ሉቃስ 17 – NASV & NIRV

New Amharic Standard Version

ሉቃስ 17:1-37

ኀጢአት፣ እምነት፣ ኀላፊነት

1ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ “ሰዎችን የሚያሰናክል መምጣቱ አይቀርም፤ ነገር ግን ለመሰናክሉ መምጣት ምክንያት ለሚሆን ለዚያ ሰው ወዮለት። 2ይህ ሰው ከእነዚህ ከታናናሾች አንዱን ከሚያሰናክል፣ የወፍጮ ድንጋይ በዐንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለው ነበር። 3ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

“ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው። 4በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ፣ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር በለው።”

5ሐዋርያትም ጌታን፣ “እምነታችንን ጨምርልን” አሉት።

6ጌታም፣ “የሰናፍጭ ቅንጣት የምታህል እምነት ቢኖራችሁ፣ ይህን ሾላ፣ ‘ተነቅለህ ባሕር ውስጥ ተተከል’ ብትሉት ይታዘዝላችኋል” አላቸው።

7ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ከእናንተ መካከል አንድ ሰው ዐራሽ ወይም በግ ጠባቂ የሆነ አገልጋይ ቢኖረው፣ ከዕርሻ የተመለሰውን አገልጋዩን፣ ‘ቶሎ ወደ ማእድ ቅረብ’ ይለዋልን? 8ከዚህ ይልቅ፣ ‘እራቴን እንድበላ አዘጋጅልኝ፣ እኔ እስክበላና እስክጠጣ ድረስ ታጥቀህ አገልግለኝ፤ ከዚያ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ፤ ትጠጣለህ’ አይለውምን? 9እንግዲህ ይህ ሰው፣ አገልጋዩ የታዘዘውን በመፈጸሙ መልሶ ያመሰግነዋልን? 10ስለዚህ እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ፣ ‘ከቍጥር የማንገባ አገልጋዮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን ተግባር ፈጽመናል በሉ።’ ”

ከለምጽ የነጹ ዐሥር ሰዎች

11ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ፣ በሰማርያና በገሊላ ድንበር በኩል ዐለፈ፤ 12ወደ አንድ መንደር እንደ ገባም ለምጽ17፥12 የግሪኩ ቃል ከለምጽ ጋር ብቻ የተያያዘ ሳይሆን፣ የተለያዩ የቈዳ በሽታዎችን ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውላል። የያዛቸው ዐሥር ሰዎች አገኙት፤ እነርሱም በርቀት ቆመው፣ 13በታላቅ ድምፅ፣ “ኢየሱስ፤ ጌታ ሆይ፤ ራራልን!” አሉት።

14እርሱም ባያቸው ጊዜ፣ “ሂዱና ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ” አላቸው። እነርሱም ወደዚያው በመሄድ ላይ ሳሉ ነጹ።

15ከእነርሱም አንዱ መፈወሱን ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ፤ 16በኢየሱስም እግር ላይ በፊቱ ተደፍቶ አመሰገነው፤ ይህም ሰው ሳምራዊ ነበረ።

17ኢየሱስም እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “የነጹት ዐሥር ሰዎች አልነበሩምን? ታዲያ፣ ዘጠኙ የት ደረሱ? 18ከዚህ ከባዕድ ሰው በስተቀር ተመልሰው እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑ የሉም ማለት ነውን?” 19ሰውየውንም፣ “ተነሥተህ ሂድ፤ እምነትህ አድኖሃል” አለው።

የእግዚአብሔር መንግሥት መምጣት

17፥2627 ተጓ ምብ – ማቴ 24፥37-39

20ፈሪሳውያን የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ እንደምትመጣ ኢየሱስን በጠየቁት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር መንግሥት በሚታዩ ምልክቶች አትመጣም፤ 21ሰዎችም፣ ‘እዚህ ነው’ ወይም ‘እዚያ ነው’ ማለት አይችሉም፤ እነሆ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ17፥21 ወይም በውስጣቸው ናትና።”

22ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፤ “ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትመኙበት ጊዜ ይመጣል፤ ደግሞም አታዩትም። 23ሰዎች፣ ‘እዚያ ነው’ ወይም ‘እዚህ ነው’ ይሏችኋል፤ ተከትላችኋቸውም አትሂዱ፤ 24ምክንያቱም መብረቅ በርቆ ሰማዩን ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን ልክ እንደዚሁ ይሆናል። 25ነገር ግን ይህ ከመሆኑ በፊት የሰው ልጅ ብዙ መሠቃየትና በዚህም ትውልድ መናቅ ይኖርበታል።

26“በኖኅ ዘመን እንደ ሆነው ሁሉ፣ በሰው ልጅ ዘመንም እንደዚሁ ይሆናል። 27ኖኅ ወደ መርከቡ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር፤ የጥፋትም ውሃ መጥቶ ሁሉንም አጠፋቸው።

