ሆሴዕ 4 – NASV & CCB

New Amharic Standard Version

ሆሴዕ 4:1-19

በእስራኤል ላይ የቀረበ ክስ

1በምድሪቱ በምትኖሩ በእናንተ ላይ

እግዚአብሔር የሚያቀርበው ክስ ስላለው፣

እናንት እስራኤላውያን ይህን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤

“ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤

እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።

2በዚያ ያለው ርግማን4፥2 መርገምን ያመለክታል፣ መዋሸት፣ መግደል፣

መስረቅና ማመንዘር ብቻ ነው፤

ቃል ኪዳንን ሁሉ ያፈርሳሉ፤

ደም ማፍሰስና ግድያ ይበዛል።

3ስለዚህ ምድሪቱ አለቀሰች፤4፥3 ወይም ደረቀች

በውስጧም የሚኖሩ ሁሉ ኰሰመኑ፤

የምድር አራዊት፣ የሰማይ ወፎች፣

የባሕርም ዓሦች ዐለቁ።

4“ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤

ማንም ሌላውን አይወንጅል፤

በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣

ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።

5ቀንና ሌሊት ትደናበራላችሁ፤

ነቢያትም ከእናንተ ጋር ይደናበራሉ፤

ስለዚህ እናታችሁን አጠፋታለሁ፤

6ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቷል።

“ዕውቀትን ስለ ናቃችሁ፣

እኔም ካህናት እንዳትሆኑ ናቅኋችሁ፤

የአምላካችሁን ሕግ ስለ ረሳችሁ፣

እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።

7ካህናት በበዙ ቍጥር፣

በእኔ ላይ የሚያደርጉት ኀጢአት በዝቷል፤

ክብራቸውንም4፥7 ማሶሬቲክ የሚለው እንዲሁ ሲሆን የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት ግን ክብሬን ይላል። በውርደት ለውጠዋል።4፥7 ሱርስትና የጥንት ዕብራውያን ጸሐፍት ትውፊት የሚሉት እንዲሁ ሲሆን፣ ማሶሬቲክ ግን እለውጠዋለሁ ይላል።

8የሕዝቤ ኀጢአት ለመብል ሆኖላቸዋል፤

ርኩሰታቸውንም እጅግ ወደዱ።

9ካህናትም ከሕዝቡ የተለዩ አይደሉም፤

ሁሉንም እንደ መንገዳቸው እቀጣቸዋለሁ፤

እንደ ሥራቸውም እከፍላቸዋለሁ።

10“ይበላሉ ግን አይጠግቡም፤

ያመነዝራሉ ግን አይበዙም፤

እግዚአብሔርን በመተው፣

ራሳቸውን 11ለአመንዝራነት፣

ለአሮጌና ለአዲስ የወይን ጠጅ አሳልፈው ሰጡ፤

በእነዚህም የሕዝቤ ማስተዋል ተወሰደ፤

12ከዕንጨት የተሠራውን ጣዖት ምክር ይጠይቃሉ፤

ዘንጋቸውም ይመልስላቸዋል።

የአመንዝራነት መንፈስ ያስታቸዋል፤

ለአምላካቸውም ታማኝ አልሆኑም።

13በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤

መልካም ጥላ ባለው፣ በባሉጥ፣

በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣

በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቍርባን ያቀርባሉ።

ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን፣

ምራቶቻችሁም አመንዝራዎች ይሆናሉ።

14“ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ሲሆኑ፣

የልጆቻችሁም ሚስቶች ሲያመነዝሩ

አልቀጣቸውም።

ወንዶች ከጋለሞቶች ጋር ይሴስናሉ፤

ከቤተ ጣዖት ዘማውያን ጋር ይሠዋሉና፤

የማያስተውል ሕዝብ ወደ ጥፋት ይሄዳል!

15“እስራኤል ሆይ፤ አንቺ ብታመነዝሪም፣

ይሁዳ በበደለኛነት አትጠየቅ።

“ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤

ወደ ቤትአዌንም4፥15 ቤትአዌን የእግዚአብሔር ቤት የተባለችው ቤቴል ስትሆን፣ የቃሉ ትርጕም የክፋት ቤት ማለት ነው። አትውጡ፤

‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁም አትማሉ።

16እስራኤላውያን እንደ እልኸኛ ጊደር፣

እልኸኞች ናቸው፤

ታዲያ እግዚአብሔር እነርሱን በመልካም መስክ ውስጥ እንዳሉ የበግ ጠቦቶች

እንዴት ያሰማራቸዋል?

17ኤፍሬም ከጣዖት ጋር ተጣምሯል፤

እስቲ ተዉት፤

18መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣

ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤

ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወድዳሉ።

19ዐውሎ ነፋስ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል፤

መሥዋዕቶቻቸውም ኀፍረት ያመጡባቸዋል።”

Chinese Contemporary Bible (Simplified)

何西阿书 4:1-19

耶和华指控以色列

1以色列人啊,

你们要留心听耶和华的话。

祂指控住在这片土地上的居民,说:

“这片土地上的人不忠不信,

毫无良善,不认识上帝。

2他们咒诅、撒谎、凶杀、偷窃、通奸,

为所欲为,血案累累。

3所以,这片土地要哀鸣,

所有的居民都要消亡,

田间的野兽、空中的飞鸟、

水里的鱼类也要灭绝。”

4耶和华说:

“谁都不要指控别人,

谁都不要责备别人,

因为我要指控的是你们祭司。

5你们白天黑夜都要跌倒,

先知也要跟你们一起跌倒,

所以我要毁灭你们的母亲以色列

6我的子民因不认识我而遭毁灭。

因为你们拒绝认识我,

我也要拒绝让你们做我的祭司;

因为你们忘记我的律法,

我也要忘记你们的儿女。

7你们祭司越增多,

所犯的罪也越多,

所以我要使你们的尊荣变为羞耻。

8你们祭司借我子民的赎罪祭自肥,

满心希望他们犯罪。

9将来,我的子民如何,

你们祭司也如何。

我要照你们的所作所为惩罚你们、报应你们,

10使你们吃却不得饱足,

行淫却不得后代4:10 行淫却不得后代”此处的意思是指责以色列人祭拜迦南人掌管生育的神明。他们以为这样能带来更多后代。

因为你们背弃耶和华,

11沉溺酒色,丧失心志。

12“我的子民祈求木头,

随从木杖的指引。

淫乱的心使他们走入歧途,

他们不忠不贞,背弃他们的上帝。

13他们在山顶和高岗上的橡树、

杨树和栗树下献祭烧香,

因为树荫怡人。

“所以,你们的女儿卖淫,

你们的儿媳通奸。

14但我不会因此而惩罚她们,

因为你们也与娼妓苟合,

与庙妓一起献祭。

无知的民族必走向灭亡。

15“虽然以色列如同妓女,对我不忠,

但不要使犹大犯罪。

不要到吉甲去,

不要到伯·亚文4:15 伯·亚文”意思是“罪恶之家”,在此指伯特利。“伯特利”意思是“上帝之家”,但当时已变成祭拜偶像之地。去,

不要凭永活的耶和华起誓。

16以色列桀骜不驯,

如同桀骜不驯的母牛。

耶和华怎能牧养他们,

如同在草场上牧养羊羔呢?

17以法莲4:17 以法莲”为北国以色列最大的支派,圣经中有时用来代指北国以色列。本卷书中下同。与偶像为伍,

任由他吧!

18他们酒足兴尽之后,

便不住地行淫;

他们的首领恋慕羞耻之事。

19风要把他们卷走,

他们必因所献的祭而蒙羞。