New Amharic Standard Version

ዘፍጥረት 12:1-20

የአብራም መጠራት

1እግዚአብሔር (ያህዌ) አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤት ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ።

2“ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤

ደግሞም እባርክሃለሁ፤

ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤

ለሌሎች በረከት ትሆናለህ።

3የሚባርኩህን እባርካለሁ፤

የሚረግሙህን እረግማለሁ፤

በምድር የሚኖሩ ሕዝቦች፣

በአንተ አማካይነት ይባረካሉ።”

4ስለዚህ አብራም እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ሲወጣ ዕድሜው 75 ዓመት ነበረ። 5አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ሳሉ ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዘው በመጓዝ ከነዓን ምድር ገቡ።

6አብራም ትልቁ የሞሬ ዛፍ እስከሚገኝበት እስከ ሴኬም ድረስ በምድሪቱ ዘልቆ ሄደ። በዚያን ጊዜ ከነዓናውያን በዚሁ ምድር ይኖሩ ነበር። 7እግዚአብሔርም (ያህዌ) ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። እርሱም ለተገለጠለት አምላክ (ያህዌ) በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠራ።

8ከዚያም ተነሥቶ ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወዳሉት ተራሮች ሄደ፤ ቤቴልን በምዕራብ፣ ጋይን በምሥራቅ አድርጎ ድንኳን ተከለ፣ በዚያም ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሠዊያ ሠራ፤ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ስም ጠርቶ ጸለየ። 9አብራምም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ ሄደ።

አብራም በግብፅ አገር

12፥10-20 ተጓ ምብ – ዘፍ 20፥1-18፤ 26፥1-11

10በዚያም ምድር ጽኑ ራብ ገብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አብራም ለጥቂት ጊዜ በዚያ ለመኖር ወደ ግብፅ ወረደ። 11ግብፅ ለመግባት ጥቂት ሲቀረው አብራም ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ውብ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤ 12ግብፃውያን አንቺን በሚያዩበት ጊዜ፣ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ብለው እኔን ይገድላሉ፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። 13ስለዚህ ለአንቺ ሲሉ እንዲንከባከቡኝ፣ ሕይወቴም እንድትተርፍ፣ ‘እኅቱ ነኝ’ በዪ።”

14አብራም በግብፅ አገር እንደ ደረሰ ግብፃውያን፣ ሦራ እጅግ ውብ ሴት እንደሆነች አዩ፤ 15የፈርዖንም ሹማምት ባዩአት ጊዜ፣ ለፈርዖን አድንቀው ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ወሰዷት። 16በእርሷም ምክንያት ፈርዖን አብራምን አክብሮ አስተናገደው፤ በጎችና ከብቶች፣ ተባዕትና እንስት አህዮች፣ ወንድና ሴት አገልጋዮች እንዲሁም ግመሎችን ሰጠው።

17እግዚአብሔርም (ያህዌ) በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና ቤተ ሰዎቹን በጽኑ ደዌ መታቸው። 18ከዚያም ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? ‘ሚስትህ እንደሆነች ለምን አልነገርኸኝም?’ 19ለምን ‘እኅቴ ናት’ አልኸኝ? ሚስቴ ላደርጋት ነበር። በል አሁንም ሚስትህ ይህችው፤ ይዘሃት ሂድ!” 20ከዚያም ፈርዖን ስለ አብራም ለባለ ሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

創世記 12:1-20

上帝呼召亞伯蘭

1耶和華對亞伯蘭說:「你要離開家鄉、親族和父親的家,到我要指示你的地方去。 2我必使你成為大國,我必賜福給你,使你聲名遠播。你必成為別人的祝福。 3我必賜福給那些祝福你的人,咒詛那些咒詛你的人。世上萬族必因你而蒙福。」

4亞伯蘭就照耶和華的吩咐離開哈蘭,侄兒羅得與他同行。那時亞伯蘭七十五歲。 5亞伯蘭帶著妻子撒萊、侄兒羅得以及在哈蘭積攢的財物和所得的奴僕啟程來到迦南。到了迦南以後, 6亞伯蘭繼續前行,來到示劍摩利橡樹12·6 橡樹」希伯來文是「大樹」,也可能指靈樹或聖樹,下同13·1814·1318·135·435·8那裡。當時迦南人住在那地方。 7耶和華向亞伯蘭顯現,對他說:「我要把這片土地賜給你的後裔。」亞伯蘭就在那裡為向他顯現的耶和華築了一座壇。 8然後,他們又啟程前往伯特利東面的山區,在那裡搭起帳篷。他們的西面是伯特利,東面是亞伯蘭又在那裡築了一座壇,求告耶和華。 9之後,亞伯蘭繼續前往南地。

亞伯蘭逃荒到埃及

10當時,那地方鬧饑荒,災情非常嚴重,亞伯蘭便下到埃及暫住。 11快要到埃及的時候,他對妻子撒萊說:「我知道你是個美貌的女子, 12埃及人看見你,一定會因為你是我的妻子而殺了我,讓你活著。 13所以,請你說你是我的妹妹,這樣他們會因為你而善待我,留我一命。」 14亞伯蘭一行到了埃及撒萊的美貌引起了埃及人的注意。 15法老的官員見了撒萊,就在法老面前稱讚她的美貌,她便被帶進法老的王宮。 16因為撒萊的緣故,法老厚待亞伯蘭,賞給他許多牛、羊、驢、駱駝和僕婢。

17耶和華因亞伯蘭妻子撒萊的緣故使法老和他全家患重病。 18法老便召見亞伯蘭,說:「你做的是什麼事?為什麼不告訴我她是你妻子? 19為什麼說她是你妹妹,以致我娶她為妻呢?現在你妻子在這裡,帶她走吧!」 20法老就吩咐人把亞伯蘭、他妻子以及他所有的一切都送走了。