ሞቷል፤ ታዲያ፣ ስለ እርሱ እንዲህ ሲወራ የምሰማው ይህ ሰው ማነው?” አለ፤ በዐይኑም ሊያየው ይሻ ነበር።

ኢየሱስ አምስት ሺሕ ሰዎችን መገበ

9፥10-17 ተጓ ምብ – ማቴ 14፥13-21ማር 6፥32-44ዮሐ 6፥5-13

9፥13-17 ተጓ ምብ – 2ነገ 4፥42-44

10ሐዋርያትም ተመልሰው በመጡ ጊዜ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት፤ እርሱም ይዟቸው ቤተ ሳይዳ ወደምትባል ከተማ በመሄድ ለብቻው ገለል አለ። 11ሕዝቡም ይህንኑ ዐውቀው ተከተሉት፤ እርሱም ተቀብሏቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ይነግራቸው ነበር፤ ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።

12ቀኑም ሊመሽ ሲል፣ ዐሥራ ሁለቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “ያለነው በምድረ በዳ ስለሆነ፣ ሕዝቡ ወደ አካባቢው መንደርና ገጠር ሄደው ማደሪያና ምግብ እንዲፈልጉ አሰናብታቸው” አሉት።

13እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተው ስጧቸው” አላቸው።

እነርሱም፣ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚበቃ ምግብ ሄደን ካልገዛን በስተቀር፣ እኛ ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ አይበልጥም” አሉት፤ 14አምስት ሺሕ ያህል ወንዶች በዚያ ነበሩና።

ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሕዝቡን በአምሳ በአምሳ ሰው መድባችሁ አስቀምጧቸው” አላቸው። 15ደቀ መዛሙርቱም በታዘዙት መሠረት ሰዎቹ እንዲቀመጡ አደረጉ። 16እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ ባረካቸው፤ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ። 17ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከእነርሱ የተረፈውን ቍርስራሽ እንጀራ ዐሥራ ሁለት መሶብ አነሡ።

ጴጥሮስ ስለ ኢየሱስ ማንነት መሰከረ

9፥18-20 ተጓ ምብ – ማቴ 16፥13-16ማር 8፥27-29

9፥22-27 ተጓ ምብ – ማቴ 16፥21-28ማር 8፥31–9፥1

18ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ እኔን ማን ነው ይሉኛል?” ብሎ ጠየቃቸው።

19እነርሱም፣ “አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ ሌሎች ደግሞ ከቀድሞ ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቷል ይላሉ” አሉት።

20እርሱም፣ “እናንተስ ማን ነው ትሉኛላችሁ?” አላቸው።

ጴጥሮስም፣ “አንተ የእግዚአብሔር መሲሕ9፥20 ወይም ክርስቶስ ነህ” ሲል መለሰለት።

21ኢየሱስም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አጥብቆ አስጠነቀቃቸው፤ 22ደግሞም፣ “የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል ይገባዋል፤ እንዲሁም በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሓፍት ዘንድ መናቅ፣ መገደልና በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መነሣት አለበት” አላቸው።

23ከዚያም ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “በኋላዬ ሊመጣ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም በየዕለቱ ተሸክሞ ይከተለኝ፤ 24ምክንያቱም ነፍሱን ሊያድናት የሚፈልግ ሁሉ ያጠፋታል፤ ነፍሱን ስለ እኔ ብሎ የሚያጠፋት ግን ያድናታል። 25ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ጥቅሙ ምንድን ነው? 26ማንም በእኔና በቃሌ ቢያፍር፣ የሰው ልጅ በራሱ ክብር እንዲሁም በአብና በቅዱሳን መላእክት ክብር ሲመጣ ያፍርበታል። 27እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መካከል የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳያዩ ሞትን የማይቀምሱ ሰዎች አሉ።”

