ሉቃስ 4 – NASV & NIVUK

New Amharic Standard Version

ሉቃስ 4:1-44

የኢየሱስ መፈተን

4፥1-13 ተጓ ምብ – ማቴ 4፥1-11ማር 1፥1213

1ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ እንደ ተመለሰ፣ መንፈስ ወደ በረሓ ወሰደው፤ 2በዚያም አርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ፤ በእነዚያም ቀናት ምንም ሳይበላ ቈይቶ በመጨረሻ ተራበ።

3ዲያብሎስም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እስቲ ይህ ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዘው” አለው።

4ኢየሱስም፣ “ ‘ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ብሎ መለሰለት።

5ከዚያም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍታ ቦታ አውጥቶት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው፤ 6እንዲህም አለው፤ “የእነዚህ መንግሥታት ሥልጣንና ክብር ሁሉ ለእኔ ተሰጥቷል፤ እኔም ለምወድደው ስለምሰጥ፣ ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ 7ስለዚህ ብትሰግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።”

8ኢየሱስም መልሶ፣ “ ‘ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፤ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።

9ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደስ ጕልላት ላይ አቆመውና እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እስቲ ራስህን ከዚህ ወደ ታች ወርውር፤ 10ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤

“ ‘ይጠብቁህ ዘንድ፣

መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል፤

11እግርህም ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ፣

በእጆቻቸው ወደ ላይ አንሥተው ይይዙሃል።’ ”

12ኢየሱስም፣ “ ‘ጌታ አምላክህን አትፈታተነው’ ተብሏል” ብሎ መለሰለት።

13ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ከእርሱ ተለየ።

ኢየሱስ በናዝሬት ተቀባይነት ማጣቱ

14ኢየሱስም በመንፈስ ኀይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ዝናውም በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ወጣ። 15እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያመሰግነው ነበር።

16ከዚያም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገባ፤ ሊያነብብም ተነሥቶ ቆመ። 17የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልል መጽሐፍም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም መጽሐፍ በተረተረው ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ክፍል አገኘ፤

18“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤

ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣

እርሱ ቀብቶኛልና፤

ለታሰሩት መፈታትን፣

ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣

የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣

19የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል።”

20ከዚያም መጽሐፉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብ የነበሩትም ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። 21እርሱም፣ “ይህ በጆሯችሁ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” ይላቸው ጀመር።

22ሁሉም ስለ እርሱ በበጎ ይናገሩ ነበር፤ ደግሞም ከአንደበቱ በሚወጣ የጸጋ ቃል እየተገረሙ፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።

23እርሱም፣ “ ‘ባለ መድኀኒት ሆይ፤ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም ስታደርግ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ ከተማ ደግሞ አድርግ’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም” አላቸው።

24ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በገዛ አገሩ አይከበርም። 25ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ተዘግቶ ጽኑ ራብ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በነበረበት በኤልያስ ዘመን፣ ብዙ መበለቶች በእስራኤል ነበሩ፤ 26ኤልያስ ከእነዚህ መካከል ወደ አንዷም አልተላከም፤ ነገር ግን በሲዶና አገር በሰራፕታ ወደ ነበረችው መበለት ተላከ። 27በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች4፥27 የግሪኩ ቃል የግድ ከለምጽ ጋር ብቻ የተያያዘ ሳይሆን፣ የተለያየ የቈዳ በሽታዎች ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውላል። ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነዚያ መካከል ማንም አልነጻም።”

28በምኵራብ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በቍጣ ገነፈሉ፤ 29ከተቀመጡበትም ተነሥተው ከከተማው አስወጡት፤ ቍልቍል ሊጥሉትም ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ወሰዱት፤ 30እርሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ።

