New Amharic Standard Version

ዕንባቆም 2:1-20

1በመጠበቂያ ላይ እቆማለሁ፤

በምሽጒ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤

ምን እንደሚለኝ፣

ለክርክሩም2፥1 ወይም በተገሠጽሁ ጊዜ የምሰጠውን ምላሽ የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ።

የእግዚአብሔር መልስ

2እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰ፤

“በቀላሉ እንዲነበብ፣

ራእዩን ጻፈው፤

በሰሌዳም ላይ ቅረጸው።

3ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃልና፤

ስለ መጨረሻውም ይናገራል፤

እርሱም አይዋሽም፤

የሚዘገይ ቢመስልም ጠብቀው፤

በርግጥ ይመጣል2፥3 የሚመጣ ሰው እንዳለ የሚያመለክቱ አሉ።፤ ከቶም አይዘገይም።

4“እነሆ፤ እርሱ ታብዮአል፤

ምኞቱ ቀና አይደለም፤

ጻድቅ ግን በእምነት2፥4 በታማኝነቱ የሚሉ አሉ። ይኖራል።

5በእርግጥ የወይን ጠጅ አታሎታል፤

ትዕቢተኛ ነው፤ ከቶ አያርፍም፤

እንደ ሲኦል2፥5 መቃብር የሚሉ አሉ። ስስታም ነው፣

እንደ ሞት ከቶ አይጠግብም፤

ሕዝቦችን ለራሱ ይሰበስባል፤

ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል።

6“ታዲያ በእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ላይ በማፌዝና በመዘበት እንዲህ እያሉ ሁሉም አይሣለቁበትምን?

“የተሰረቀውን ሸቀጥ ለራሱ ለሚያከማች፣

ራሱን በዐመፅ ባለጠጋ ለሚያደርግ ወዮለት!

ይህ የሚቀጥለውስ እስከ መቼ ነው?”

7ባለ ዕዳ2፥7 ወይም አበዳሪ ያደረግሃቸው ድንገት አይነሡብህምን?

ነቅተውስ አያስደነግጡህምን?

በእጃቸውም ትወድቃለህ።

8አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ፣

የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፤

የሰው ደም አፍሰሃልና፤

አገሮችንና ከተሞችን፣ በውስጣቸው የሚኖሩትን ሁሉ አጥፍተሃል።

9“በተጭበረበረ ትርፍ መኖሪያውን ለሚገነባ፣

ከጠላት እጅ ለማምለጥ፣

ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት!

10የብዙ ሰዎች ነፍስ እንዲጠፋ አሢረሃል፤

በገዛ ቤትህ ላይ ውርደትን፣ በራስህም ላይ ጥፋትን አምጥተሃል።

11ድንጋይ ከቅጥሩ ውስጥ ይጮኻል፤

ከዕንጨት የተሠሩ ተሸካሚዎችም ይመልሱለታል።

12“ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚሠራ፣

በወንጀልም ለሚመሠርታት ወዮለት።

13ሰዎች ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣

ሕዝቦችም በከንቱ እንዲደክሙ፣

እግዚአብሔር ጸባኦት ወስኖ የለምን?

14ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን ሁሉ፣

ምድርም የእግዚአብሔርን ክብር በማወቅ ትሞላለችና።

15“ኀፍረተ ሥጋቸውን ለማየት፤

ባልንጀሮቹን ለሚያጠጣ፣

እስኪሰክሩም ድረስ ወይን ለሚቀዳላቸው ወዮለት!

16በክብር ፈንታ ዕፍረት ትሞላለህ፤

አሁን ደግሞ ተራው የአንተ ነውና፤ ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤

በእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ ይመለስብሃል፤

ክብርህንም ውርደት ይሸፍነዋል።

17በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤

እንስሳቱን ማጥፋትህም ያስደነግጥሃል፤

የሰው ደም አፍሰሃልና፤

አገሮችንና ከተሞችን በውስጣቸው የሚኖሩትንም ሁሉ አጥፍተሃልና።

18“የሰው እጅ የቀረጸው ጣዖት፣

ሐሰትንም የሚናገር ምስል ምን ፋይዳ አለው?

ሠሪው በገዛ እጁ ሥራ ይታመናልና፣

መናገር የማይችሉ ጣዖታትን ይሠራልና።

19ዕንጨቱን፣ ‘ንቃ!’

ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ፣ ‘ተነሣ!’ ለሚል ወዮለት፤

በውኑ ማስተማር ይችላልን?

እነሆ፤ በወርቅና በብር ተለብጦአል፤

እስትንፋስም የለውም።

20እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣

ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል።

Chinese Contemporary Bible (Traditional)

哈巴谷書 2:1-20

1我要登上瞭望塔,

站在望樓上等候,

看耶和華要對我說什麼,

要怎樣答覆我的抱怨。

耶和華的答覆

2耶和華對我說:

「將我的啟示記下來,

清楚地刻在版上,

便於人們閱讀。

3這啟示實現的日期還沒到,

它是關於末後的事,沒有虛假。

即使緩慢,也要等候,

因為這事終必發生,不再遲延。

4看那驕傲之人,他們心術不正,

但義人必靠信心2·4 信心」或譯「忠信」。而活。

5財富2·5 「財富」參照死海古卷,多個希伯來抄本為「酒」。會欺騙人,

使驕傲之人永不安分,

像陰間一樣貪得無厭,

如死亡一般永不滿足。

因此,他們征服列國,

擄掠萬民。

6「但那些被擄的人必用詩歌和俗語嘲諷他們,說,

『你們有禍了!

你們吞沒別人的財產,

靠剝削別人囤積財富,

要到何時呢?』

7向你們借債的人必突然攻擊你們,

使你們戰戰兢兢,

成為俘虜。

8你們從前擄掠許多國家,

殺人流血,

摧毀他們的土地、城市和人民,

所以各國的餘民必掠奪你們。

9「為自己的家積蓄不義之財、

在高處搭窩躲避災禍的人啊,

你們有禍了!

10你們陰謀毀滅各族,

以致自辱己家,自害己命。

11牆上的石頭必高聲指控你們,

房子的梁木必同聲回應。

12「以人血建城邑,

以罪惡造城池的人啊,

你們有禍了!

13列邦的財富都化為灰燼,

列國勞碌卻是一場空。

這不都是出於萬軍之耶和華嗎?

14大地必充滿對耶和華之榮耀的認識,

就像海洋充滿了水一樣。

15「用酒灌醉鄰居以觀看他們祼體的人啊,

你們有禍了!

16你們必飽受羞辱,毫無榮耀。

你們喝吧,露出下體吧!

耶和華右手中的杯將傳給你們,

你們的榮耀將變成羞辱。

17你們以暴虐對待黎巴嫩

自己必被暴虐吞噬;

你們毀滅野獸,

自己必被恐怖籠罩。

因為你們殺人流血,

摧毀土地、城市和人民。

18「雕刻的偶像有什麼益處?

騙人的鑄像有什麼用處?

製造者竟信靠自己造的啞巴偶像!

19對木頭說『醒醒吧』,

對啞巴石頭說『起來吧』的人啊,你們有禍了!

它們能教導你們嗎?

看啊,它們外面包金裹銀,

裡面卻毫無生命。

20但耶和華住在祂的聖殿中,

世人都要在祂面前肅靜。」