የኢየሱስ መልክ መለወጥ

9፥28-36 ተጓ ምብ – ማቴ 17፥1-8ማር 9፥2-8

28ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ያህል በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስንና ያዕቆብን ይዞ ሊጸልይ ወደ አንድ ተራራ ወጣ። 29በመጸለይ ላይ እንዳለም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ መብረቅ የሚያንጸባርቅ ነጭ ሆነ። 30እነሆ፤ ሁለት ሰዎች፣ እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤ 31በክብርም ተገልጠው፣ በኢየሩሳሌም ይፈጸም ዘንድ ስላለው ከዚህ ዓለም ስለ መለየቱ ይናገሩ ነበር። 32ጴጥሮስና አብረውት የነበሩት ግን እንቅልፍ ተጭኗቸው ነበር፤ ሲነቁ ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ። 33ሰዎቹም ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፤ እዚህ ብንሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ስለዚህ ሦስት ዳስ እንሥራ፤ አንዱ ለአንተ፣ አንዱ ለሙሴ፣ አንዱም ለኤልያስ ይሆናል” አለው፤ የሚናገረውንም አያውቅም ነበር።

34ይህንም እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ፈሩ። 35ከደመናውም ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ። 36ድምፁም በተሰማ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ፤ ደቀ መዛሙርቱም ነገሩን በልባቸው ያዙ እንጂ ስላዩት ነገር በዚያን ወቅት ለማንም አልተናገሩም።

ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ ያለበትን ልጅ ፈወሰ

9፥37-4243-45 ተጓ ምብ – ማቴ 17፥14-182223ማር 9፥14-2730-32

37በማግስቱም ከተራራው ከወረዱ በኋላ፣ ብዙ ሕዝብ መጥቶ ኢየሱስን አገኘው። 38በዚህ ጊዜ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ “መምህር ሆይ፤ ያለኝ ልጅ እርሱ ብቻ ስለሆነ፣ ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ። 39መንፈስ ሲይዘው በድንገት ይጮኻል፤ ዐረፋ እያስደፈቀው ያንፈራግጠዋል፤ ጕዳትም ካደረሰበት በኋላ በስንት መከራ ይተወዋል፤ 40ደቀ መዛሙርትህ እንዲያወጡለት ለመንኋቸው፤ ነገር ግን አልቻሉም።”

41ኢየሱስም “እምነት የለሽ ጠማማ ትውልድ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? በል ልጅህን ወደዚህ አምጣው” አለ።

42ልጁ በመምጣት ላይ ሳለም ጋኔኑ መሬት ላይ ጥሎ አንፈራገጠው፤ ኢየሱስ ግን ርኩሱን9፥42 ወይም ክፉ መንፈስ ገሥጾ ልጁን ፈወሰው፤ ለአባቱም መልሶ ሰጠው። 43ሰዎቹም ሁሉ በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ።

እርሱ ባደረገው ሁሉ ሰዎች ሁሉ እየተገረሙ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ 44“ይህን የምነግራችሁን ነገር ከቶ እንዳትዘነጉ፤ የሰው ልጅ ዐልፎ በሰዎች እጅ ይሰጣልና” አለ። 45እነርሱ ግን ይህን አባባል አልተረዱም፤ እንዳያስተውሉ ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ መልሰው እንዳይጠይቁትም ፈሩ።

ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን?

9፥46-48 ተጓ ምብ – ማቴ 18፥1-5

9፥46-50 ተጓ ምብ – ማር 9፥33-40

46ከእነርሱ ማን እንደሚበልጥ በደቀ መዛሙርቱ መካከል ክርክር ተነሣ። 47ኢየሱስም የልባቸውን ሐሳብ ተረድቶ፣ አንድ ሕፃን ይዞ በአጠገቡ አቆመ፤ 48እንዲህም አላቸው፤ “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ማንም ቢኖር እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ደግሞ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ከሁሉ ይበልጣልና።”

49ዮሐንስም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየን፤ ከእኛ ጋር ሆኖ ስለማይከተል ልንከለክለው ሞከርን” አለው።