ኢየሱስ ርኩስ መንፈስ አስወጣ

4፥31-37 ተጓ ምብ – ማር 1፥21-28

31ከዚያም በገሊላ አውራጃ ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም በሰንበት ዕለት ሕዝቡን ያስተምር ጀመር፤ 32የሚናገረው በሥልጣን ስለ ነበር በትምህርቱ ተደነቁ።

33በምኵራብም የርኩስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ነበረ፤ እርሱም ከፍ ባለ ድምፅ ጮኾ፣ 34“ወዮ! የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፤ ምን የሚያገናኘን ጕዳይ አለ? የመጣኸው ልታጠፋን ነውን? አንተ ማን እንደ ሆንህ ዐውቃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ!” አለው።

35ኢየሱስም፣ “ጸጥ ብለህ ከዚህ ሰው ውጣ!” ብሎ ገሠጸው። ጋኔኑም ሰውየውን በሕዝቡ ሁሉ ፊት ጣለውና ምንም ጕዳት ሳያደርስበት ለቅቆት ወጣ።

36ሰዎቹም ሁሉ ተገረሙ፤ እርስ በእርሳቸውም፣ “ለመሆኑ ይህ ትምህርት ምንድን ነው? በሥልጣንና በኀይል ርኩሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም እኮ ይወጣሉ” ተባባሉ። 37የእርሱም ዝና በአካባቢው ወዳለው ስፍራ ሁሉ ወጣ።

ኢየሱስ ብዙ በሽተኞችን ፈወሰ

4፥38-41 ተጓ ምብ – ማቴ 8፥14-17

4፥38-43 ተጓ ምብ – ማር 1፥29-38

38ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከምኵራብ ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም ዐማት ኀይለኛ ትኵሳት ይዟት ታማ ነበር፤ እንዲፈውሳትም ስለ እርሷ ለመኑት። 39እርሱም ወደ ተኛችበት ጠጋ ብሎ በማጐንበስ ትኵሳቱን ገሠጸው፤ ትኵሳቱም ለቀቃትና ወዲያው ተነሥታ አስተናገደቻቸው።

40ፀሓይ መጥለቂያ ላይም፣ የተለያየ ሕመም ያደረባቸውን ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ ፈወሳቸው። 41አጋንንትም ደግሞ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” እያሉና እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ። እርሱ ግን ገሠጻቸው፤ ክርስቶስ4፥41 ወይም መሲሕ መሆኑንም ያውቁ ስለ ነበር፣ አንዳች እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

42ሲነጋም ኢየሱስ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ ሄደ፤ ሕዝቡም ይፈልጉት ነበር፤ እርሱ ወዳለበትም ቦታ መጡ፤ ከእነርሱ ተለይቶ እንዳይሄድ ሊከለክሉት ሞከሩ። 43እርሱ ግን፣ “ወደ ሌሎቹም ከተሞች ሄጄ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል መስበክ ይገባኛል፤ የተላክሁት ለዚሁ ዐላማ ነውና” አላቸው። 44በይሁዳ ምኵራቦችም መስበኩን ቀጠለ።

New International Version – UK

Luke 4:1-44

Jesus is tested in the wilderness

1Jesus, full of the Holy Spirit, left the Jordan and was led by the Spirit into the wilderness, 2where for forty days he was tempted4:2 The Greek for tempted can also mean tested. by the devil. He ate nothing during those days, and at the end of them he was hungry.

3The devil said to him, ‘If you are the Son of God, tell this stone to become bread.’

4Jesus answered, ‘It is written: “Man shall not live on bread alone.”4:4 Deut. 8:3

5The devil led him up to a high place and showed him in an instant all the kingdoms of the world. 6And he said to him, ‘I will give you all their authority and splendour; it has been given to me, and I can give it to anyone I want to. 7If you worship me, it will all be yours.’