28“በሎጥ ዘመንም እንዲሁ ነበር፤ ሰዎች ይበሉና ይጠጡ፣ ይገዙና ይሸጡ፣ ተክል ይተክሉና ቤት ይሠሩ ነበር፤ 29ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ዕለት ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ በሙሉ አጠፋቸው።

30“የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንደዚሁ ይሆናል። 31በዚያን ቀን በቤቱ ጣራ ላይ ያለ፣ ማንም ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ለመውሰድ አይውረድ፤ እንዲሁም በዕርሻ ቦታ ያለ ሰው ወደ ኋላው አይመለስ። 32የሎጥን ሚስት አስታውሱ። 33ሕይወቱን ለማሰንበት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያቈያታል። 34እላችኋለሁ፤ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ይተኛሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። 35ሁለት ሴቶች አብረው ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች። 36ሁለት ሰዎች በዕርሻ ቦታ አብረው ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።”17፥36 አንዳንድ ቅጆች ቍጥር 36 የላቸውም።

37እነርሱም መልሰው፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወሰዱት ወዴት ነው?” አሉት።

እርሱም፣ “ጥንብ ባለበት አሞሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው።

New International Reader’s Version

Luke 17:1-37

Sin, Faith and Duty

1Jesus spoke to his disciples. “Things that make people sin are sure to come,” he said. “But how terrible it will be for anyone who causes those things to come! 2Suppose people lead one of these little ones to sin. It would be better for those people to be thrown into the sea with a millstone tied around their neck. 3So watch what you do.

“If your brother or sister sins against you, tell them they are wrong. Then if they turn away from their sins, forgive them. 4Suppose they sin against you seven times in one day. And suppose they come back to you each time and say, ‘I’m sorry.’ You must forgive them.”

5The apostles said to the Lord, “Give us more faith!”

6He replied, “Suppose you have faith as small as a mustard seed. Then you can say to this mulberry tree, ‘Be pulled up. Be planted in the sea.’ And it will obey you.

7“Suppose one of you has a servant plowing or looking after the sheep. And suppose the servant came in from the field. Will you say to him, ‘Come along now and sit down to eat’? 8No. Instead, you will say, ‘Prepare my supper. Get yourself ready. Wait on me while I eat and drink. Then after that you can eat and drink.’ 9Will you thank the servant because he did what he was told to do? 10It’s the same with you. Suppose you have done everything you were told to do. Then you should say, ‘We are not worthy to serve you. We have only done our duty.’ ”

Jesus Heals Ten Men Who Have a Skin Disease

11Jesus was on his way to Jerusalem. He traveled along the border between Samaria and Galilee. 12As he was going into a village, ten men met him. They had a skin disease. They were standing close by. 13And they called out in a loud voice, “Jesus! Master! Have pity on us!”

14Jesus saw them and said, “Go. Show yourselves to the priests.” While they were on the way, they were healed.

15When one of them saw that he was healed, he came back. He praised God in a loud voice. 16He threw himself at Jesus’ feet and thanked him. The man was a Samaritan.

17Jesus asked, “Weren’t all ten healed? Where are the other nine? 18Didn’t anyone else return and give praise to God except this outsider?” 19Then Jesus said to him, “Get up and go. Your faith has healed you.”

The Coming of God’s Kingdom

20Once the Pharisees asked Jesus when God’s kingdom would come. He replied, “The coming of God’s kingdom is not something you can see. 21People will not say, ‘Here it is.’ Or, ‘There it is.’ That’s because God’s kingdom is among you.”

22Then Jesus spoke to his disciples. “The time is coming,” he said, “when you will long to see one of the days of the Son of Man. But you won’t see it. 23People will tell you, ‘There he is!’ Or, ‘Here he is!’ Don’t go running off after them. 24When the Son of Man comes, he will be like the lightning. It flashes and lights up the sky from one end to the other. 25But first the Son of Man must suffer many things. He will not be accepted by the people of today.

26“Remember how it was in the days of Noah. It will be the same when the Son of Man comes. 27People were eating and drinking. They were getting married. They were giving their daughters to be married. They did all those things right up to the day Noah entered the ark. Then the flood came and destroyed them all.

28“It was the same in the days of Lot. People were eating and drinking. They were buying and selling. They were planting and building. 29But on the day Lot left Sodom, fire and sulfur rained down from heaven. And all the people were destroyed.

30“It will be just like that on the day the Son of Man is shown to the world. 31Suppose someone is on the housetop on that day. And suppose what they own is inside the house. They should not go down to get what they own. No one in the field should go back for anything either. 32Remember Lot’s wife! 33Whoever tries to keep their life will lose it. Whoever loses their life will keep it. 34I tell you, on that night two people will be in one bed. One person will be taken and the other left. 35-36Two women will be grinding grain together. One will be taken and the other left.”

37“Where, Lord?” his disciples asked.

He replied, “The vultures will gather where there is a dead body.”