ሆሴዕ 11 – NASV & CCBT

New Amharic Standard Version

ሆሴዕ 11:1-12

የእግዚአብሔር ፍቅር ለእስራኤል

1“እስራኤል ገና ሕፃን ሳለ ወደድሁት፤

ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት።

2እስራኤል ግን አብዝቼ በጠራኋቸው11፥2 አንዳንድ የሰብዓ ሊቃናት ቅጆች እንዲሁ ሲሆኑ፣ ዕብራይስጡ ግን በጠሯቸው ይላል። ቍጥር፣

አብዝተው ከእኔ11፥2 ሰብዐ ሊቃናት እንዲሁ ሲሆን፣ ዕብራይስጡ ግን ከእነርሱ ይላል። ራቁ፤

ለበኣል አማልክት ሠዉ፤

ለምስሎችም ዐጠኑ።

3ኤፍሬምን እጁን ይዤ፣

እንዲራመድ ያስተማርሁት እኔ ነበርሁ፤

ነገር ግን የፈወስኋቸው እኔ እንደ ሆንሁ፣

እነርሱ አላስተዋሉም።

4በሰው የርኅራኄ ገመድ፣

በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤

ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤

ዝቅ ብዬም መገብኋቸው።

5“ታዲያ ንስሓ መግባትን እንቢ በማለታቸው፣

ወደ ግብፅ አይመለሱምን?

አሦርስ አይገዛቸውምን?

6በከተሞቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዛል፤

የበሮቻቸውን መወርወሪያ ይቈርጣል፤

ስለ ክፉ ዕቅዳቸውም ይደመስሳቸዋል።

7ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤

ወደ ልዑል ቢጣሩም፣

በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።

8“ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ?

እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ?

እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ?

እንዴትስ እንደ ሲባዮ እፈጽምብሃለሁ?

ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤

ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቷል።

9የቍጣዬን መቅሠፍት አላመጣም፤

ተመልሼም ኤፍሬምን አላጠፋም፤

እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣

ሰው አይደለሁምና፣

በቍጣ አልመጣም።11፥9 ወይም በማንኛውም ከተማ ላይ በተቃውሞ አልመጣም

10እግዚአብሔርን ይከተላሉ፤

እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤

እርሱ ሲያገሣ፣

ልጆቹ እየተንቀጠቀጡ ከምዕራብ ይመጣሉ።

11እንደ ወፍ ከግብፅ፣

እንደ ርግብ ከአሦር፣

እየበረሩ ይመጣሉ፤

እኔም በቤታቸው አኖራቸዋለሁ”

ይላል እግዚአብሔር

የእስራኤል ኀጢአት

12ኤፍሬም በሐሰት፣

የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤

ይሁዳ ለአምላክ የማይገዛ፣

የታመነውን ቅዱሱን የሚቃወም ነው።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

何西阿書 11:1-12

耶和華對以色列的愛

1耶和華說:

以色列年幼時,我就愛他,

視他為兒子,把他從埃及召出來。

2可是,我越召喚他們,他們就跑得越遠,

巴力獻祭,向偶像燒香。

3是我教以法蓮學步,張開雙臂抱他們,

他們卻不知道是我醫治他們。

4我用慈繩愛索牽引他們,

解開他們所負的重軛,

彎腰餵養他們。

5「他們要返回埃及

亞述要統治他們,

因為他們不肯歸向我。

6刀劍之災要臨到他們的城邑,

毀壞他們的城門,將他們吞噬,

因為他們倚仗自己的計謀。

7我的子民執意離我而去,

他們雖然求告至高的我,

我也不會拯救他們。

8以法蓮啊,我怎能捨棄你?

以色列啊,我怎能棄絕你?

我怎能使你的下場如押瑪

我怎能對待你如對待洗扁

我的心意改變,我滿懷憐愛。

9我不再發烈怒,

也不再毀滅以法蓮

因為我是上帝,不是世人,

是住在你們中間的聖者,

我必不帶著烈怒來臨。

10以色列子民必跟隨耶和華,

祂要像獅子一樣吼叫。

祂吼叫的時候,

他們要戰戰兢兢地從西方來。

11他們必戰戰兢兢地來,

就像從埃及趕來的鳥兒,

像從亞述飛來的鴿子。

我要帶他們返回家園。

這是耶和華說的。」

對以色列和猶大的指控

12耶和華說:

以法蓮用謊話包圍我,

以色列家用詭詐環繞我;

猶大依然背離聖潔、信實的上帝11·12 猶大依然背離聖潔、信實的上帝」或譯為「猶大卻與上帝同行,忠於聖者」。