50ኢየሱስም፣ “አትከልክሉት፤ የማይቃወማችሁ ሁሉ እርሱ ከእናንተ ጋር ነውና” አለው።

የሰማርያ ሰዎች ተቃውሞ

51ኢየሱስ ወደ ሰማይ የሚያርግበት ጊዜ በመቃረቡ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ፤ 52አስቀድሞም መልእክተኞችን ወደዚያ ላከ። እነርሱም ሁኔታዎችን አስቀድመው ሊያመቻቹለት ወደ አንድ የሳምራውያን መንደር ገቡ። 53ሕዝቡ ግን ወደ ኢየሩሳሌም እያመራ መሆኑን ስላወቁ አልተቀበሉትም። 54ደቀ መዛሙርቱም ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ሲያዩ፣ “ጌታ ሆይ፤ ኤልያስ እንዳደረገው ሁሉ9፥54 አንዳንድ ቅጆች ኤልያስ እንዳደረገው ሁሉ የሚለው የላቸውም። እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት። 55ኢየሱስ ግን ዘወር ብሎ ገሠጻቸውና፣ “እናንተ ከምን ዐይነት መንፈስ እንደ ሆናችሁ አታውቁም፤ የሰው ልጅ የመጣው የሰውን ሕይወት ለማዳን ነው እንጂ ለማጥፋት አይደለምና” አላቸው፤ 56ወደ ሌላ መንደርም ሄዱ።9፥55፡56 አንዳንድ ቅጆች ገሠጻቸው ይላሉ፤ 56 ከዚያም ወደ ሌላ መንደር ይላሉ። በ55 ላይ በትምርተ ጥቅሱ ውስጥ የሚገኘው ዐረፍተ ነገር ተአማኒ በሆኑ ብዙ የጥንት ቅጆች ላይ አይገኝም።

ደቀ መዝሙርነት የሚያስከፍለው ዋጋ

9፥57-60 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥19-22

57በመንገድ ሲሄዱም አንድ ሰው ቀርቦ፣ “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።

58ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጐጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ዐንገቱን እንኳ የሚያስገባበት የለውም” አለው።

59ሌላውን ሰው ግን፣ “ተከተለኝ” አለው።

ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፤ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን ልቅበር” አለው።

60ኢየሱስም፣ “ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ” አለው።

61ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፤ መከተልስ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን ልመለስና መጀመሪያ የቤቴን ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለ።

62ኢየሱስ ግን፣ “ዕርፍ ጨብጦ ወደ ኋላ የሚመለከት ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” አለው።

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

路加福音 9:1-62

差遣十二使徒

1耶稣召集了十二个使徒,赐他们能力和权柄可以医病赶鬼, 2又差遣他们出去宣讲上帝国的福音、医治病人。 3耶稣叮嘱他们:“出门的时候,什么也不要带,不要带手杖、背包、干粮、金钱,也不要带两件衣服。 4有人家接待你们,就住下来,一直住到你们离开。 5如果有人不欢迎你们,你们在离开那城的时候,就把脚上的尘土跺掉,作为对他们的警告。”

6使徒领命出发,走遍各个乡村,到处宣扬福音,替人治病。

希律的困惑

7耶稣的事迹很快便传到希律耳中,令他十分困惑,因为有人说:“约翰死而复活了”, 8有人说:“以利亚显现了”,还有人说:“古代的某个先知复活了”。 9希律说:“约翰已经被我斩首,这个行奇事的人到底是谁呢?”于是他想见耶稣。

五饼二鱼的神迹

10使徒回来后,向耶稣报告了他们所行的事。随后耶稣带着他们悄悄地来到伯赛大城。 11但百姓发现了耶稣的行踪,随即也赶来了。耶稣接待他们,向他们宣讲天国的福音,医好了有病的人。 12黄昏将近,十二个使徒过来对耶稣说:“请遣散众人,好让他们到附近的村庄去借宿找吃的,因为这地方很偏僻。”

13耶稣对他们说:“你们给他们吃的吧。”

使徒们说:“我们只有五个饼和两条鱼,除非我们去买食物才够这么一大群人吃。” 14当时那里约有五千男人。

耶稣便对使徒说:“让这些人分组坐下,每组大约五十人。” 15于是使徒安排众人都坐好。 16耶稣拿起那五个饼、两条鱼,举目望着天祝谢后,掰开递给门徒,让他们分给众人。 17大家都吃饱了,把剩下的零碎收拾起来,竟装满了十二个篮子。

彼得宣告耶稣是基督

18有一次,耶稣独自祷告的时候,门徒也在旁边。

耶稣问他们:“人们说我是谁?”

19他们答道:“有人说你是施洗者约翰,也有人说你是以利亚,或是一位复活的古代先知。”

20耶稣对他们说:“那么,你们说我是谁?”