8Jesus answered, ‘It is written: “Worship the Lord your God and serve him only.”4:8 Deut. 6:13

9The devil led him to Jerusalem and had him stand on the highest point of the temple. ‘If you are the Son of God,’ he said, ‘throw yourself down from here. 10For it is written:

‘ “He will command his angels concerning you

to guard you carefully;

11they will lift you up in their hands,

so that you will not strike your foot against a stone.”4:11 Psalm 91:11,12

12Jesus answered, ‘It is said: “Do not put the Lord your God to the test.”4:12 Deut. 6:16

13When the devil had finished all this tempting, he left him until an opportune time.

Jesus rejected at Nazareth

14Jesus returned to Galilee in the power of the Spirit, and news about him spread through the whole countryside. 15He was teaching in their synagogues, and everyone praised him.

16He went to Nazareth, where he had been brought up, and on the Sabbath day he went into the synagogue, as was his custom. He stood up to read, 17and the scroll of the prophet Isaiah was handed to him. Unrolling it, he found the place where it is written:

18‘The Spirit of the Lord is on me,

because he has anointed me

to proclaim good news to the poor.

He has sent me to proclaim freedom for the prisoners

and recovery of sight for the blind,

to set the oppressed free,

19to proclaim the year of the Lord’s favour.’4:19 Isaiah 61:1,2 (see Septuagint); Isaiah 58:6

20Then he rolled up the scroll, gave it back to the attendant and sat down. The eyes of everyone in the synagogue were fastened on him. 21He began by saying to them, ‘Today this scripture is fulfilled in your hearing.’

22All spoke well of him and were amazed at the gracious words that came from his lips. ‘Isn’t this Joseph’s son?’ they asked.

23Jesus said to them, ‘Surely you will quote this proverb to me: “Physician, heal yourself!” And you will tell me, “Do here in your home town what we have heard that you did in Capernaum.” ’

24‘Truly I tell you,’ he continued, ‘no prophet is accepted in his home town. 25I assure you that there were many widows in Israel in Elijah’s time, when the sky was shut for three and a half years and there was a severe famine throughout the land. 26Yet Elijah was not sent to any of them, but to a widow in Zarephath in the region of Sidon. 27And there were many in Israel with leprosy4:27 The Greek word traditionally translated leprosy was used for various diseases affecting the skin. in the time of Elisha the prophet, yet not one of them was cleansed – only Naaman the Syrian.’

28All the people in the synagogue were furious when they heard this. 29They got up, drove him out of the town, and took him to the brow of the hill on which the town was built, in order to throw him off the cliff. 30But he walked right through the crowd and went on his way.

Jesus drives out an impure spirit

31Then he went down to Capernaum, a town in Galilee, and on the Sabbath he taught the people. 32They were amazed at his teaching, because his words had authority.

33In the synagogue there was a man possessed by a demon, an impure spirit. He cried out at the top of his voice, 34‘Go away! What do you want with us, Jesus of Nazareth? Have you come to destroy us? I know who you are – the Holy One of God!’

35‘Be quiet!’ Jesus said sternly. ‘Come out of him!’ Then the demon threw the man down before them all and came out without injuring him.

36All the people were amazed and said to each other, ‘What words these are! With authority and power he gives orders to impure spirits and they come out!’ 37And the news about him spread throughout the surrounding area.

Jesus heals many

38Jesus left the synagogue and went to the home of Simon. Now Simon’s mother-in-law was suffering from a high fever, and they asked Jesus to help her. 39So he bent over her and rebuked the fever, and it left her. She got up at once and began to wait on them.

40At sunset, the people brought to Jesus all who had various kinds of illness, and laying his hands on each one, he healed them. 41Moreover, demons came out of many people, shouting, ‘You are the Son of God!’ But he rebuked them and would not allow them to speak, because they knew he was the Messiah.

42At daybreak, Jesus went out to a solitary place. The people were looking for him and when they came to where he was, they tried to keep him from leaving them. 43But he said, ‘I must proclaim the good news of the kingdom of God to the other towns also, because that is why I was sent.’ 44And he kept on preaching in the synagogues of Judea.