彼得回答说:“你是上帝所立的基督。”

21耶稣郑重地吩咐他们不许泄露祂的身份, 22又说:“人子必须受许多苦,被长老、祭司长和律法教师弃绝,杀害,但必在第三天复活。”

跟从主的代价

23耶稣又教导众人说:“如果有人要跟从我,就应当舍己,天天背起他的十字架跟从我。 24因为想救自己生命的,必失去生命;但为了我而失去生命的,必得到生命。 25人若赚得全世界,却失去自己或丧掉自己,又有什么益处呢? 26如果有人以我和我的道为耻,将来人子在自己、天父和圣天使的荣耀中降临时,也必以这人为耻。 27我实在告诉你们,有些站在这里的人在有生之年就必看见上帝的国。”

登山变象

28讲完这些话后大约八天,耶稣带着彼得约翰雅各一同到山上祷告。 29耶稣在祷告的时候,容貌改变了,衣裳洁白发光。 30忽然,摩西以利亚二人在跟耶稣交谈。 31二人在荣光中显现,谈论有关耶稣离世的事情,就是祂在耶路撒冷将要成就的事。 32彼得和两个同伴都困得睡着了,他们醒来后,看见了耶稣的荣光以及站在祂身边的两个人。 33摩西以利亚要离开时,彼得对耶稣说:“老师,我们在这里真好!让我们搭三座帐篷,一座给你,一座给摩西,一座给以利亚。”其实彼得并不知道自己在说什么。 34他的话还没说完,有一朵云彩飘来,笼罩他们,他们进入云彩中,都很害怕。 35云彩中有声音说:“这是我的儿子,是我拣选的,你们要听从祂!” 36声音消逝了,门徒只见耶稣独自在那里。那些日子,他们对这事都绝口不提,没有告诉任何人。

山下赶鬼

37次日,他们来到山下,有一大群人迎接耶稣。 38人群中有一个人高声喊叫:“老师,求求你看看我的儿子吧!他是我的独生子, 39鬼控制着他,他常常突然狂喊乱叫、抽搐、口吐白沫,倍受折磨,无休无止。 40我曾求过你的门徒把鬼赶出去,但他们都无能为力。”

41耶稣回答说:“唉!这又不信又败坏的世代啊!我要跟你们在一起容忍你们多久呢?把你的儿子带来吧。”

42那孩子走过来时,鬼又把他摔倒,使他抽搐,耶稣立刻斥责污鬼,把那孩子治好了,交给他父亲。 43大家看见了上帝的大能,都很惊奇。

再次预言受难

他们正为耶稣所做的一切惊讶不已时,耶稣对门徒说: 44“你们要牢记人子所说的话,因为祂将要被交到人的手里。” 45但门徒不明白这句话的意思,因为还没有向他们显明,他们听不懂,又不敢追问耶稣。

论地位

46门徒开始议论他们当中谁最伟大。 47耶稣知道他们的心思,就叫了一个小孩子来,让他站在自己身旁, 48然后对门徒说:“任何人为了我的缘故接待这样一个小孩子,就是接待我;接待我,就是接待差我来的那位。你们当中最卑微的其实是最伟大的。”

49约翰说:“老师,我们看见有人奉你的名赶鬼,就阻止他,因为他不是和我们一起跟从你的。” 50耶稣却对他说:“你不要阻止他,因为不反对你们的,就是支持你们的。”

不肯接待耶稣的村庄

51耶稣被接回天家的日子快到了,祂决定前往耶路撒冷52祂先派人到撒玛利亚的一个村庄去预备食宿, 53撒玛利亚人见他们是上耶路撒冷去的,不肯接待他们。 54祂的门徒雅各约翰见状,说:“主啊,你要我们9:54 有古卷加“像以利亚一样”。叫天上的火降下来烧死他们吗?” 55耶稣转过身来责备他们9:55 有古卷在“责备他们”之后有“说,‘你们的心如何,你们自己不知道,人子来是为了拯救人,不是为了毁灭人。’”56接着,一行人改道去另一个村子。

跟从主的代价

57在路上有人对耶稣说:“无论你往哪里去,我都要跟从你。”

58耶稣对他说:“狐狸有洞,飞鸟有窝,人子却没有安枕之处。”

59耶稣又对另一个人说:“跟从我!”但是那人说:“主啊,请让我先回去安葬我的父亲。”

60耶稣说:“让死人去埋葬他们的死人吧,你只管去传扬上帝国的福音。”

61又有一个人说:“主啊!我愿意跟从你,但请让我先回去向家人告别。”

62耶稣说:“手扶着犁向后看的人不配进上帝的国。”